ከ1,700 በላይ የኦሮሚያ የመንግሥት ኃላፊዎችና ሠራተኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት

ኃላፊነታቸውን ባለመወጣትና በብጥብጡ ውስጥ በመሳተፍ የተጠረጠሩ ናቸው

ኢዛ (ማክሰኞ ነኀሴ ፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 11, 2020)፦ ከአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ በተከሰተው ኹከት ተሳትፎ ነበራቸው ተብለው የተጠረጠሩ ከ1,700 በላይ የመንግሥት ኃላፊዎችና ሠራተኞች ላይ እርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወላይታ ዞን ችግር አለ

Asefa Wodajo

የዞኑ አመራሮች እየታሰሩ ነው
በተፈጠረው አለመረጋጋት ሰዎች ሞተዋል

ኢዛ (ሰኞ ነኀሴ ፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 10, 2020)፦ በወላይታ ዞን በተፈጠረው አለመረጋጋትና ግርግር የሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና ለችግሩ መንሥኤ ናቸው የተባሉ የዞኑ አመራሮችና ሌሎች እጃቸው አሉባቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ መኾኑ ተሰማ። በቁጥጥር ከዋሉት ሰዎች ውስጥ አቶ አሰፋ ወዳጆ ይገኙበታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኦነግ መግለጫ ሰጠ

የኦነግ አመራሮች

ከሕወሓት ጋር ግንኙነት የለኝም አለ፣ የታሰሩ አባሎቼ ይፈቱልኝም ብሏል
አቶ ዳውዲ ኢብሳ መግለጫው ከእኔ እውቅና ውጭ ነው አለ

ኢዛ (ሰኞ ነኀሴ ፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 10, 2020)፦ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ታስረውብኛል ያላቸውን አመራሮችና ደጋፊዎቹ እንዲፈቱለት ሲጠይቅ፤ ከሕወሓትና ኦነግ ሸኔ ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም ብሏል። በመግለጫው አቶ ዳውድ ኢብሳ ያልተገኙ ሲሆን፤ ስለመግለጫው የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እነአቶ ጃዋር ዳኛ ይቀየርልን ሲሉ አቤት አሉ

Jawar Mohammed

በዕለቱ ይሰማሉ የተባሉ ምስክሮች ቃል ሳይሰማ ቀርቷል፤ ፍርድ ቤቱም በመጥሪያ እስኪጠሩ ማረሚያ ቤት ይቆዩ ብሏል

ኢዛ (ሰኞ ነኀሴ ፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 10, 2020)፦ ዛሬ ነኀሴ 4 ቀን 2012 ዓ.ም. በቀጠሮ ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ ጃዋር በዓቃቤ ሕግ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ማሰማት በጀመረበት ወቅት፤ እነአቶ ጃዋር ዳኛው ከመዝገባቸው ይነሳላቸው ዘንድ አቤቱታ በማቅረባቸው ምስክሮች ሳይሰማ ቀረ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በዝግ ስብሰባ ተቀምጠዋል

Prosperity Party

ወሳኝ የተባሉ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሏል

ኢዛ (ሰኞ ነኀሴ ፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 10, 2020)፦ የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ለሁለት ቀናት ያካሔደው ዝግ ስብሰባ መጠናቀቅ ማግሥት የአማራ ብልጽግና ፓርቲም በዝግ ስብሰባ እየተወያየ ይገኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ሕወሓት በድንበር አካባቢ ለጦርነት እየተዘጋጀ መኾኑን አመለከተ

Amhara Prosperity Party and TPLF

ምሽግና በክልል ደረጃ የሚያዝ የጦር መሣሪያዎችም ታይተዋል

ኢዛ (ረቡዕ ሐምሌ ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 5, 2020)፦ ሕወሓት ከአማራ ክልል ጋር በሚዋሰንባቸው ቦታዎች የትንኮሳ እንቅስቃሴ ውስጥ መግባቱ እንደሚታወቅና በክልል ደረጃ ሊያዙ የሚችሉ የጦር መሣሪያዎችን በመያዝ እየተንቀሳቀሰ መኾኑን የአማራ ብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ምርጫ ጉዳይ ውሳኔ ያሳልፋል ተባለ

TPLF

ክልሉ ምርጫውን የሚከለክለኝ የለም ብሏል

ኢዛ (ረቡዕ ሐምሌ ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 5, 2020)፦ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል ከሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ውጭ ምርጫን ለማድረግ የሚገፋበት ከኾነ በቅርቡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በመሰብሰብ ውሳኔ ሊያሳልፍ ይችላል ተብሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የትግራይ ክልል ለማስጠንቀቂያው ምላሽ ሰጠ

TPLF and Ethiopian Election 2020

ምርጫውን ለማድረግ የሚከለክለኝ የለም እያለ ነው

ኢዛ (ሰኞ ሐምሌ ፳፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 3, 2020)፦ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል ምርጫ ለማካሔድ የሚደረገው እንቅስቃሴ ሕገ መንግሥታዊ ባለመኾኑና ይህንን እንቅስቃሴ የክልሉ መንግሥት ካላቆመ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ላስጠነቀቀበት ደብዳቤ፤ የትግራይ ክልል ምላሽ ሰጠ። በሕወሓት የሚመራው የትግራይ ክልል መንግሥት፤ ምርጫውን ለማድረግ የሚከለክለኝ የለም እያለ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ2012 ዓ.ም. 47ኛ ሳምንት አንኳር ወሬዎች

Ethiopia Zare's weekly news digest, week 47th, 2012 Ethiopian calendar

የዓመቱ አርባ ሰባተኛ ሳምንት አንኳር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ክንውኖች

ኢዛ (ከሐምሌ 20 - 26 ቀን 2012 ዓ.ም.) ያሳለፍነው ሳምንት የተለያዩ ክዋኔዎች የታዩበት ነው። ከፖለቲካው አንፃር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች ጋር ያደረጉት ውይይት አንዱ ነው። በዚህ መድረክ መንግሥት ሕግ የማስከበር ሥራውን አጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸው ጐልቶ የሚጠቀስ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልልን አስጠነቀቀ

TPLF

በክልሉ ለማድረግ ያሰበውን ምርጫ በአስቸኳይ ያቁም ብሏል
የትግራይ ክልል እስካሁን ምላሽ አልሰጠም

ኢዛ (ዓርብ ሐምሌ ፳፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 31, 2020)፦ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ምርጫ ለማካሔድ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በአፋጣኝ የማያቆም ከኾነ በሕግ እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መኾኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስጠንቅቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ