Ethiopia Zare (ረቡዕ ሚያዝያ 13 ቀን 2002 ዓ.ም. April 21, 2010)፦ እሁድ ሚያዝያ 10 ቀን 2002 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ባልደረቦች የሆኑ ትራፊኮችና ሌሎች የፖሊስ አባላት ለሥልጠና ወደ ሰንዳፋ ማምራታቸው ተገለጸ።

 

የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን ኃላፊዎች እንደገለጹት ምርጫ 2002ን እና ሥጋቱን በተመለከተ ፖለቲካዊና የአድማ ብተና ሥልጠና ለአንድ ሣምንት ለማግኘት በመቶዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶች ወደ ሰንዳፋ አምርተዋል። መንግሥት ከፌደራልና ከአድማ በታኝ ልዩ ግበረ-ኃይል በተጨማሪ ሁሉም ፖሊሶች (ትራፊኮችን ጨምሮ) ወደዚህ መሰሉ ሥልጠና ያመራሉ።

 

እሁድ ሚያዝያ 10 ቀን ወደ ሰንዳፋ ያመሩት ፖሊሶች ከሥልጠናው ሲመለሱ ሌሎች ለተመሳሳይ ሥልጠና ወደዚያው እንደሚያመሩ ለማወቅ ተችሏል።

 

ከዚህ በፊት ሠልጥነዋል የተባሉ አድማ በታኝ የፌደራል ፖሊሶች በጃልሜዳ አካባቢ ሰፍረው በአራት ኪሎ አካባቢ በሠራተኞችና ተማሪዎች መውጫና መግቢያ ሰዓት ይዘዋወሩ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!