ሁለት ቆሰሉ፣ አምስት ተረፉ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ግንቦት 12 ቀን 2000 ዓ.ም. May 20, 2008)፦ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አካባቢ ሚኒባስ ውስጥ በተከሰተ ፍንዳታ የሰው ሕይወት ማለፉን ከአዲስ አበባ ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰው ጥቆማ አስረዳ።

 

ከአዲስ አበባ የደረሰን ጥቆማ እንደሚያመለክተው ከሆነ አስር ሰዎችን ተሳፍረውበት የነበረ ሚኒባስ ላይ በደረሰው ከፍተኛ ፍንዳታ ምክንያት የሦስት ሰዎች ሕይወት ሲጠፋ፣ ሁለቱ በከፍተኛ ሁኔታ ቆስለዋል።

 

ሚኒባሱ ላይ ከነበሩት ተሳፋሪዎች ውስጥ አምስቱ መትረፋቸውን ይኸው ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰው ጥቆማ ያመለክታል።

 

ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ ፍንዳታውን አስመልክቶ ከመንግሥት የተደመጠም ሆነ የተሰጠ መግለጫ እስካሁን ድረስ የለም። ኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ በአዲስ አበባ የሚገኙ ሪፖርተሮቹ ጉዳዩን አጣርተው ዘገባ እስኪያቀርቡለት ድረስ እየተጠባበቀ ሲሆን፣ ዘገባው እንደደረሰን ለማቅረብ እንሞክራለን።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ