የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ስብሰባ ነገ ይካሔዳል
ኢሕአዴግ
በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል
ኢዛ (ዓርብ ኅዳር ፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 15, 2019)፦ የተለያዩ ውሣኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ የሚጠበቀው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ነገ ኅዳር 6 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደሚሰበሰብ ታወቀ።
ኮሚቴው በነገው ዕለት የሚሰበሰብባቸው ዝርዝር አጀንዳዎች ባይገለጹም፤ ከኢሕአዴግ ጽ/ቤ የወጣው መረጃ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚወያይና የወደፊቱን አቅጣጫዎችንም እንደሚያስቀምጥ ያስረዳል። (ኢዛ)



