የእነ ኃይሌ ገ/ሥላሴ ሥራ አስኪያጅ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 15 ቀን 2000 ዓ.ም. July 22, 2008)፦ የፊታችን ነሐሴ 3 ቀን 2000 ዓ.ም. (August 8, 2008) በሚከፈተው የቤጂንጉ ኦሎምፒክ የሚሳተፉ አትዮጵያውያን አትሌቶች ታወቁ። በዚህ በቻይና በሚደረገውና 17 ቀናት በቀሩት ኦሎምፒክ ላይ ኢትዮጵያ በአምስት የተለያዩ ውድድሮች በሴቶችም በወንዶችም ትሳተፋለች።

 

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የሆኑት ወ/ሮ ብስራት ጋሻውጠና በውድድሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ የተመረጡት አትሌቶች ካለምንም አድልዎና ብቃት ያላቸው መሆናችን መግለጻቸው ታውቋል። በማራቶን የሚሳተፉት አትሌቶች በቅርቡ ወደ ጃፓን ሄደው የእስያን አየር ንብረት ይለማመዱ ዘንድ ውሳኔ መተላለፉን ፕሬዝዳንትዋ አክለው ገልጸዋል።

 

ከዚህም ሌላ ወ/ሮ ብስራት የታዋቂ አትሌቶች ማናጀር የሆነው ሆላንዳዊው ጆስ ሄርሜንስ የታዋቂ አትሌቶቹን የቤጂንግ ተሳትፎ በሚመለከት ከአሁን በኋላ ምንም አይነት አስተያየት ለመገናኛ ብዙኃኖች እንዳይገልጽ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው ታውቋል። ጆስ ሄርሜንስ የአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴና የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ማናጀር (ሥራ አስኪያጅ) እንደሆነ ይታወቃል።

 

ኢትዮጵያ በቤጂንጉ ኦሎምፒክ በ10,000 ሜትር፣ በ5,000 ሜትር፣ በማራቶን፣ በ3,000 ሜትር መሰናክል እና በ1,500 ሜትር በወንዶችም በሴቶችም ትሳተፋለች።

 

በቤጂንጉ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው ርቀቶችና ተሳታፊ አትሌቶች ስም ዝርዝር፣

 

በ10,000 ሜትር

ወንዶች

ቀነኒሳ በቀለ፣ ስለሺ ስህን እና ኃይሌ ገ/ሥላሴ

 

ሴቶች

ጥሩነሽ ዲባባ፣ መስታወት ቱፋ እና እጅጋየሁ ዲባባ፣

 

በ5,000 ሜትር

ወንዶች

አብርሃም ጨርቆሴ፣ ታሪኩ በቀለ፣ ዓሊ አብዶሽ እና ቀነኒሳ በቀለ

 

ሴቶች

መሰረት ደፋር፣ መሰለች መልካሙ፣ በላይነሽ ፍቃዱ እና ጥሩነሽ ዲባባ

 

በማራቶን

ወንዶች

ድሪባ መርጋ፣ ፀጋዬ ከበደ እና ጋሻው መለስ

 

ሴቶች

ጌጤ ዋሚ፣ ድሬ ቱሬ እና ብርሃኔ አደሬ

 

በ3,000 ሜትር መሰናክል፣

ወንዶች

ናሆም መስፍን፣ ሮባ ጋሪ እና ያዕቆብ ጃርሶ

 

ሴቶች

ዘምዘም አህመድ፣ መቅደስ በቀለ እና ሶፊያ አሰፋ፣

 

በ1,500 ሜትር

ወንዶች

ደረሰ መኮንን፣ ደባ ዳባ እና ሙሉጌታ ወንድሙ፣

 

ሴቶች

ገለቴ ቡርቃ እና መስከረም አሰፋ በቤጂንጉ ኦሎምፒክ ይሳተፋሉ።

 

የቤጂንጉ ኦሎምፒክ ሰኞ ነሐሴ 3 ቀን 2000 ዓ.ም. (August 8, 2008) ተጀምሮ፣ እሁድ ነሐሴ 18 ቀን 2000 ዓ.ም. (August 24, 2008) ይጠናቀቃል።

 

የኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ለኢትዮጵያውያን አትሌቶቻችን መልካም ዕድል ከወዲሁ ይመኛል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ