ጋሹ ዱጋዝ

አቶ ጋሹ ዱጋዝ

ታጣቂዎች አንድ የውጭ ዜጋን ጨምሮ አሥራ አራት ንጹኀንን ገድለዋል

ኢዛ (ሐሙስ መስከረም ፳፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 8, 2020)፦ በተደጋጋሚ የጸጥታ ችግር ሲስተዋልበት በቆየው የመተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በመንቀሳቀስ ሽብር ሲፈጥሩ ነበሩ የተባሉ 14 ታጣቂዎችን መግደሉንና ሁለት መማረኩን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አስታወቀ።

በክልሉ በተለይ በመተከል ዞን ሥር ባሉ የተለያዩ ወረዳዎች ሰሞኑን በንጹኀን ዜጎች ላይ ጥቃት አድርሰው ከነበሩት ኃይሎች መካከል 14 ያህሉ መደምሰሳቸውንና ሁለቱ ደግሞ ከነሙሉ ትጥቃቸው መያዛቸውን የገለጹት የክልሉ የሰላም ግንባታና ጸጥታ ኃላፊ ናቸው።

ኃላፊው አቶ ጋሹ ዱጋዝ እንዳመለከቱት ሽብር ሲፈጥሩ በነበሩት ኃይሎች ላይ በተወሰደው እርምጃ አምስት ክላሽ እና ኋላ ቀር ናቸው የተባሉ አሥር የጦር መሣሪያዎች ተይዘዋል።

ከኃላፊው ገለጻ መረዳት እንደቻለውም ከሁለት ቀናት በፊት በዳንጉር ወረዳ ጉብላክ ቀበሌ ውስጥ 14 ንጹኀን ዜጎች በእነዚሁ ኃይሎች መገደላቸውንና ስምንት መቁሰላቸውን ነው። በጥቃቱ ሰለባ ከኾኑት መካከል አንዱ የውጭ ዜጋ ነው ተብሏል።

በመተከል ዞን በተደጋጋሚ የተከሰተውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ እና የክልሉ ልዩ ኃይል በጋራ እየሠሩ መኾኑም ተጠቅሷል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ