የረቡዕ ግጥም ፬ኛ ዓመት፣ ቁ. ፲፪

በጁ ባይዝ እንኳን፣ ዘርፎ ይሠጥ ነበር እጅግ ብዙ ቅኔ
ዘርፎ ይሠጥ ነበር
የሀብት መለኪያው መስፈሪያው ገረመኝ
ሀብታሙን ድሀ አ'ርጎ ምስኪን ነው የሚለኝ
እሱ ድሀ አይደለም፤ ደሀ ኾኖ አልኖረም አውቃለሁኝ እኔ
በጁ ባይዝ እንኳን፣ ዘርፎ ይሠጥ ነበር እጅግ ብዙ ቅኔ
ወለላዬ ከስዊድን (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)