20210302 adwa

የቴዲ አፍሮ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ከ5 - 10 ዓመት እስር ይጠብቀዋል

የቴዲ አፍሮ ክስና እስር ዝርዝር ዘገባ

  • ‘ቃሊቲ’ መውረዱ ሴት አድናቂዎቹን በእንባ አራጨ

Teddi Afro

Ethiopia Zare (ዓርብ ሚያዝያ 10 ቀን 2000 ዓ.ም. April 18, 2008)፦ ከትናንት በስቲያ ረቡዕ ሚያዝያ 8 ቀን 2000 ዓ.ም. የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስምንተኛ ወንጀል ችሎት፤ (ለሁለት ዓመታት የዘለቀውንና የቅንጅት አመራሮች .. የተከሰሱበትን የሁለተኛ ወንጀል ችሎት በቀኝ ዳኝነት ሲያስችሉ በነበሩት) ዳኛ አቶ ልዑል ገብረ ማርያም ተሰይሟል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ምርጫ ትናንት፤ "ምርጫ" ዛሬ

ልዩ ሪፖርታዥ

Ethiopia Zare (ዓርብ ሚያዝያ 10 ቀን 2000 ዓ.ም. April 18, 2008)፦ “ምርጫ” የሚለው ቃል በኢትዮጵያውያኖች ዘንድ ሲነሳ ትውስታ የሚፈጥረው “ምርጫ 97” ነው። የምርጫ 97 ትዝታ ለሚቀጥሉት … ዓመታት ከኢትዮጵያውያኖች የትውስታ ሣጥን ይጠፋል ተብሎ አይታሰብም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አስተዳደር ዳይሬክተሩ ጉዳይ አልተቋጨም

  • ሪፖርቱ ለዳኞች ቀረበ
  • ከሥራ ታግደው እንዲጣራ ተጠየቀ
  • ዳይሬክተሩ መልቀቂያ አስገብተዋል
  • ሪፖርቱን ተከትሎ ጠ/ፍርድ ቤት እርምጃ መውሰድ ጀመረ

Ethiopia Zare (ዓርብ ሚያዝያ 10 ቀን 2000 ዓ.ም. April 18, 2008)፦ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዳኛቸው ካሳ በሠራተኞች ላይ ፈጽመውታል የተባለውን በደል እንዲያጣራ የተቋቋመው ኮሚቴ ሪፖርቱን ለሦስቱም ፍርድ ቤት ዳኞች አቀረበ። በአስቸኳይ ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድ ዳኞች የጠየቁ ሲሆን፣ አስተዳደር ዳይሬክተሩ የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸው ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዮድ አቢሲኒያ የባሕል ምግብ ቤት በእሳት ወደመ

Yod Abyissinia Traditional Restaurant on fireEthiopia Zare (ኀሙስ ሚያዝያ 9 ቀን 2000 ዓ.ም. April 17, 2008)፦ አዲስ አበባ ውስጥ በሚኪሌላንድ መንገድ የሚገኘውና የአቶ ትዕዛዙ ኮሬ ንብረት የሆነው "ዮድ አቢሲኒያ የባሕል ምግብ ቤት" ትናንት ሚያዝያ 8 ቀን 2000 ዓ.ም. በደረሰ የእሳት አደጋ ምግብ ቤቱ ሙሉ ለሙሉ ወደመ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድነት ፓርቲ በረቂቅ ሰነዶቹ ላይ ቅዳሜ ይወያያል

Ethiopia Zare (ኀሙስ ሚያዝያ 9 ቀን 2000 ዓ.ም. April 17, 2008)፦ በተቀዳሚት ምክትል ሊቀመንበሯ ወ/ት ብርቱካን የሚመራው የቀድሞው የቅንጅት የአመራር አባላት ለማቋቋም ላይ የሚገኙት አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሮግራም፣ በመመስረቻ ሰነድ እና በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ የፊታችን ቅዳሜ ውይይት ሊካሄድ እንደሆነ ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቴዲ አፍሮ ዛሬ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ገባ

Teddi Afro

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሚያዝያ 8 ቀን 2000 ዓ.ም. April 16, 2008) ዝነኛው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከዚህ ቀደም "በመኪና ሰው ገለህ አምልጠሀል" በሚል ተከሶበት በነበረው ክስ ምክንያት የፌደራል ዓቃቢ ሕግ የዋስትና መብት ሊሰጠው አይገባም በማለቱ የዋስ መብቱን በሚመለከት ውሳኔ እስኪሰጥ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት የተላከ መሆኑን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ጠቆመ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቦንብ ፍንዳታዎቹ ዝርዝር ዘገባ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሚያዝያ 7 ቀን 2000 ዓ.ም. April 15, 2008) ትናንት በሁለት የኖክ የነዳጅ ማደያዎች የደረሰውን ፍንዳታ የአሸባሪዎች ጥቃት ነው ሲል የኢህአዴግ መንግሥት ገለጠ። ድርጊቱን አቶ አየለ ጫሚሶ እና አቶ ልደቱ አያሌው ማውገዛቸውን የመንግሥት መገናኛ ብዙኀን ገለጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በትናንቱ ፍንዳታ ሦስት ሰዎች ሞቱ፣ 11 ሰዎች ቆሰሉ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሚያዝያ 7 ቀን 2000 ዓ.ም. April 15, 2008)፦ ትናንት አመሻሹ ላይ ወደ አስራ ሁለት ሰዓት ተኩል አካባቢ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ነዳጅ ማደያዎች ላይ በደረሰው የቦንብ ፍንዳታ የሦስት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ አስራ አንድ ሰዎች መቁሰላቸውን ከአዲስ አበባ ዛሬ ጠዋት የኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ የደረሰው መረጃ ጠቆመ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሼህ አላሙዲን ሁለት የነዳጅ ማደያዎች ፍንዳታ ተከሰተ

Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 6 ቀን 2000 ዓ.ም. April 14, 2008)፦ ንብረትነቱ የሼክ መሐመድ ሁሴን አላሙዲንን (በዋናነት)፣ የአቶ አብነት ገ/መስቀል እና የአቶ ታደሰ ጥላሁን የተባሉ አንድ ሌላ ባለሀብት የሆነው ናሽናል ኦይል ኩባንያ (ኖክ) በተባለው ነዳጅ ማደያ ላይ በዛሬው ዕለት ፍንዳ መድረሱን ከስፍራ የደረሰን ዘገባ አስረዳ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢህአዴግ የአንድነት ፓርቲን ፈቃድ ለመከልከል ሕግ አወጣ

“ሕጉ ሆን ተብሎ አንድነት ፓርቲን ለመምታትና ፈቃድ ለመከልከል የተነጣጠረ ነው”

የፖለቲካ ታዛቢዎች

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሚያዝያ 4 ቀን 2000 ዓ.ም. April 12, 2008) ኀሙስ ሚያዝያ 2 ቀን 2000 ዓ.ም. 23ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደው የተወካዮች ምክር ቤት ያፀደቀው የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ኢህአዴግ ለፈለገው ቡድን ብቻ እውቅና ለመስጠት እንዲያስችለው ተደርጎ የተረቀቀ መሆኑ ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...