Ethiopia Zare (እሁድ ግንቦት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. May 9, 2010)፦ አንድ ወራት የአድማ ብተና ሥልጠና ያገኙ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን 621 የፖሊስ አባላት በትናንትናው ዕለት ተመረቁ።

 

 

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ በጥበቃና ተዘዋዋሪ ኃይል ውስጥ ሲያገለግሉ የነበሩት እነዚሁ ሠልጣኞች፤ ሥልጣናውን ያገኙት በጦላይ መሆኑ ታውቋል።

 

ሠልጣኞቹ ለ167 ሰዓታት ሥልጠና ያገኙ ሲሆን፣ በምረቃው ሥነሥርዓት ላይ የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ምክትል ኮሚሽነት ይህድጎ ሥዩም ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

 

ምክትል ኮሚሽነሩ፣ በፊታችን ምርጫ ”መንግሥትና ህዝብ የጣለባችሁን ኃላፊነት በተገቢው መንገድ መወጣት ይጠበቅባችኋል” በማለት ለተመራቂዎቹ ንግግር ማድረጋቸው ታውቋል።

 

ከዚህ ቀድም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሥራ መውጫና መግቢያ ሰዓት እንዲሁም በጃንሜዳ አካባቢ አድማ ብተና ሠልጣኞች ልምምድ ሲያደርጉ እንደነበር መዘገባችን አይዘነጋም።

 

ኢህአዲግ ሥልጣን ከያዘበት ከግንቦት 1983 ዓ.ም. ጀምሮ ሦስት ምርጫዎች መካሄዳቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ የዛሬ ሁለት ሣምንት፣ ግንቦት 15 ቀን 2002 ዓ.ም. ደግሞ አራተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ እንደሚካሄድ ይታወቃል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ