አራት ሰዎች ሞተዋል

Ethiopia Zare (ሰኞ መስከረም ፲፱-19 ቀን ፳፻፩-2001 ዓ.ም. September 29, 2008)፦ እሁድ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ በጅጅጋ ከተማ "አንድነት" በተባለ ሆቴል በተከሰተ ፍንዳታ አራት ሰዎች መሞታቸውንና አስር ሰዎች መቁሰላቸውን ኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች አረጋገጡ።

 

ምንጮቹ እንዳረጋገጡት በአንድነት ሆቴል በድንገት የተከሰተው ፍንዳታ እስከ አሁን የቆሰሉ አስር ሰዎች ሲሆኑ፣ ከፍተኛ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ቁስለኞች ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ችለናል።

 

በአሁኑ ሰዓት ሲያፈነዳ ታይቷል የተባለ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፣ ምክንያቱና ማንነቱ እስካሁን ያልተረጋገጠ መሆኑ ታውቋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ