የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አባት ጨምሮ ሦስት ተከሳሾች መከላከያ አቀረቡ

ፍርድ ቤቱ የአቶ ጌቱ ወርቁን የቪዲዮ ማስረጃ አልቀበልም አለ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ነሐሴ 19 ቀን 2001 ዓ.ም. August 25, 2009)፦ ከግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጋር በተያያዘ ከተከሰሱት ግለሰቦች ውስጥ የንቅናቄው መስራች የሆኑት የአቶ አንዳርጋቸው አባት፣ አቶ ጽጌ ኃብተማርያምን ጨምሮ ሦስት ተከሳሾች ዛሬ የመከላከያ ምስክሮቻቸውንና የሰነድ ማስረጃዎቻቸውን ለፍርድ ቤቱ አቀረቡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኦፌዲን በምርጫ 2002 የመሣተፍ ተስፋችን ደብዝዟል አለ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ነሐሴ 19 ቀን 2001 ዓ.ም. August 25, 2009)፦ የመንግሥት የደህንነት ሰዎች፣ ካድሬዎችና የወረዳ ቀበሌ ሹማምንቶች፤ በአባላትና በደጋፊዎቻቸው ላይ ያልተቋረጠ የማወዋከብ ድርጊት እየፈጸሙ መሆኑን የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዲን) አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመንግሥት ሠራተኞች የጣት አሻራ እየሰጡ ነው

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ነሐሴ 19 ቀን 2001 ዓ.ም. August 25, 2009)፦ የደምወዝ ታክስ የሚቆረጥባቸው የመንግሥት ሠራተኞች፤ በአዲስ መልክ የተጀመረው የታክስ መክፈያ ማረጋገጫ የጣት አሻራ መስጠት ጉዳይ የደህንነት ሥጋት እየፈጠረባቸው መሆኑን ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አትሌት ገለቴ ተገፍትራ በመውደቋ ሜዳሊያ አጣች

ገፍታሪዋ የወርቅ ሜዳሊያውን ተነጠቀች

Gelete Burka (C) of Ethiopia is helped by medical staff after crossing the finish line last following a fall in the women's 1500 meters final during the world athletics championships at the Olympic stadium in Berlin, August 23, 2009.

Ethiopia Zare (እሁድ ነሐሴ 17 ቀን 2001 ዓ.ም. August 23, 2009)፦ በሴቶች 1500 ሜትር ርቀት ውድድሩን እስከ 1200 ሜትር ስትመራ የነበረችው አትሌት ገለቴ ቡርቃ በስፔይኗ አትሌት ናታሊያ ሮድሪከዝ ተገፍትራ መሬት ላይ በመውደቅዋ ውድድሩን ሳታሸንፍ ቀርታለች። ናታሊያ ውድድሩን በአንደኝነት ብትጨርስም ዳኖቹ አሸናፊነትዋን ውድቅ በማድረግ የወርቅ ሜዳሊያውን እንዳታገኝ አድርገዋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ታሪክ ሠራ

በዓለም ሻምፒዮና በ10000 እና በ5 ሺህ በማሸነፍ ለዓለም የመጀመሪያው አትሌት ሆነ

(ተጨማሪ ፎቶግራፎች የታከለበት)

BERLIN: Kenenisa Bekele of Ethiopia celebrates winning the gold medal in the men's 5000 Metres Final during day nine of the 12th IAAF World Athletics Championships at the Olympic Stadium on August 23, 2009 in Berlin, Germany.

Ethiopia Zare (እሁድ ነሐሴ 17 ቀን 2001 ዓ.ም. August 23, 2009)፦ ኮከቡ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በበርሊኑ 12ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ5000 ሜትር አንደኛ በመውጣት ለራሱም ለሀገሩም ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝቷል። በሻምፒዮናው በአስር ሺህ እና በአምስት ሺህ ወርቅ በማግኘት በዓለም ቀዳሚው አትሌት ሆኗል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አሰለፈች መርጊያ በማራቶን ሦስተኛ ወጣች

Aselefech Mergia of Ethopia crosses the finish in third place in the women's marathon at the 12th world athletics championships in central Berlin August 23, 2009.
 

Ethiopia Zare (እሁድ ነሐሴ 17 ቀን 2001 ዓ.ም. August 23, 2009)፦ ዛሬ እሁድ ነሐሴ 17 ቀን 2001 ዓ.ም. በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን በተደረገው የሴቶች ማራቶን ከተሳተፉት አምስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውስጥ አሰለፈች መርጊያ ሦስተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ 4ኛውን የነኀስ ሜዳሊያ አስገኝታለች። ሙሉውን አስነብበኝ ...

መሰረት ደፋርና ፀጋዬ ከበደ የነኀስ ሜዳሊያዎች አስገኙ

ኬንያውያን አትሌቶች ኢትዮጵያውያኑን በልጠው ተገኝተዋል

Meseret Defar, Berlin 22 Aug 2009, Bronz medal (AP)

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ነሐሴ 16 ቀን 2001 ዓ.ም. August 22, 2009)፦ በዛሬው ዕለት (ቅዳሜ ነሐሴ 16) ስምንተኛ ቀኑን በያዘው በበርሊኑ 12ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶች ማራቶን 3ኛ፣ 4ኛ እና 15ኛ ሲወጡ፣ በሴቶች 5000 ሜትር ደግሞ 3ኛ፣ 4ኛ እና 5ኛ ወጥተዋል። የዛሬውን ሁለት የነኀስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ያስገኙት አትሌት ፀጋዬ ከበደ በማራቶን፣ አትሌት መሰረት ደፋር ደግሞ በ5000 ሜትር ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ13 ዓመቱ የአቦይ ስብሃት ልጅ በመኪና ሰው ገጨ

‘ሌላው በአንድ ዓመቱ ታስሮ እየወጣ ልጄን አታስጨንቁት’ ወላጅ እናቱ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ነሐሴ 16 ቀን 2001 ዓ.ም. August 22, 2009)፦ የህወሓት መስራችና በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውሰጥ ያለው አገዛዝ አውራ ናቸው የሚባሉት የአቦይ ስብሃት ነጋ የ13 ዓመት ታዳጊ ወጣት ልጅ ነሐሴ 10 ቀን 2001 ዓ.ም. ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ አዲስ አበባ ውስጥ ሁለት ሰዎችን በመኪና ገጭቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የረመዳን ፆም ዛሬ ተጀመረ

Ethiopia Zare (ዓርብ ነሐሴ 15 ቀን 2001 ዓ.ም. August 21, 2009)፦ በኢትዮጵያ የእስልምና ዕምነት ተከታዮች የረመዳንን ፆም ዛሬ ዓርብ ነሐሴ 15 ቀን 2001 ዓ.ም. ጀምረዋል። የአውሮፓ ሙስሊሞችም እንዲሁ በዛሬ ዕለት ፆሙን የሚጀምሩ ሲሆን፣ የሰሜን አሜሪካ ሙስሊሞች ደግሞ ነገ ቅዳሜ ነሐሴ 16 ቀን እንደሚጀምሩ ታውቋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...