አ.ሰ.አ.ድ.ድ.ማ. የአንድነት ፓርቲን ሕጋዊ ፈቃድ አስመልክቶ መግለጫ አወጣ
Ethiopia Zare (ሰኞ ነኀሴ 19 ቀን 2000 ዓ.ም. August 25, 2008)፦ ”አንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማኅበር” የተሰኘውና በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የአንድነት ፓርቲን ሕጋዊ ፈቃድ ማግኘት ተንተርሶ ”አንድነት ፓርቲ በአዲስ ምዕራፍ ይጀመራል!” በሚል ርዕስ መግለጫ አወጣ። በዚሁ መግለጫው ላይ ማኅበሩ ለፓርቲው የሚያስፈልገውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል።