ኢየሩሳሌም አርኣያ
በትግራይ ተምቤን - አብዪአዲ የሚገኘውና በጀግናው ራስ አሉላ አባነጋ ስም ተሰይሞ የቆየው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስያሜው ተቀይሮ በመለስ ዜናዊ ስም እንዲሰየም መወሰኑን ታማኝ ምንጮች አስታወቁ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥቅምት 28 ቀን 2005 ዓ.ም. November 7, 2012)፦ በዩናይትድ ስቴስ ኦፍ አሜሪካ እስከ ትናንት እኩለ ሌሊት ሲደረግ በነበረው ምርጫ ፕሬዝዳንት ባራክ ሁሴን ኦባማ ለሁለተኛ ጊዜ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል። ተቀናቃኛቸውን ሚት ሩምኒን 303 ኤሌክትሮ ቮት ለ206 ኤሌክትሮ ቮት በሆነ ልዩነት አሸንፈዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ጠበቆቹን አሰናብቶ ራሱ ይከራከራል
ሪፖርተር ጋዜጣ (በታምሩ ጽጌ)
በተከሰሰበት የሽብርተኝነት ወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ሰኔ 20 ቀን 2004 ዓ.ም. በ18 ዓመታት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ውሳኔውን በመቃወም ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበው ይግባኝ ተቀባይነት በማግኘቱ ለክርክር ለጥቅምት 27 ቀን 2005 ዓ.ም. ተቀጠረ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ሪፖርተር ጋዜጣ (በታምሩ ጽጌ)
የፌዴራል የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ኤጀንሲ እንዳያንቀሳቅሱ ያገደባቸውን ገንዘብ በሚመለከት፣ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብለው የነበሩት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባዔ (ኢሰመጉ) እና የኢትዮጵያ ሴት የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር (ኢሴሕባማ) ይግባኛቸው ውድቅ ሆኖ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲወረሱ ጥቅምት 9 ቀን 2005 ዓ.ም. ተወሰነ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የሃገር ወሬ (ታላቅ ሰው ምንአለ ከአዲስ አበባ)
ለመብራት ችግር ምክንያት የሆነውን ትራንስፎርመር ለመተካት 30 ሚሊየን ብር ተጠየቀ!
ትራንስፎርመሩን እንዴትና በማን እንደተሰረቀ እስካሁን አልተገለጸም!
Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥቅምት 7 ቀን 2005 ዓ.ም. October 17, 2012)፦ በአዲስ አበባ በርካታ አካባቢዎች በተለይም በቂርቆስ ክ/ከተማ፣ በየካ ክ/ከተማ፣ በጉለሌ ክ/ከተማ፣ በኮልፌ ቀራንዮና በአዲስ ከተማ ክ/ተማዎች ከፍተኛ የውሃ ዕጥረት ተስተውሏል። ሙሉውን አስነብበኝ ...
ማትያስ ከተማ
Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥቅምት 7 ቀን 2005 ዓ.ም. October 17, 2012)፦ በኢትዮጵያ እስር ቤት ለአስራ አራት ወራት ያህል በእስር የቆዩት ጋዜጠኛ ዮሐን ፐርሾን እና ጋዜጠኛ ማርቲን ሺቢ ከእስር ተለቀው ወደ ስዊድን ከገቡ በኋላ በተለያየ ጊዜና ቦታ ስዊድን ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር በመነጋገር ላይ ይገኛሉ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...በሞባይላቸው መልእክት የተላላኩ እየታደኑ ነው
Ethiopia Zare ቅዳሜ መስከረም 15 ቀን 2005 ዓ.ም. Sebtember 22, 2012)፦ የመለስ ዜናዊ ሞትና የቀብር ሥርዓታቸው አፈጻጸም ጉዳይ ረገብ አድርጎት የቆየው የሙስሊሞቹ የመብታችን ይከበር ጥያቄ ዓርብ መስከረም 11 ቀን 2005 ዓ፣ም በታላቁ አንዋር መስጂድ ሲቀጥል በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሙስሊሞች “መሪዎቻችን ይፈቱ! ያታሰሩት ሳይፈቱ የዑላማዎች ምርጫ አይካሄድም! ምርጫው የሚካሄደውም በመስጂድ ብቻ መሆን አለበት!መንግሥት ከጣልቃ ገብነት ተግባሩ ያታቀብ!...” የሚሉና ሌሎች የመብት ማስከበሪያ ጥያቄ ድምፆችን “አላህ ወ አክበር!” ከሚለው ተክቢራ ጋር ደጋግመው አሰምተዋል፡፡ ሙሉውን አስነብበኝ ...ትኩስ ወሬ ከሃገሬ - ሰኞመስከረም 7ቀን 2005 ዓ.ም
Ethiopia Zare (ሰኞ መስከረም 7 ቀን 2005 ዓ.ም. Sebtember 17, 2012)፦ የአህባሽን አስተምህሮ የሚቃወሙትንና መጅሊሱ እንዲለወጥ የሚጠይቁትን ሙስሊሞች ዓላማ ለማምከን እንደዚሁም ሕዝበ ሙስሊሙን በተለያየ አቋም ለመከፋፈል፤ኢሕአዴግ ከፍተኛ የካድሬ እንቅስቃሴ በማካሄድ ተግባር ተጠምዶአል። ሙሉውን አስነብበኝ ...አቶ ደሳለኝ ኃይለምሪያም ሊቀመንበር ሲሆኑ በምክትልነት አቶ ደመቀ መኮንን ተመርጠዋል
Ethiopia Zare (ቅዳሜ መስከረም 5 ቀን 2005 ዓ.ም. Sebtember 13, 2012)፦ ለበርካታ ወራት ቁርጡ ባልታወቀ የአመራር ክፍተት ሲታመስ ነበረው ህወሃት መራሹ የኢህአዴግ መንግስት ለ21 አመታት ሀገሪቱን በሽግግር መንግስት ፕሬዚዳንትነትና ጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩትን አቶ መለስ ዜናዊን ቦታ የሚተካ አመራር የመረጠ ሲሆን የድርጅቱ ዋና ሊቀመንበር አቶ ደሳለኝ ኃይለማሪያምን ሲመርጥ አቶ ደመቀ መኮነንን በምክትል ሊቀመንበርነት ሰየመ። ሙሉውን አስነብበኝ ...