በኢትዮጵያ ተማሪዎች የመብት ጥያቄዎችን አንስተው ተቃውሞ አሰሙ (ቨኦኤ)

በሔኖክ ሰማእግዜር ፈንቴ

የተማሪዎቹ ጥያቄዎች የተለያዩ መልክ ያላቸው ናቸው። ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ከተማ የትምህርት ነጻነታችንን የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ተጋፍቶናል ሲሉ በመቶዎች የተቆጠሩ የአወሊያ የመለስተኛ፣ ሁለተኛ ደረጃና ኮሌጅ ተማሪዎች ድምጻቸውን በማሰማት ላይ ናቸው።

 

ጥያቄዎቻችን ካልተመለሱ ወደቤታችን አንሄድም በሚል በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ዛሬ ሊያድሩ የወሰኑት ተማሪዎች፤ ቁጥራቸው ከ600 በላይ እንደሆነ ይናገራሉ። ለአንድ ሳምንትም ትምህርት ተቋርጧል።

 

“ምንም አይነት ችግር ሳይፈጠር ኮሌጁን የእልምና ጉዳዮች ዘግቶብናል፣ የኮሌጁ መምህራንና ዲኖች ከስራ ተሰናብተዋል፣ እንዲሁም የአወሊያ መስጊድ ኢማም የሆኑት ሼክ ይማም ተባረዋል” ስትል አንዲት ስሟ እንዳይጠቀስ የፈለገች የአረቢኛ ቋንቋ የኮሊጅ ተማሪ ገልጻለች።

 

የጸጥታ ሃይሎች የትምህርት ቤቱን ግቢ ከበዋል፤ እስካሁን ሰልፉን ለመበተን ከማስፈራራት በስተቀር በተማሪዎቹ ላይ የደረሰባቸው ጥቃት የለም።

 

በወለጋ ዩኒቨርስቲ ደግሞ ተማሪዎች የምግብ ጥራት መጓደል አሳስቧቸዋል፤ አልፎም ለተቃውሞ አድርሷቸዋል።

 

ከለት ወደለት የደፈረሰ የጎርፍ ውሃ የመሰለ ሽሮ መብላት ታከተን፤ በአግባቡ ያልተበጠረና አሸዋ ያለበት እንጀራ መብላት እስከመቼ? የሚመደብልን በጀት በቂ ሆኖ ሳለ፤ የምግብ ጥራት ማሽቆልቆሉ ለምን? እያሉ ውስጥ ውስጡን ሲያጉተመትሙ የነበሩት የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች፤ የገና ለት ነው አንጀታቸው ለይቶለት የተቆረጠው።

 

ከቤተሰባቸው ተለይተው በዓሉን የሚያከብሩት ተማሪዎች እልቅ ቅጠል የማይል ምግብ ቀረበልን ሲሉ፤ ምግብ ላለምብላት ይወስኑና፤ በምግብ ቤቱ ዙሪያ ይሰባሰባሉ።

 

ተማሪዎቹ የምግብ ጥራት እንዲሻሻል ሲጠይቁ የመጀመሪያቸው አልነበረም። ወዲያውኑ የጸጥታ ሃይሎች በአካባቢው ተገኝተው ተማሪዎቹ ጋር ግብ ግብ  ይገጥማሉ። የታጠቁ ሃሎች በከፈቱት ተኩስ አንድ ተማሪ መቁሰሉንና ሌሎች ደግሞ መደብደባቸውን ተማሪዎቹ ይናገራሉ።

 

ጥቃት ከደረሰባቸው አንዱ በአሁኑ ወቅት የቀዶ ጥገና ህክምና ተደርጎለት በነቀምት ሆስቲታል ውስጥ ይገኛል። የፌዴራልና የኦሮሚያ ፖሊስ በአካባቢው ተገኝተው በወሰዷቸው እርምጃዎች ድብደባ ደርሶባቸው በሆስፖታል የሚገኙ ተማሪዎች እንዳሉም ተገልጿል።

 

የሶስተኛ አመት ተማሪ ተስፋየ ደገፋ በአካዳሚክ ፕሬዝደንቱ ዶር ኤባ ሚጀና ስለተደበደብ ለህይወቱ አስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገን ተማሪዎቹ ለኦሮሚኛ ዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል።

 

የተማሪው የጤና ሁኔታ አስጊ በመሆኑ ለተጨማሪ የህክምና እርዳታ ወደ አዲስ አበባ ከአቅም በላይ ተብሎ ሊላክ እንደታሰበ ተማሪዎቹ ይናገራሉ። በወለጋ ዩኒቨርስቲ የትምህርት ሂደቱ በከፊል ቀጥሏል። የዩኒቨርስቲውን ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ፈቃዱ በየነ የዝግጅት ክፍላችን በተደጋጋሚ ደውሎላቸው ስልካቸውን አያነሱም።

 

የምስራቅ ወለጋ የፖሊስ ኮሚሽነር ኢንስፔክተር ኦላና ጌታቸው የተጎዱ የሚባሉት ተማሪዎች ማን እንደደበደባቸውና ጥቃቱን እያደረሰባቸው እንደሆነ አልታወቀም ብለዋል። እስካሁን የታሰሩ ተማሪዎች አለመኖራቸውን ነው ኢንስፔክተር ኦላና የገልጹት።

 

በደቡብ ክልል ሃዲያ ዞን ደግሞ፤ በሆሳእና ከተማና አካባቢዋ የሚገኙ ከ429 በላይ ተማሪዎች ትምህርታችንን አጠናቀን ስራ አጥተናል በሚል የዞኑ መስተዳድር የስራ እድል እንዲከፍትላቸው ጠይቀዋል።

 

ተማሪዎቹ ተወካዮች መርጠው ከመስተዳድሩ ጋር ለረጅም ጊዜ ሲደራደሩና ሁኔታውን ሲከታተሉ መቆየታቸውን ነው የሚናገሩት። በስተመጨረሻ ተወካዮቻቸው ከዞኑ መስተዳድር ጋር ለመነጋገር ገብተው ባለመመለሳቸው ተቃውሞው መባባሱን አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ተማሪ ገልጾልናል።

 

የሃዲያ ዞን የፖሲስ አዛዥ ኮማንደር አዲሴ ፈይሳ ግጭቱ መፈጠሩን ገልጸው፤ ከታሰሩ ተማሪዎች መካከል ሁሉም ትምህርት ተሰጥቷቸው መፈታታቸውን ተናግረዋል።

በኦነግ አዲስ አቋም ዙሪያ ውዝግቡ ቀጥሏል

“በኦነግ ውስጥ የተፈጠረው ችግር ምክንያት የጠራ ራእይ ማጣት ነበር” የኦነግ ከፍተኛ አመራር

Ethiopia Zare (ሐሙስ ታህሳስ 26 ቀን 2004 ዓ.ም. January 5, 2011) በፈረንጆችቹ አዲስ አመት መግቢያ የኦሮሞ ተወላጆች በብዛት ይኖሩባታል በምትባለው ሜኔሶታ ክፍለ ከተማ በተጠራ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ይፋ የሆነውና ኦነግ (የኦሮሞ ነጻነት ግንባር) ከተመሰረተበት ከ1960 እኤአ ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያን አንድነት የተቀበለበትን መግለጫ ካወጣ ጀምሮ የተለያዩ አስተያየቶች በመሰማት ላይ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የእስክንድር ነጋ አክስትም ተገኝተው ነበር

በዋሽንግተን ዲሲ ወርሀዊ የሻማ መብራት ስነስርአት ተካሄደ!

Ethiopia Zare (ሰኞ ታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓ.ም. January 2, 2011)፦ በ”ማርች ፎር ፍሪደም”ና በሌሎች የሰብአዊ መብት ድርጅቶች አስተባባሪነት በየወሩ በአሜሪካን ፕሬዚዳንት መኖሪያ ፊት ለፊት የሚካሄደውና በኢትዮጵያ የታሰሩ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞችን የሚያስበው የሻማ ማብራት ስነስርአት በሞቀ ሁኔታ ተካሄደ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የቅዱስ ገብርኤልን በዓል በዲሲ አከበሩ

የመኖሪያቸውና ጽህፈት ቤታቸው ግንባታ እየተጠናቀቀ ነው!

የበአሉ እለት፡ በቤተመቅደስ ውስጥ መለስተኛ ረብሻ ተነስቶ ነበር!

Ethiopia Zare (ሰኞ ታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓ.ም. January 2, 2011)፦ በውጭ ሀገር በስደት ላይ የሚገኘውና ህጋዊው ሲኖዶስ ብጹዕ ወቅዱስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ አቡነ መርቆሪዮስ መቀመጫቸውን በአሜሪካዋ መናገሻ ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ እንደሚያደርጉ እና ጽህፈት ቤታቸውና የመኖሪያ ቤታቸው ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በደሴ ከተማ 11 ቤቶች ተቃጠሉ

ሕዝብ እና ፌደራል ፖሊስ ተፋጠዋል

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ታህሳስ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. December 27, 2011)በደሴ ከተማ ልዩ ስሙ አራዳ ገበያ በመባል የሚታወቀው ቦታ 11 ቤቶች ተቃጥለው ነዋሪዎች በድጋሚ በእሳት የጋዩ ቤቶቻቸውን ለመስራት  ሲሞክሩ በስፍራው የደረሱ የፌደራል ፖሊሶች ቤቶቹ እንዳይሰሩ በመከልከላቸው ምክንያት  ህዝብና የፌደራል ፖሊስ መፋጠጣቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ጠቆመ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፍርድ ቤት ድራማ በተደናገጡና በተምታቱ ምስክሮች ለቅሶ ተገባደደ፤ ዛሬም ይቀጥላል

ምንጭ፦ አዲስ ነገር

ማክሰኞ ታህሳስ 10 ቀን 2004 ዓ.ም ፡- የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በሽብርተኝነት ወንጀል በከሰሳቸው 24 የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት፣ የመብት ተሟጋቾችና ጋዜጠኞች ላይ በኢቲቪ አኬልዳማ ዶኩመንተሪ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ሰዎችን በዋና ምስክርነት አቀረበ። ብዙዎቹ መስካሪዎች በጭንቀትና በመርበትበት ሲናገሩ፣ አንዳንዶቹም ሲያለቅሱ ነበር። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኮ/ል መንግስቱ “ትግላችን” መጽሐፍ በገበያ ላይ ይውላል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ታህሳስ 7 ቀን 2004 ዓ.ም. December 17, 2011)፦ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት እና በአሁኑ ሰዓት በስደት ዚምባቡዌ የሚገኙት፤ በመጥፎነታቸው የሚታወቁት የኮ/ል መንግስቱ ኃይለማሪያም ባለ ሶስት ቅጽ መጽሐፍ የመጀመሪያው ክፍል በሚቀጥለው ሳምንት በገበያ ላይ ሊውል ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአዲስ አበባ የፌደራል ፖሊስ ጥበቃ ተጠናክሯል

የውጭ ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያዊያን በየቤታቸው ይፈተሻሉ

Ethiopia Zare (አርብ ህዳር 29 ቀን 2004 ዓ.ም. December 9, 2011) በመናገሻዋ አዲስ አበባ በየትላልቅ ፎቆችና ዋና ዋና መንገዶች ዙሪያ የፌደራል ፖሊስ በመባል የሚታወቁት ተወርዋሪ የጥበቃ ኃይሎችና የደህንነት አባላት ሩጫ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ መታየታየቱ ተገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኦባንግ ሜቶ ኦታዋ ገባ፡ በኮንጎዎች የተቃውሞ ሰልፍ ላይም ተሳተፈ

“የኦታዋና ቶሮንቶ ኢትዮጵያዊያንን እንቅስቃሴ ያሳድጋል” ተብሎ ተስፋ ተደርጓል

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ህዳር 28 ቀን 2004 ዓ.ም. December 8, 2011)፦ የጋራ ንቅናቄ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ በእንግሊዘኛው Solidarity Movement for New Ethiopia የተባለው የተባለው መቀመቻው በሰሜን አሜሪካ የሆነ የኢትዮጵያዊአን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት መስራችና ስራ አስኪአጅ አቶ ኦባንግ ሜቶ፡ ቀድሞ ይኖርበት ከነበረው ሳስካቱን ከተማ ወደ ካናዳ ዋና ከተማ ኦታዋ በዚህ በያዝነው ሳምንት መዛወሩ ታወቀ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በካናዳ ዋና ከተማ፡ ኦታዋ፡ የኔሰው ገብሬ በሻማ ማብራት ስነስርአት ታሰበ

አያሌ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና የፖለቲካ ድርጅቶች አባላት ተገኝተው ነበር

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ህዳር 26 ቀን 2004 ዓ.ም. December 6, 2011)፦ ከማል አቡበከር ይባላል። የአገሩ ጉዳይ የሚያንገበግበው ጎልማሳ ነው። በእለቱ የቤቱን እቃ ለማጓጓዝ የጭነት መኪና ለስድስት ሰዓት ያህል ቢከራይም፡ የየኔሰው ገብሬ መታሰቢያ እንደሚደረግ ስነግረው፡ መኪናውን ከመንገድ ጥግ አቁሞ ወደ ካናዳ ፓርላማ ለመጓዝ ሰከንድም አልፈጀበትም። “አረ ትኬት እንዳይሰጡህ” ቢባልም “እንኩዋን ትኬት መስጠት፡ ጎትተውም ይውሰዱት ከፈለጉ” ብሎ ወደ ሻማ ማብራቱ አቀና። እሁድ፡ ዲሴምበር 4፡ 2011 ዓ.ም፡ ከሰኣት በኋላ። ሙሉውን አስነብበኝ ...