ቴዲ ለሚቀጥሉት 75 ቀናት ቃሊቲ ይቆያል
- ክሱን ተከላከል ተባለ
- ወዳጅ ዘመዶቹ በእንባ ተራጭተዋል
Ethiopia Zare (ሰኞ ሐምሌ 14 ቀን 2000 ዓ.ም. July 21, 2008)፦ አዲስ አበባ በፍተኛ ዝናብ ተውጣለች። ዝናቡን ከምንም ያልቆጠሩ የቴዲ አፍሮ ቤተሰቦች፣ ጓደኞችና አድናቂዎቹ በከፍተኛው ፍርድ ቤት መግቢያ በር ላይ በተለመደው ሁኔታ ሰልፍ ይዘዋል። ከላይ ስለሚወርድባቸው ዝናብ አንድም ያዘነ ፖሊስ አለነበረም። “ምናለበት ውስጥ ገብተን ብንጠብቅ?” የሚለው ጥያቄም መልስ አላገኘም። በተለመደው ሰዓት ከጠዋቱ 2፡45 ሲሆን፣ ወደ ግቢው እንድንገባ ተፈቀደ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...





