Ethiopia Zare (ኀሙስ ግንቦት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. May 29, 2008)፦ ኢህአዴግ አዲስ አበባን የተቆጣጠረበትን 17ኛ ዓመት ባከበረበት ረቡዕ ግንቦት 20 ቀን 2000 ዓ.ም. በነገሌ ቦረና ከተማ በሁለት ሆቴሎች ላይ ተወርውሮ በፈነዳ ቦምብ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ አምስት ቆሰሉ።

 

ነገሌ ቦረና ከአዲስ አበባ 595 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ስትሆን፣ የመጀመሪያው ፍንዳታ ”ኪዳነ ምሕረት” በተባለ ሆቴል ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በሦስት ደቂቃ ልዩነት ”ሹፌሮች ሆቴል” ሊፈነዳ ችሏል።

 

በቦምብ ፍንዳታው ከሞቱት ውስጥ ሁለቱ ሴቶች ሲሆኑ፣ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው አምስት ሰዎች ይርጋለም ከተማ በሚገኘው የይርጋለም ሆስፒታል ተኝተው በመታከም ላይ እንደሚገኙ ለማረጋገጥ ተችሏል።

 

ፖሊስ ፍንዳታው በተከሰተ ሰዓት በወቅቱ በቁጥጥር ሥር ያልዋለ ወጣት ወርውሮት ሲሮጥ መታየቱን ጠቁሟል። በዛሬው ዕለትም በፍንዳታ የተጠረጠሩ ሰዎችን መያዝ መጀመሩን አስታውቋል።

 

በሀገሪቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተደጋጋሚ ፍንዳታዎች መበራከታቸው ህዝቡን ስጋት ላይ እየጣለው መምጣቱን የኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ካሰባሰባቸው ሪፖርቶች ለመረዳት ችለናል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ