Prof. Mesfin W.Mariam, 090326 Sweden (Photo S)ፕ/ር መስፍን በቀንዱና በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ጽሑፍ አቀረቡ

Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 18 ቀን 2001 ዓ.ም. March 27, 2009)፦ በአፍሪካ ቀንድ በሚገኙት ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያና ጅቡቲ ሀገሮች ላይ ባተኮረውና ኀሙስ መጋቢት 17 ቀን በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በተደረገ የአንድ ሙሉ ቀን ሴሚናር ላይ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳና ጋዜጠኛ ዳዊት ይስኃቅ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸው ነበር። ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም በሁለት ርዕሰ ጉዳዮ ጽሑፍ አቀረቡ።

 

በግድያ ሕይወታቸውን ባጡት ተወዳጁ የቀድሞው የስዊድን ጠቅላይ ሚኒስትር ኡሎፍ ፓልመ ስም የሚጠራው ”ኡሎፍ ፓልመስ ዓለም አቀፍ ማዕከል” እና በስዊድን የሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ በመተባበር በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያዘጋጁት የአንድ ቀን ሴሚናር በስቶክሆልም ከተማ ከጠዋቱ አራት (10፡00) ሰዓት እስከ ረፋዱ ከሰዓት በኋላ 10 (16፡00) ሰዓት ድረስ ተካሂዷል።

 

Horn of Africa Seminar, Stockholm, 090326; (Photo S)የሴሚናሩ ዋና ዓላማ በእነዚህ የቀንዱ ሀገሮች እየተስፋፋና ስር እየሰደደ ያለውን ችግር በሚመለከት ለብዙኀኑ ለማሳወቅና ግንዛቤ ለማስጨበጥ እንደሆነ ለመረዳት ችለናል። ሴሚናሩን በንግግር የከፈቱት የሴሚናሩ አወያይ ጆዪ ፍራንስ ሲሆኑ፣ ጆዪ ከሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ የተወካዮች ምክር ቤት (የፓርላማ) አባል ናቸው።

 

በፕሮግራሙ መሠረት የመጀመሪያውን የተናጋሪነት ቦታ የተሰጣቸው ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ሲሆኑ፣ ከጠዋቱ 4፡15 (10፡15) ሰዓት እስከ 5፡30 (11፡30) ሰዓት በ”አፍሪካ ቀንድ” ዙሪያ ጽሑፍ አቅርበዋል። ፕ/ር መስፍን በከሰዓት በኋላውም ዝጅግት ላይ ኢትዮጵያን አስመልክቶ ከሰባት ሰዓት ተኩል (13፡30 ሰዓት) እስከ ስምንት ሰዓት (14፡00 ሰዓት) ድረስ ለተሰብሳቢዎቹ ንግግር አድርገዋል።

 

Paris Mohamed Ali (L), Rezene Tesfazion (R) 090326; (Photo S)ኤርትራን አስመልክቶ የሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ የፓርላማ አባል የሆኑት አቶ ረዘነ ተስፋጽዮን፣ ሶማሊያን አስመልክቶ ፓሪስ መሐመድ አሊ፣ እንዲሁም ጅቡቲን አስመልክቶ ሐሚድ ኢሣ ገለፃ አድርገዋል። በመጨረሻም በቀንዱ እያጋጠሙ ባሉ ችግሮችና በመፃይ ጉዳዮች ላይ ለአንድ ሰዓት የፓናል ውይይት ተደርጓል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ