ቅምሻ ስለአንጋፋው ጋዜጠኛ ፀጋዬ እንደሻው

Tsegaye Endeshaw, journalistEthiopia Zare (እሁድ መስከረም ፬ (4) ቀን ፳፻፩ (2001) ዓ.ም. September 14, 2008)፦ ባለፈው ዓመት ረቡዕ ጳጉሜን 5 ቀን 2000 ዓ.ም. አንጋፋው ጋዜጠኛ ፀጋዬ እንደሻው በ65 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ጋዜጠኛ ፀጋዬ ለጀርመን ድምፅ ራዲዮ የሀገር ቤት ወኪል እንደነበር አይዘነጋም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለቴዲ አፍሮ የአዲሱ ዓመት የመልካም ምኞት መግለጫዎች

Teddy AfroEthiopia Zare (ቅዳሜ መስከረም ፫ (3) ቀን ፳፻፩ (2001) ዓ.ም. September 13, 2008)፦ ላለፉት ድፍን አምስት ወራት “በመኪና ሰው ገጭተህ ገድለሃል” በሚል በእስር ላይ ለሚገኘው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አዲሱን ዓመት (፳፻፩ ዓ.ም.) ምክንያት በማድረግ የፖለቲካ መሪዎች፣ ታዋቂ ሰዎች እና የተለያዩ የኅብረተሰቡ ክፍሎች የእንኳን አደረሰህ መልዕክት እና የመልካም ምኞት መግለጫዎችን አስተላለፉ። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በደርግ ባለሥልጣናት ላይ የተጣለው የሞት ፍርድ ወደ ዕድሜ ልክ እንዲቀየር ሽምግልና ተጀመረ

Derg AuthoritiesEthiopia Zare (ዓርብ መስከረም ፪ (2) ቀን ፳፻፩ (2001) ዓ.ም. September 12, 2008)፦ ባለፈው ዓመት ግንቦት 18 ቀን 2000 ዓ.ም. የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኮ/ል መንግሥቱ ኃይለማርያምን ጨምሮ በሃያ የደርግ ባለሥልጣናት ላይ የሞት ፈርዶባቸው የነበረ ሲሆን፣ አሁን በእስር ላይ የሚገኙትና ሞት የተፈረደባቸው የደርግ ባለሥልጣናት ቅጣታቸው ወደ ዕድሜ ልክ እንዲቀየርላቸው ለማድረግ የሀገር ሽማግሌዎች ጥረት መጀመራቸውን ምንጮች ጠቆሙ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የተንቤን ነዋሪዎች ጠ/ሚ/ር መለስን ወቀሱ

PM Meles ZenawiEthiopia Zare (ዓርብ መስከረም ፪ (2) ቀን ፳፻፩ (2001) ዓ.ም. September 12, 2008)፦ጠ/ሚ/ር መለስ ተንቤንን ሲጎበኝ የከተማው ነዋሪ ”… ግንባር ቀደም ሆነን ታግለናል፣ ልጆቻችንን መሥዋዕት አድርገናል፣ ታዲያ ለምንድነው ያገለልከን? የመጣኸበትን መንገድ አይተኸዋል? ለሌሎች ክልሎች በጀት መድበህ እንደምታስገነባው ሁሉ ለምን ለእኛም እንደዛ አታደርግም? ስንዴ መጥቷል ተባልን ነገር ግን እንደሌሎቹ በገንዘባችን እንኳን ማግኘት አልቻልንም፣ በረሃብ እያለቅን ነው፣ ይኼ ሁሉ ሲሆን ዝም ብለህ የምታየን ለምንድነው? …” ሲል ተቃውሞውንና ቅሬታውን በማሰማት ጠ/ሚ/ር መለስን ወቀሰ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በትግራይ አምስት ዞኖች ብቻ 763 ሺህ ህዝብ አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ያስፈልገዋል

የረሃብ አደጋው ጨምሯል፣ ራያ እና እንደርታ ክፉኛ ተጠቅተዋል 

Ethiopia Zare (ዓርብ መስከረም ፪ (2) ቀን ፳፻፩ (2001) ዓ.ም. September 12, 2008)፦በመላው በኢትዮጵያ በቅርቡ በተለያዩ የዕርዳታ ድርጅቶች በተደረገ የዳሰሳ ጥናት በትግራይ በጣም በድርቅ አደጋው የተጠቁት ራያ እና እንደርታ ሲሆኑ፣ በእነዚህ አካባቢዎች 127 ሺህ ህዝብ በድርቁ ተጎድቷል። በአምስት የትግራይ ዞኖች 601 ሺህ ህዝብ አጣዳፊ ዕርዳታ፣ 162 ሺ ህዝብ ደግሞ የቅርብ ክትትል ያስፈልገዋል። በኢትዮጵያ ለተከሰተው ረሃብ ከሚያስፈልገው ዕርዳታ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የተገኘው ከግማሽ የማይበልጥ መሆኑ ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲሱ የዓባይ ድልድይ ተመረቀ

The new Abbai bridgeስያሜው ”ኅዳሴ” ተብሏል

Ethiopia Zare (ኀሙስ መስከረም ፩ (1)  ቀን ፳፻፩ (2001) ዓ.ም. September 11, 2008)፦ የዓባይ ድልድይ ያለበት እና ከጎሃ ጽዮን (ኦሮሚያ) እስከ ደጀን (ጎጃም) ድረስ ያለውን 40 ኪሎ ሜትር ርቀት የአስፋልት ሥራ 320 ሚሊዮን ብር ፈጅቶ እየተጠናቀቀ ሲሆን፣ የአባይ አዲሱ ድልድይ ረቡዕ ጳጉሜን 5 ቀን 2000 ዓ.ም. ተመረቀ። ስያሜው ”ኅዳሴ” ተብሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ15 ዓመቱ ታዳጊ በቡታጅራው ብጥብጥ እጁን አጥቷል

ከ66 ሰዎች በላይ ታስረዋል፣ እነሱን ለማስፈታት 20 ሽማግሌዎች አዲስ አበባ ናቸው

Abdulekerim, age 15, lost his right arm on Butajira conflictEthiopia Zare (ኀሙስ መስከረም ፩ (1) ቀን ፳፻፩ (2001) ዓ.ም. September 11, 2008)፦ በቡታጅራ ከተማ በተነሳው ብጥብጥ ቀኝ እጁን ያጣው አብዱልከሪም የተባለው የ15 ዓመት ታዳጊ ወጣት ”ነኀሴ 2 ቀን 2000 ዓ.ም. ከቤቴ ወጥቼ ወደ አያቴ ቤት ስዔድ፣ በድንገት ቀኝ እጄን በጥይት ተመታሁ። ሐኪም ቤት በሄድኩ ሰዓት አደጋው ከፍተኛ ስለሆነ፣ እጅህን መቆረጥ አለብህ ተባልኩና አደጋው በደረሰብኝ ማግስት በቡታጅራ ሆስፒታል ተቆረጥኩ” ብሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እንኳን ለ፳፻፩ (2001) ዓ.ም. አደረስዎ!

Ethiopia Zare (ኀሙስ መስከረም ፩ (1) ቀን ፳፻፩ (ለ2001) ዓ.ም. September 11, 2008)፦ በአዲስ አበባ ሰዓት አቆጣጠር መስከረም ፩ (1) ቀን ፪፻፩ (2001) ዓ.ም. ተጀምሯል። እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማትዮስ በሠላም አሸጋገርዎ! አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የደስታ፣ የብልጽግና፣ ... ከነቤተሰብዎ ይሁንልዎ! ... በአዲሱ ዓመት በኢትዮጵያችን ዲሞክራሲ፣ ሠላም፣ ፍትህ፣ ... ይሰፍን ዘንድ፤ የዜጎች ሰብዓዊ መብት፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት፣ ... ይከበር ዘንድ፤ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከችግር፣ ከችጋር፣ ከረሃብ፣ ከሰቆቃ፣ ከስደት፣ ከእስር፣ ከስቃይ፣ ከመንገላታት፣ ከድብደባ፣ ከግድያ፣ ... ይድን ዘንድ የኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ምኞት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢቲቪ የሥርጭት ሰዓቱን ሊጨምር ነው

ክልሎች ፕሮግራማቸውን በየክልላቸው ያደርጋሉ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጳጉሜን 4 ቀን 2000 ዓ.ም. September 09, 2008)፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ድርጅት ከመስከረም 1 ቀን 2001 ዓ.ም. ጀምሮ ከጧቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ድረስ ሥርጭቱን ሊያራዝም መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለፁ። የትግሪኛ እና የኦሮምኛ ፕሮግራሞች ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በየክልላቸው ይደረጋሉ መባሉ ተቃውሞ አስነስቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...