Ethiopia Zare (ረቡዕ ነኀሴ 14 ቀን 2000 ዓ.ም. August 20, 2008)፦ ዛሬ በቤጂንግ በሦስት ምድብ በተደረገው የወንዶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ የተወዳደሩት ሦስቱም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውድድሩን በሦስተኝነት በመጨረስ ማጣሪያውን አልፈዋል።

 

ከምድብ አንድ አትሌት ታሪኩ በቀለ በ13፡37.63 ደቂቃ ሦስተኛ፣ ከምድብ ሁለት አትሌት አብርሃም ጨርቆስ በ13፡47.60 ደቂቃ ሦስተኝ፣ ከምድብ ሦስት አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በ13፡40.13 ደቂቃ ሦስተኛ በመውጣት ውድድራቸውን ጨርሰዋል።

 

አትሌት ዓሊ አብዶሽ በርቀቱ ይሳተፋሉ ከተባሉት አትሌቶች ውስጥ አንዱ ቢሆንም፣ አንድ ሀገር ሦስት አትሌቶችን ብቻ ማሰለፍ ስለሚፈቀድላት ሳይሳተፍ ቀርቷል።

 

የወንዶቹ የ5 ሺህ ፍፃሜ የፊታችን ቅዳሜ ነኀሴ 17 ቀን 2000 ዓ.ም. (August 23, 2008) በአዲስ አበባ ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ ዘጠኝ ሰዓት ከአስር ደቂቃ (3፡10 P.M. / 15፡10) ይካሄዳል። በዚህ የፍፃሜ ውድድር ላይ ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ”አረንጓዴ ጎርፍ” ይሠራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

 

የሴቶች 1,500 ሜትር መሰናል

 

የሴቶች 1,500 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ነገ ሐሙስ ነኀሴ 15 ቀን 2000 ዓ.ም. (August 21, 2008) በሦስት ምድቦች የሚካሄድ ሲሆን፣ አትሌት ገለቴ ቡርቃ እና አትሌት መስከረም አሰፋ ይሳተፋሉ።

 

ምድብ አንድ በአዲስ አበባ ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ ስምንት ሰዓት፣ ምድብ ሁለት ስምንት ሰዓት ከዘጠኝ ደቂቃ፣ ሦስተኛው ምድብ ደግሞ ስምት ሰዓት ከ18 ደቂቃ ይካሄዳሉ።

 

የፊታችን ዓርብ ነኀሴ 16 ቀን 2000 ዓ.ም. (August 23, 2008) በአዲስ አበባ ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ ለአስርዘጠኝ ሰዓት ከ10 ደቂቃ (3፡10 P.M. / 15፡10) ላይ ሲሆን፣ በተለይ በኢትዮጵያውያን አትሌቶቹ መሠረት ደፋር እና ጥሩነሽ ዲባባ መሃከል ከፍተኛ ፉክክር እንደሚኖር ስለተገመተ ውድድሩ በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል።

 

በአዲስ አበባ ሰዓት አቆጣጠር ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ተኩል (እሁድ ነኀሴ 18 ቀን 2000 ዓ.ም. - August 24, 2008) የወንዶች ማራቶን ይጀመራል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ