አና ጐሜዝ የአውሮፓ ሕብረት መሪዎችን ወቀሱ

Anna GomezEthiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 11 ቀን 2000 ዓ.ም. July 18, 2008)፦ የአውሮፓ ፓርላማ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አባልና ዲፕሎማት የሆኑት ሚስ አና ጐሜዝ የአውሮፓ ሕብረት መሪዎች በቡድን 8 ሀገሮች ጉባዔ ላይ በሰብዓዊ መብት ረገጣ ከሚወቀሱ የአፍሪካ መሪዎች ጋር መሆን ለሰብዓዊ መብት ጥበቃ ያላቸው አመለካከት ዝቅተኛ ነው በማለት ወቀሱ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድነት ፓርቲ ስሙን ተከለከለ

Ethiopia Zare (ኀሙስ ሐምሌ 10 ቀን 2000 ዓ.ም. July 17, 2008)፦ “አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ” በሚል ስያሜ ፓርቲ ለማቋቋም ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዶና አስፈላጊውን ማስረጃዎችና ፎርማሊቲዎች አሟልተው ባለፈው ሣምንት ረቡዕ ለምርጫ ቦርድ ፈቃድ መጠየቂያ ማመልከቻውን ያስገቡትና መሥራቾቹ “አንድነት” የሚለውን ስም መጠቀም እንደማይችሉ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት መግለጹን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮቻችን ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መልካም ልደት ለቴዲ አፍሮ!

Teddy Afroቴዲ "ቅማል በላኝ" በማለቱ 32ኛ ዓመቱን በጨለማ ቤት አከበረ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 8 ቀን 2000 ዓ.ም. July 15, 2008)፦ ቴዲ አፍሮ ባለፈው ዓርብ ሐምሌ 4 ቀን 2000 ዓ.ም. በዋለው ችሎት "… እኔ አንድም ሰው አልገደልኩም ሰውም አልገጨሁም። ነገር ግን በማላውቀው ነገር ሰብዓዊ መብቴ ተገፍፎ ቅማል እየበላኝ ሦስት ወር ታስሬያለሁ። …" ብሎ በመናገሩ ምክንያት ወደ ጨለማ ቤት መወርወሩንና የልደት በዓሉን ትላንት በጨለማ ቤት ማክበሩን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድነት ፓርቲ ማመልከቻውን ለምርጫ ቦርድ አስገባ

Ethiopia Zare (እሁድ ሐምሌ 6 ቀን 2000 ዓ.ም. July 13, 2008)፦ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሰኔ 11 ቀን 2000 ዓ.ም. ጠቅላላ ጉባዔውን ጠርቶ የላዕላይ ምክር ቤቱንና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴውን የመረጠ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ባሳለፍነው ሣምንት ረቡዕ ሐምሌ 2 ቀን 2000 ዓ.ም. ፓርቲውን ለማስመዝገብ ማመልከቻውን ለምርጫ ቦርድ ማስገባቱን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአውሮጳ የኢትዮጵያዊያን የስፖርት ውድድርና የባህል ፌስቲቫል በስዊድን ይካሄዳል

መንግሥቱ ወርቁ በክብር እንግድነት ይገኛል

Ethiopia Zare (እሁድ ሐምሌ 6 ቀን 2000 ዓ.ም. July 13, 2008)፦ ስድስተኛው የአውሮጳ የኢትዮጵያዊያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ሐምሌ 25 እና 26 (August 1 እና 2) በስዊድን ርዕሰ ከተማ ስቶክሆልም እንደሚከናወን የውድድሩ አዘጋጅ ማኅበር ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለፀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እነኮ/ል መንግሥቱ በእስር እንዲቀጡ የወሰኑት ዳኛ “አሸባሪዎችን በዋስ ለቀዋል” ተብለው ከሥራ ታገዱ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሐምሌ 5 ቀን 2000 ዓ.ም. July 12, 2008)፦ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሦስት ዳኞች፣ ይሰሩበት ከነበረው የድሬደዋ ከተማ ፍርድ ቤት ጅጅጋ ከተማ ባስቻሉት ተዘዋዋሪ ችሎት በአሸባሪነት ተጠርጥረው ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ የተደረጉ 28 ተጠርጣሪዎችን የዋስ መብት ፈቅደዋል የሚል የዲሲፕሊን ክስ ቀረበባቸው። ክሱ የደረሰው የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጉዳዩ እልባት እስኪያገኝ ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ የእግድ ትዕዛዝ በአንዱ ዳኛ ላይ አሳልፏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባና ስለሺ ስኅነ በሮሙ ጎልደን ሊግ በአንደኝነት አጠናቀቁ

Athlete Tirunesh Dibaba(ተጨማሪ ዘገባ የታከለበት)

Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 4 ቀን 2000 ዓ.ም. July 11, 2008)፦ ዛሬ (ሐምሌ 4 ቀን 2000 ዓ.ም. July 11, 2008) ማምሻውን በጣሊያን ዋና ከተማ ሮም ላይ በተካሄደው የጎልደን ሊግ ዓለም አቀፍ አትሌቲክስ የ5,000 ሜትር ውድድር በሴቶች የ22 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ፣ በወንዶች ደግሞ አትሌት ስለሺ ስኅነ በአንደኝነት አጠናቀቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቴዲ አፍሮ በድጋሚ ለብይን ተቀጠረ

- የምኒልክ ሆስፒታል ኩባዊ አስክሬን መርማሪ ፍርድ ቤት በሰነዱ ላይ ምስክርነት ሰጡ

- ቴዲ አፍሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ምሬቱን ለፍርድ ቤቱ ገለፀ

- ቴዲ ሲናገር እናቱን ጨምሮ ሰዎች አለቀሱ

Teddy Afro

Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 4 ቀን 2000 ዓ.ም. July 11, 2008)፦ በህዝብ ዘንድ ታዋቂና ተወዳጅ የሆነው አርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) በቀረበበት ክስ ላይ ሁለት ዓይነት ቀን ያለው የሰነድ ማስረጃ ሰጥቷል የተባለው የዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል ባለሙያ ፍርድ ቤት ቀርቦ እንዲያስረዳ በታዘዘው መሰረት የኩባ ዜግነት ያላቸው የአስክሬን መርማሪ ፍ/ቤት ቀርበው የምስክርነት ቃል ሰጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በክዊን በርገር የተመገቡ 19 ሰዎች ታመሙ

Ethiopia Zare (ኀሙስ ሐምሌ 3 ቀን 2000 ዓ.ም. July 10, 2008)፦ ትናንት ማምሻውን ኦሎምፒያ አካባቢ በሚገኘው ”ክዊን በርገር” በተሰኘው ሐምበርገር ቤት በተበከለ ምግብ 19 ሰዎች መታመማቸውንና ወደ ሕክምና መሄዳቸውን ከአዲስ አበባ ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰው መረጃ ጠቆመ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

31 የቅንጅት እስረኞች ተለቀቁ

እነፕ/ር ኤፍሬም የፖለቲካ እስረኞችን አስፈቱ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 1 ቀን 2000 ዓ.ም. July 8, 2008) ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘ ኢህአዴግ ወደ እስር ከወረወራቸው በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ውስጥ በዛሬው ዕለት ሰላሳ አንዱ ይቅርታ ጠይቀው መፈታታቸውን ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ የደረሰው መረጃ ጠቆመ። እስረኞቹን ያስፈታው በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስኃቅ የሚመራው የሽማግሌዎች ቡድን እንደሆነ ለማወቅ ችለናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...