በሱማሊያ የኢትዮጵያ ጦር ሰፈር በአጥፍቶ ጠፊዎች ተጠቃ!

አልሸባብ 10 ወታደሮች ገደልኩ ብሏል

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2004 ዓ.ም. January 25, 2012)፦ በደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር ጠቅላይ ሰፈር ላይ የአልሸባብ አጥፍቶ ጠፊ በሚኒባስ ሙሉ የታጨቁ ቦምቦች ማፈንዳቱ ተዘገበ። በጥቃቱ 10 የኢትዮጵያ ወታደሮች መግደሉን አልሸባብ ገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአፋር ክልል ለታገቱት ጀርመናዊያን አርዱፍ ኃላፊነት ወሰደ

‘5ቱ ጎብኝዎች የሞቱት በኢትዮጵያ መንግስት ጥይት ነው’ አርዱፍ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 14 ቀን 2004 ዓ.ም. January 23, 2011)፦ ባለፈው ሳምንት ለ5 ጎብኝዎች ሞት ምክንያት ለሆነው እና ለ27 ጎብኝዎች ላይ ለተቃጣው ጥቃት በህወሀት መራሹ የኢትዮጵያ ወታደሮችና በአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር (አርዱፍ) መሀከል በተነሳ ጦርነት መሆኑንና ታጋቾቹ ሁለት ጀርመናዊያን በእጁ እንደሚገኙ አርዱፍ አስታወቀ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከጓድ መንግስቱ ኃይለማርያም ‹‹ትግላችን›› ጋር…

ተመስገን ደሳለኝ

ማን ይፈራል ሞት

ማን ይፈራል

ለእናት ሀገር ሲባል..

የጊዜው ወታደራዊ ደርግ አስተዳደር፣ የአብዮታዊ ጦር ሰራዊት ጠቅላይ አዛዥ፣ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ ዋና ፀሀፊ፣ የኢህዴሪ ሊቀመንበር፣ የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት… ጓድ መንግስቱ ኃ/ማርያም ሰሞኑን በስደት ከሚኖሩበት ዙምባቤ ‹‹ትግላችን›› የተሰኘ መጽሐፍ አሳትመው በ39 የአሜሪካ ዶላር እየቸበቸቡ ነው። በእርግጥ ሀገር ከመሸጥ መጽሐፍ መሸጥ የተሻለ ነበር። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአፋር ክልል የተገደሉት ጎብኝዎች ዜግነት ታወቀ

4 ሰዎች ታግተዋል፣ ሁለት ቆስለዋል

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 9 ቀን 2004 ዓ.ም. January 18, 2011)ትላንት ማክሰኞ ከጠዋቱ 5 ሰዓት ላይ  በአፋር ክልል ያልታወቁ ታጣቂዎች በወሰዱት ርምጃ የተገደሉት አምስት ጎብኝዎች ዜግነት መረጋገጡ እና አራት ሰዎች መታገታቸው ታወቀ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

70ሺህ ኢትዮጵያዊያን በግዳጅ ተፈናቀሉ

አስገድዶ መድፈርና ከፍተኛ የመብት ረገጣ ተፈጽሞባቸዋል

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 9 ቀን 2004 ዓ.ም. January 18, 2011)፦ በኢትዮጵያ ለም የሆኑ የእርሻ መሬቶችን ለኢንቨስትመንት ለመስጠት መንግስት በያዘው ፕሮግራም ሳቢያ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከሚኖሩባቸው አካባቢዎች በግዳጅ እየተነሱ ለኑሮ ተስማሚ ወዳልሆኑ ቦታዎች መወሰዳቸውን ሂዩማን ራይትስ ወች አጋልጧል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ወታደሮች ሁለት የሶማሌን ባለስልጣናትን ማሰራቸው ተገለጸ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 9 ቀን 2004 ዓ.ም. January 18, 2011)፦ ሁለቱ ባለስልጣናት የታሰሩት እሁድ ከሰዓት የሰላም ስምምነቱን ካፈረሱ በሁዋላ መሆኑን ሶማልላንድ ፕሬስ ዘግቡዋል። የታሰሩት ባለስልጣናት አደን አብድላሂ አወል የሱማሌ ክልል አኩ ሱና ፓርላማ ቡድን መሪ እና አብዱልፈታህ ሀሰን ጃማ የሸበሌ ቫሊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት መሆናቸው ታውቋል ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ባንኮች ተቀማጭ ገንዘባቸው በመቀነሱ ትርፋቸውም መቀነሱ ተገለጸ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 9 ቀን 2004 ዓ.ም. January 18, 2011)፦ ብሉምበርግ የአክሰስ ካፒታል ሼር ካምፓኒን ጠቅሶ እንደዘገበው በዚህ አመት የኢትዮጲያ ባንኮች ትርፋቸው እየቀነሰ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ህጉ አበዳሪዎች ከመንግስት የዋስትና ሰነድ (ሴኩሪቲ)እንዲገዙ ስለሚጠይቅ መሆኑን ገልጿል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአፋር ክልል አምስት የውጭ ሀገር ዜጎች በታጣቂዎች ተገደሉ

አቶ በረከት ኤርትራን ተጠያቂ አድርገዋል

ሁለት ጀርመናዊያን ተጠልፈዋል

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥር 8 ቀን 2004 ዓ.ም. January 17, 2012)፦ ባለፈው ሰኞ  ማምሻው ላይ በአፋር ክልል ይንቀሳቀሱ በነበሩ የጎብኝዎች ቡድን ላይ ማንነታቸው ያልተረጋገጠ ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ ቢያንስ 5 ሰዎች መሞታቸውና ሁለት ሌሎች ቱሪስቶች ደግሞ ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ታሳሪዎቹ ስዊድናዊያን ጋዜጠኞች ምህረት የማግኘት እድላቸው የመነመነ ነው ተባለ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ጥር 5 ቀን 2004 ዓ.ም. January 14, 2011)፦ ባለፈው አመት ጁን ወር ላይ በሶማሌ ክልል ከሚንቀሳቀሰው የኦብነግ ወታደሮች ጋር በጥይት ተመተው የተማረኩትና በፍትህ አጉዳይነቱ በሚታወቀው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ለ11 ዓመታት እስር ላይ እንዲቆዩ የተፈረደባቸውን ሁለቱን ስዊድናዊ ጋዜጠኞች በተመለከተ የዲፕሎማሲው ፍጥጫ ቀጥሏል። በምህረት የመፈታታቸው እድልም የመነመነ መሆኑ ተገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አላሙዲ በአሜሪካ ተለጣፊ የስፖርት ፌዴሬሽን አቋቋሙ

አዲሱ ፌዴሬሽን (ESFNA-ONE) ተብሏል

አቶ አብነት የስፖርት ክለቦችን ለመደለል ገንዘብ መበተን ጀምሯል

Ethiopia Zare (ሐሙስ ጥር 3 ቀን 2004 ዓ.ም. January 12, 2011)፦ የኢትዮጵያዊያን በሰሜን አሜሪካ ስፖረት ፌደሬሽን የሚያካሂደው አመታዊ የስፖርት ውድድር አመታዊ ዝግጅቱን በዳላስ ቴክሳስ እንደሚያካሂድ ይፋ ማድረጉ የሚታወቅ ሲሆን በሼህ መሀመድ አላሙዲ ወዳጅ አቶ አብነት የሚመራ አዲስ ፌደሬሽን ተቋቁሞ ሌላ የስፖርት ውድድር በዋሽንግተን ዲሲ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ መሆኑ ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ