Amare Aregawi, journalist, Publisher & editor-in-chief of Reporter newspaperEthiopia Zare (ዓርብ ጥቅምት 21 ቀን 2001 ዓ.ም. October 31, 2008)፦ የሪፖርተር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅና ባለቤት አቶ አማረ አረጋዊ ባልታወቁ ሰዎች በድንጋይ ተደብድቦና ራሱን ስቶ ወደ ሆስፒታል መወሰዱን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች አረጋገጡ።

 

ጋዜጠኛ አማረ አረጋዊ ቦሌ አካባቢ በላዳ ታክሲ ውስጥ ሆነው ሲጠብቁት በነበሩ ሦስት ግለሰቦች በድንጋይ ጭንቅላቱና አንገቱ አካባቢ ባደረሱበት ከፍተኛ ድብደባ ብዙ ደም ስለፈሰሰው ራሱን በመሳቱ በሀያት ሆስፒታል በጥብቅ ቁጥጥር በሕክምና ላይ መሆኑ ታውቋል።

 

አቶ አማረ ልጆቹን ከትምህርት ቤት ሊያመጣ ከቀኑ አስር ሰዓት አካባቢ በመሄድ ላይ መሆኑ የተገመተ ሲሆን፣ ደብዳቢዎቹ ግለሰቦች በአካባቢው ህዝብ ሁለቱ የተያዙ ሲሆን፤ አንድኛው ግለሰብ ግን ሊያመልጥ ችሏል። የተያዙተ ሁለቱ ግለሰቦች በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኙ ለማወቅ ችለናል።

 

ኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኝነት በከፍተኛ አደጋ ላይ ነው የሚሉ አንድ ታዛቢ፤ በሀገሪቱ በራሱ የሚተማመን ዜጋ እንዳይኖርና ጭላንጭል የተከፈተችው የፕሬስ እንቅስቃሴ ደብዛዋ እንድትጠፋ የሚደረገው ያላሰለሰ ጥረት መኖሩን ሰሞኑን በጋዜጠኞች ላይ የሚደረገው የማይረባ ክስና ወከባ ያረጋግጣል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ