የረቡዕ ግጥም ፬ኛ ዓመት፣ ቁ. ፫

ከወየበው ቅጠል
አንዱ እኔን ይመስላል
በጨመረ ቁጥር
እያንዳንዱ ቀናት
እያንዳንዱ ወራት
እያንዳንዱ ዓመታት
ከወየበው ቅጠል
ከሚረግፈው መሐል
ልቤ ድንግጥ አለ
አንዱ እኔን ይመስላል
ወለላዬ ከስዊድን (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)