”በፈርስ የሚያጓጉር ከብት ብቻ ነው!” እና እስኪ መርዶ መቀበልን በቃ እንበል!

የግል አስተያየት፦ አያልሰው ደሴ፤ መስከረም ሁለት ሺህ አራት ዓ.ም.

ሰሞኑን የአቶ መለስ ዜናዊ አገዛዝ በሀገራችን ያለውን አስከፊና አስጊ ሁኔታ በመቃወም እና የህዝባችንን እሮሮ እንደሌለ መቁጠርም ሆነ በዝምታ ለመመልከት ኅሊናቸው ያልፈቀደላቸው እንደ አቶ አንዱዓለም አራጌና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን የመሰሉ ዜጎችን በተለመደ እብሪት ወደ እስር እንደወረወራቸው ይታወቃል።

 

ለዚህ የግፍ እርምጃ ሰለባ የሆኑት ወገኖች ገን በተለይ ከገዥዎቹ ድርጅታዊ ባህሪና የቆየ ታሪክ አኳያ የተያያዙት ሠላማዊ ትግል ይህን ሊያስከትል እንደሚችልም ሆነ ይህንን ዋጋ እንደሚጠይቅ ዘንግተውት አይደለም ድምፃቸውን ማሰማትና የኅሊናቸው ተገዥ መሆንን የመረጡት።

 

ኢትዮጵያውያን፣ በተለይም ከሀገር ውጭ የሚገኙና ድምፃቸውን በነፃነት ማሰማት የሚችሉ ወገኖች፣ በእነዚህ ዜጎች ላይ የተፈፀመውን ግፈኛና አፋኝ ድርጊት እየተቃወሙ፣ እያወገዙና የታሰሩት የኅሊና እስረኞች በአስቸኳይና ያለ ምንም ቅድመ-ሁኔታ እንዲፈቱ ”ዛሬ እኔም እስክንድር ነኝ! ዛሬ እኔም አንዱዓለም ነኝ!” ብለው በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው። አዎን! ማንኛውም ለፍትህ፣ ለሕግ የበላይነትና ለሰብዓዊ መብቶች መከበር የቆመ ሁሉ ይህንን መፈክር አንግቦ መንቀሳቀስ ይገባዋል። ... ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ