መድረክ ስብሰባውን ረግጦ ወጣ

Dr. Merera and Prof. BeyeneEthiopia Zare (ኀሙስ ነሐሴ 28 ቀን 2001 ዓ.ም. September 3, 2009)፦ በእንግሊዝ ኤምባሲ አግባቢነት መጪውን የ2002 ዓ.ም. የሀገር አቀፍ ምርጫን አስመልክቶ በተቃዋሚዎችና በገዥው ፓርቲ መካከል የተጀመረውን ስብሰባ መድረክ (መድረክ ለዲሞክራሲያዊ ምክክር በኢትዮጵያ) ዛሬ (ኀሙስ ነሐሴ 28 ቀን 2001 ዓ.ም.) ረግጦ ወጣ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢ.ቴ.ቪ ጋዜጠኞችና የአንድነት ደጋፊዎች በሐዋሳ ተጋጩ

Ethiopia Zare (ኀሙስ ነሐሴ 28 ቀን 2001 ዓ.ም. September 3, 2009)፦ ባለፈው እሑድ ነሐሴ 24 ቀን 2001 ዓ.ም. በሐዋሳ ከተማ አንድነት ፓርቲ ህዝባዊ ስብሰባውን ያካሄደ ሲሆን፣ በቦታው የተገኙ የኢ.ቴ.ቪ. ጋዜጠኞችና የፓርቲው ደጋፊዎች ጋር ግጭት ፈጥረው ስብሰባውን ሳይቀርጹ መመለሳቸውን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአተት ምክንያት ምግብ ቤቶች እየታሸጉ ነው

Ethiopia Zare (ኀሙስ ነሐሴ 28 ቀን 2001 ዓ.ም. September 3, 2009)፦ በሀገሪቱ ውስጥ በቅርቡ የተከሰተውን የአጣዳፊ ተቅማጥና ተውከት (አተተ) በሽታ ለመከላከል በሚል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በአንዳንድ አገልግሎት ሰጪ የአዲስ አበባ ሆቴሎችንና ምግብ ቤቶችን በማሸግ ላይ መሆኑ ተገለፀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአንድነት መሪ ወ/ት ብርቱካን የዓመቱ ድንቅ ሰው ተብላ ተሸላሚ ሆነች

Ethiopia Zare (ረቡዕ ነሐሴ 27 ቀን 2001 ዓ.ም. September 2, 2009)፦ የሕግ የበላይነትን፣ ዲሞክራሲንና ነፃነትን በግል ሕይወቷ ላይ ተግባራዊ ያደረገችው የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት የፖለቲካ ፓርቲ መሪ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የ2001 ዓ.ም. የዓመቱ ድንቅ ሰው ሽልማት አሸናፊ ሆነች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጅምላ ግድያ፣ ዝርፊያና የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በፈጸሙ ሰዎች ላይ ውሳኔ ሊሰጥ ነው

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ነሐሴ 26 ቀን 2001 ዓ.ም. September 1, 2009)፦ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 2ኛ የወንጀል ችሎት፤ ከአንድ ዓመት በፊት በምሥራቅ ወለጋ በሚገኙ ሦስት የቤኒሻንጉል ጉምዝ “ክልል” አዋሳኝ ሥፍራዎች “የግድያ፣ የዝርፊያ፣ የአስገድዶ መድፈርና የንብረት ማውደም ወንጀል ፈጽመዋል” ባላቸው 101 ተከሳሾች ላይ የመጨረሻ የቅጣት ውሳኔ ለማስተላለፍ ለነሐሴ 27 ቀን 2001 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢህአዲግ ከተቃዋሚዎች ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ነሐሴ 23 ቀን 2001 ዓ.ም. August 29, 2009)፦ በመጪው ሰኞ ነሐሴ 25 ቀን 2001 ዓ.ም. የኢትዮጵያው ገዢ ፓርቲ (ህወሓት/ኢህአዲግ) በሀገር ውስጥ አሉ ከሚባሉት “ዋንኛ” የሚባሉ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ጋር ውይይት እንደሚያካሂድ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቀነኒሳ በቀለ አምስተኛውን የጎልደን ሊግ ወርቅ አገኘ

Kenenisa Bekele sets a World Leading 5000m time of 12:52.32 in Zurich. (Getty Images)የአንድ ሚሊዮን ዶላሩን ጃክ ፖት ለመቋደስ አንድ ውድድር ይቀረዋል

Ethiopia Zare (ዓርብ ነሐሴ 22 ቀን 2001 ዓ.ም. August 28, 2009)፦ በዛሬው ዕለት ማምሻውን በስዊዘርላንድ ዙሪክ ከተማ በተደረገው የ2009ኙ የጎልደን ሊግ 5ኛ ዙር ውድድር ላይ ቀነኒሳ በቀለ በ5000 ሜትር አንደኛ በመሆን ውድድሩን አሸነፈ። የአንድ ሚሊዮን ዶላሩን ጃክ ፖት ለመቋደስ ከቀሩት ሦስት አትሌቶች ውስጥ አንዱ ሆኗል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያዊ ካናዳዊያን ዜጎች ሊግ የዋሽንግተኑን ሰለፍ ደገፎ መግለጫ አወጣ

Ethiopia Zare (ዓርብ ነሐሴ 22 ቀን 2001 ዓ.ም. August 28, 2009)፦ ኢ.ካ.ዜ.ሊ. በመባል የሚታወቀውና መቀመጫውን ካልጋሪ - ካናዳ ያደረገው ኢትዮጵያዊ ካናዳዊያንን አሰባስቦ የሚንቀሳቀሰው ሊግ በኢትዮጵያና በአፍሪካ የሰፈነውን አምባገነንነትንና ዘር ማጥፋትን ለማስቆም በእ.ኤ.አ. መስከረም 13 ቀን ለሚደረገው ሰልፍ ድጋፍ በመስጠት መግለጫ አወጣ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለመጀመሪያ ጊዜ ታላላቅ ሠዓሊያን ሥራዎቻቸውን ሊያቀረቡ ነው

Ethiopia Zare (ሐሙስ ነሐሴ 21 ቀን 2001 ዓ.ም. August 27, 2009)፦ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላቸው የተከበሩ ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌን ጨምሮ ታላላቅ ሠዓሊያን በዘመነ ኢህአዲግ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ላይ ኤግዚቢሽን ሊያቀርቡ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...