ቴዎድሮስ ካሳሁን ዋስትና ተከለከለ

- በችሎቱ ብዙ ደህንነቶች ነበሩ
- 20 ሰዎች ታስረዋል
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሚያዝያ 21 ቀን 2000 ዓ.ም. April 29, 2008)፦ ታዋቂው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የዋስትና መብት የማይሰጠው መሆኑንና ክሱን በእስር ቤት ሆኖ እንዲከታተል ዛሬ የዋለው ችሎት መወሰኑን የአዲስ አበባው ሪፖርተራችን ከችሎት ዘገበ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሚያዝያ 21 ቀን 2000 ዓ.ም. April 29, 2008)፦ ታዋቂው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የዋስትና መብት የማይሰጠው መሆኑንና ክሱን በእስር ቤት ሆኖ እንዲከታተል ዛሬ የዋለው ችሎት መወሰኑን የአዲስ አበባው ሪፖርተራችን ከችሎት ዘገበ።
አምስት ሰዎች ብቻ እንዲጠይቁት ተፈቀደ
Ethiopia Zare (እሁድ ሚያዝያ 19 ቀን 2000 ዓ.ም. April 27, 2008)፦ ዝነኛው ድምጻዊ፣ የግጥምና ዜማ ደራሲ ቴዎድሮስ ካሳሁን ወደ ጨለማ ቤት መግባቱንና ውስን ሰዎች ብቻ እንዲጠይቁት መደረጉን ዛሬ የአዲስ አበባ ምንጮቻችን ገለጹ።
Ethiopia Zare (እሁድ ሚያዝያ 19 ቀን 2000 ዓ.ም. April 27, 2008)፦ ፍትህ ሚኒስቴር ኅዳር 17 ቀን 2000 ዓ.ም. የሙያ ግድፈት ፈጽመዋል ያላቸው ዳኞች በዲሲፕሊን እንዲጠየቁ ለዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ያቀረበውን ክስ ጉባዔው በሚያዝያ 9 ቀን 2000 ዓ.ም. በሰጠው ውሳኔ ውድቅ ማድረጉን እንዳስታወቀ ተዘገበ። ሃያ ገፆችን የያዘው የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ክሱን እና ምላሹን በዝርዝር ያብራራ ሲሆን፣ ፍትህ ሚኒስቴር ያቀረበውን አቤቱታም አስፍሯል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...Ethiopia Zare (ዓርብ ሚያዝያ 17 ቀን 2000 ዓ.ም. April 25, 2008)፦ የኢ.ፌ..ዲ.ሪ የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አሰፋ ከሲቶ እና ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ሐሺም ተውፊቅ የግለሰቦችን ጉዳይ በያዘ አንድ መዝገብ ላይ «ክስ ሳይቋረጥ ይቀጥል» በሚል የተለያየ ደብዳቤ ለፍርድ ቤት በመፃፍ ተወዛገቡ፡፡ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የወንጀል መምሪያም በዚሁ መዝገብና በአንድ ዓይነት ጉዳይ ሁለት የተለያዩ ውሳኔዎችን ሰጥቷል፡፡
ሙሉውን አስነብበኝ ...እነአቶ አንዳርጋቸው፣ መስፍን አማን፣ ዳንኤል አሰፋና ቸኮል ጌታሁንም አሉበት
Ethiopia Zare (ኀሙስ ሚያዝያ 16 ቀን 2000 ዓ.ም. April 24, 2008)፦ ዶ/ር ብርሃኑና ሌሎች አራት የቅንጅት አመራር አባላት በቀድሞው ቅንጅትም ሆነ አሁን በአገዛዙ አፈና ስማቸው ተወስዶባቸው በሌላ ስም ለመንቀሳቀስ ከወሰኑትና ራሳቸውን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህና ብለው ከሰየሙ የቅንጅት አባላት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸውና ራሳቸውን ያገለሉ መሆኑን ዛሬ ባወጡት መግለጫ ገለጹ።
- በፍርድ ቤት አካባቢ ህዝቡ በእጥፍ ጨምሯል
- ችሎቱ ሰፊ አዳራሽ ውስጥ ነበር

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሚያዝያ 15 ቀን 2000 ዓ.ም. April 23, 2008)፦ ቴዲ አፍሮ ዛሬ ወደ ችሎት ሲቀርብ በርካታ አድናቂዎቹና ጋዜጠኞች እንዲሁም ብዛት ያላቸው የፍርድ ቤቱ ሰራተኞች ከአሁን በፊት ከነበረው ችሎት ሰፋ ወዳለ አዳራሽ የተቀየረውን ቦታ አጨናንቀውት እንደነበር የአዲስ አበባ ሪፖርተራችን ዘገበ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሚያዝያ 14 ቀን 2000 ዓ.ም. April 22, 2008)፦ “ኳታር የኢትዮጵያን ብሔራዊ ደህንነት ለመጉዳት ያልፈነቀለችው ድንጋይ የለም። በኢትዮጵያ አለመረጋጋትን ለመፍጠርና ፀጥታዋን ለማናጋት የተነሱ ኃይሎች ሁሉ የኳታር ድጋፍና አይዞህ ባይነት አልተለያቸውም” በሚል የኢህአዴግ መንግሥት ከኳታር ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማቋረጡ ታወቀ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 13 ቀን 2000 ዓ.ም. April 21, 2008)፦ ዛሬ ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ላይ የከፍተኛው ፍርድ ቤት በፍርድ ቤት ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ በህዝብ ተጨናንቆ እንደነበር በችሎቱ አካባቢ የተገኙ የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ።
ምርጫው ሲጠናቀቅ ሩዝ ኪሎው ከ6 ወደ 12 ብር ገባ
Ethiopia Zare (እሁድ ሚያዝያ 12 ቀን 2000 ዓ.ም. April 20, 2008)፦ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ደውለን ባገኘነው መረጃ መሠረት ኢህአዴግ “አረጋግቼዋለሁ” ያለው የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች ዋጋ ከ15 % እስከ 100 % (በእጥፍ) ማደጉን ለመረዳት ችለናል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...Ethiopia Zare (እሁድ ሚያዝያ 12 ቀን 2000 ዓ.ም. April 20, 2008)፦ ባለፈው ዓመት እሁድ ጥር 13 ቀን ከንጋቱ 12 ሰዓት ከ30 ደቂቃ አካባቢ ላይ በላንጋኖ መዝናኛ ሥፍራ የተፈጸመው ፍቅረኛሞች አሳዛኝ ግድያ ተናፍሶ መቆየቱ ይታወሳል። የፍቅረኛሞቹ አሟሟት ሁኔታ አሁንም ድረስ አሳዛኝ ነው። ገዳይ ለግድያው የተጠቀመበትን ሽጉጥ የተቀበለው ከእናቱ የመሆኑ ወሬ መሰማት ደግሞ የሁሉንም ሰው ቀልብ ሲስብ፤ ለሟች ቤተሰቦች መሪር ኀዘንን መፍጠሩ ተዘገበ።