Ethiopia Zare (አርብ ጥቅምት 23 ቀን 2006 ዓ.ም November 1, 2013):- ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል በእስር ላይ የሚገኘውን የብእር ሰው፣ ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ ባለቤቷን እስክንድር ነጋን ተለይታ ከምትኖርበት ዋሽንግተን ዲሲ የሀገሯን የመጨረሻ ስንብት በሚመለከት ለህሊና እስረኞች ለሆኑት ታሳሪዎች ያስተላለፈችው መልእክት ይፋ ተደረገ።

 

ጋዜጠኛ ሰርካለም በእስር ቤት ከተወለደው የሰባት አመት ታዳጊ ልጇ ናፍቆት እስክንድር ጋር በአሁኑ ሰአት በአሜሪካን ሀገር የምትገኝ ሲሆን በአምባገነኖች እስር ላይ የተጣለውን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ዘወትር በየቀኑ ትጎበኝ የነበረች ብቸኛ ሴት እንደነበረች የሞታወቅ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ከሶስት ወራት በላይ ከምትገኝበት ሜሪላንድ ግዛት ለባለቤቷ፣ ለአንድነቱ ምክትል ሊቀመንበር አንዷለም አራጌ፣ ለአንተነህ ሙሉጌታ፣ ውብሸት ታዬ እና "ጽናት" ብላ ለጠራቻት ብርቱዋ አምደኛና መምህርት ርዕዮት አለሙን ጨምሮ በጨቋኞች እስር ቤት በግፍ ለታሰሩ ወገኖች መልእክቷን አስተላልፋለች።

እስክንድር ነጋ እስር ቤት ከመጣሉ በፊት ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ 'እንደ አንድ ዜጋ እርስዎን ለ21 አመት በስልጣን ላይ ማየት ሰለቸኝ" በማለት ስልጣናቸውን እንዲለቁ በመጠየቁ በደህንነቶች የአይን ቁራኛ ክትትልና እስር እንደተዳረገ አይዘነጋም።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ