ዶ/ር ብርሃኑ በቫንኩቨር የተሳካ ውይይት አካሄዱ
(ውይይቱን በድምፅ አቅርበነዋል)
'በሞኖፖል የተያዘውን የኢትዮጵያ ሚድያ ከውጭ ሃገር ሆኖ መስበር ይቻላል' ዶ/ር ብርሃኑ

Ethiopia Zare (እሁድ ግንቦት 3 ቀን 2000 ዓ.ም. May 11, 2008)፦ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ትናንት ቅዳሜ ግንቦት 3 ቀን 2000 ዓ.ም. ከቫንኩቨር ነዋሪዎች ጋር ያካሄዱት ውይይት የተሳካና ግልጽ ውይይት አካሄዱ። ውይይቱ የተጀመረው በቀድሞ የአዲስ አበባ የኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፕሬዝዳንት የነበረው ተማሪ ተክለሚካኤል አበበ የዶ/ሩን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመምህርነት ተግባርና ከዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጋር የነበራቸውን ቅርርብ፣ በማስተማርና በመማር ሂደት ላይ ያላቸውን ችሎታ በማውሳትና ምስክርነት በመስጠት ነበር።
ሙሉውን አስነብበኝ ...




