በስደት ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች መግለጫ አወጡ
እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬና ርዕዮት ዓለሙ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቀዋል
Ethiopia Zare (ሰኞ መስከረም 15 ቀን 2004 ዓ.ም. September 26, 2011)፦ በነፃ ፕሬስ ላይ በሚደረገው ጫና፣ እስርና እንግልት ምክንያት በስደት ላይ የሚገኙ የነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች በ’ሽብርተኝነት’ ስም በእስር ላይ የሚገኙት እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ እና ርዕዮት ዓለሙ ላይ የተፈጸመውን እስር አወገዙ።
በአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደህንነት (ሆም ላንድ ሴኩሪቲ) በሚረዳው MIPT በተባለ የአሸባሪነትን የውስጥ ገመና በመበርበር የሚታወቅ ተቋም ከዓመታት በፊት አሸባሪ ድርጅቶች ጋር የቀላቀለው የኢህአዴግ አገዛዝ ጋዜጠኞችን “ሽብርተኛ” በማለት በሃሳብ ነፃነት ላይ የሚያደርሰውን አፈና ለዓለሙ ማኅበረሰብ ማጋለጣችንን እንቀጥላለን ብለዋል። ... (ሙሉውን መግለጫ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)



