ሕገወጥ ገንዘብ

በሰበታ አንድ ፓኪስታናዊ ከተከራየበት ቤት አልጋ ሥር የተገኘው ገንዘብ

2,950 ዶላር እና የተለያዩ ገንዘቦችም ተይዘዋል
ገንዘቡ የተገኘው ፓኪስታናዊ ከተከራየበት ቤት ውስጥ ነው

ኢዛ (ረቡዕ መስከረም ፲፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. September 23, 2020)፦ በሰበታ ከተማ በሕገወጥ መንገድ በአንድ ቤት ውስጥ ከ3.75 ሚሊዮን ብር በላይ እና ሌሎች የተለያዩ አገር ገንዘቦች ተያዙ።

የከተማው አስተዳደር እንዳስታወቀው ከተያዘው ገንዘብ ውስጥ 3.75 ሚሊዮን ብር ሲሆን፣ 2,950 ዶላር እና የዱባይ የተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ፣ የኦማንና የፓኪስታን ገንዘቦች ናቸው።

እንደመረጃው ገንዘቡ የተያዘው አንድ ፓኪስታናዊ ተከራይቶ ከነበረበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው። ገንዘቡ ተሸሽጎ የነበረውም አልጋ ሥር ነው።

ገንዘቡ የተያዘው በሕብረተሰቡ ጥቆማና በጸጥታ ኃይሎች ክትትል ነው ተብሏል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ