ማን ነው ሽብርተኛው? እስክንድር ነጋ ወይስ የወያኔው መንጋ?!
ቴድሮስ ኃይሌ - This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

”… ጎበዝ እንግዲህ ኢትዮጵያችን የምትገዛው ዛሬም ይህን በመሠለ ሣጥናዔላዊ ቡድን ነው። እናትን ገሎ፤ አባትን አስሮ፤ ብላቴናውን አቁስሎ፤ ታላቅ እህትን አሰድዶ፤ ቀሪ ሕጻናትን ያለ ተንከባካቢ የትም ሜዳ እንዲበተኑ የሚያደርግ አረመኔው የህወሓት ቡድን ከአሌቃይዳ የማይተናነስ ጨካኝ ዘረኛና ሽብርተኛ ቡድን መሆኑን ከላይ ከመግቢያ ላይ የቀረበው ዓለም የተስማማበት የሽብርተኝነት ትርጓሜ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸም ማናቸውም አይነት የሰቆቃ ተግባር የሚያደርግ ቡድንም ይሁን ግለሰብ ድርጊቱ ፈጻሚውን በሽብርተኝነት የሚያስጠይቅ አድራጎት ነው። ...”
In human history, terrorism is widely recognized as the world most famous enemy of mankind. As history itself will admit that terrorism is annihilation with far-reaching and destructive effects, it is the cruelest of crimes against humanity.
በታላቋ ሀገራችን ቅድስቲቱ ኢትዮጽያ ላለፉት 20 ዓመታት የተንሰራፋው ሠይጣናዊው ሽብርተኛውና ዘረኛው የትግራይ ነፃ አውጭ ነኝ ባዩ መልቲ የማፍያ ቡድን ጠባብ ዓላማውን ለማሳካት ፍቅርን በሰበኩ፤ አንድነትን በመከሩ፤ ስለ እኩሌነት በተናገሩ የዲሞክራሲ ታጋዮችና ሠላማዊ ዜጎች ላይ ማለቂያ የሌለው ስም በመለጠፍ በእንበለ ፍርድ በየአደባባዩ የረሸናቸው በየእስር ቤቱ ያጎራቸው ዜጎች ቁጥር ለመጥቀስ እስኪያዳግት ድረስ በግፍ ላይ ግፍ በበደል ላይ በደል ከመፈጸም ሊታቀብ ይቅርና ጭራሽ እየባሰበት ከመሄድ ሊገታው የሚችል ሁኔታ ባለመፈጠሩ የጭቆና የብረት ቀንበሩን በሕዝብ ላይ በመጫን ሀገሪቱን በፍጥነት ወደ ታላቅ እስር ቤትነት ለውጧታል።
የህወሓት ሠይጣናዊ ቡድን በአሁኑ ወቅት በሰሜን አፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ የተቀጣጠለው ሕዝባዊ አብዮት ወጋገን ለሀገራችን ጭቁን ሕዝብ አበረታችና አርኣያ ሆኖ ከስሩ እንዳይመነግለው ክፉኛ ከመስጋቱ የተነሳ ለዓለም መሣቂያ እስኪሆን ድረስ በሠላማዊ እንቅስቃሴያቸው፤ በአስተሳሰብ አድማሳቸው፤ በምሁራዊና በስነምግባራዊ ተክለሠውነታቸው በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ጭምር አክብሮት የተቸራቸውንና እውቅና ያላቸውን ጋዜጠኞችንና የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን አበው ”የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ” እንዳለ አሸባሪ ብሎ በመፈረጅ የጀመረው የዚህ ሰሞኑ የእስር ዘመቻ በሚሊዮን በሚቆጠር ሠራዊትና ነጭለባሽ የሚጠበቁት የአገዛዙ መሪዎች ብዕር ባነገቡ ንፁሐን የዲሞክራሲ ተሟጋቾች መርበድበዳቸውና ጥቂቶችን በማሰር አይቀሬውን ህዝባዊ አመጽ ለመቀልበስ የመሞከራቸው ሂደት የአረመኔ አገዛዛቸውን መቀበሪያ ጉድጓድ ከማራቅ ውጭ ከቶም ሊያስቀሩት የማይችሉት የቁጣ ማዕበል ሞገድ ተነስቶ ሳይጠራርጋቸው ከሰጠሙበት ድቅድቅ ዘረኛና ኋላቀር የጥፋት ጨለማ ወጥተው ራሳቸውንም ሆነ ሀገሪቱን ከመከራ ለመታደግ መልካም ዕድል ቢጠቀሙበት በእጃቸው ይገኛል። (ጋዲፊን ያየ በሕዝብ አይቀልድም)
የህወሓት መሪዎች አረመኔያዊ ተግባር በተሟላ መረጃ በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማትና በምዕራቡ መንግስታት የሚታወቅና መሪውን ጨምሮ በተወሰኑትም ላይ በሰው ዘር ፍጅት (GENOCIDE) ክስ የቀረበባቸው መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም! ከጋምቤላ እስከ አዋሳ፤ ከአሰቦት እስከ ጅጅጋ፤ ከአቢአዲ እስከ አደባባይ እየሱስ፤ ... እንዘርዝረው ቢባል ብዕርና ወረቀት የሚበቃው አይመስለኝም። 17 ዓመት በትግል ስም፣ 20 ዓመት በመንግስትነት ጥብቆ በተከተለው የሽብር አገዛዝ የስንት ንፁሐን ዜጎች ደም በከንቱ ፈሰሰ? በምርጫ 97 የሕዝብ ድምፅ መነጠቁ ሳያንስ ከሕጻን እስከ አረጋውያን የተካሄደው ሽብራዊና ፋሽስታዊ ጭፍጨፋ ከቶም የሚዘነጋ አይደለም እዚህ ላይ አንድ የትግል ጓዳችን ቤተሰብ ላይ የተፈጸመውን የህወሓትን አረመኔ ድርጊት ለማስታወስ እገደዳለሁ።
የመኢአድ/ቅንጅት የወጣቶች ም/ቤት አባል በነበረችው ጠንካራዋ ታጋይ ወጣት ዓለምዙሪያ ተሾመና አባቷ የአዲስ አበባ ክልል ም/ቤት ተወዳዳሪ የነበሩት አቶ ተሾመ በነበረው ሕጋዊ የምርጫ ሂደት ቅንጅትን ወክለው በማሸነፋቸውና የሕዝብን ድምፅ እንዲከበር በመጠየቃቸው ብቻ እኝህን ጨዋና በስነምግባራቸው በሁላችን ዘንድ አክብሮት የተቸራቸውን የሠላምና የዲሞክራሲ ታጋይ ከቤታቸው አፍኖ ሊወስዳቸው የመጣውን የህወሓት አረመኔ ወታደሮች የአቶ ተሾመ ባለቤትና ሕጻናት ልጆቻቸው በልመናና ተማጽኖ የአባወራው ታስሮ መሄድ በመጠየቃቸው ብቻ እኝህን ምንም የማያውቁ ግሳጼ እንኳን የሚበዛባቸውን ምስኪን የህጻናት እናት የአጋዚው ታጋይ በያዘው ክላሽ ደጋግሞ በመተኮስ ሴትዮይቱን አፍ ባልፈቱ ሕጻናት ልጆቻቸው ፊት ገድለው፤ ”እናቴን!” ብሎ ትንሽ ነብስ ያወቀው ተዳጊ በመጮሁ እሱን ደግሞ እግሩን ተኩሶ በማቁሰል የውጭ ወራሪ ጠላት እንደገደለ ምስኪኑን ቀን የጨለመባቸውን አቶ ተሾመን ወደ እስር ቤት ይዘው ሄዱ።
የህወሓቱ ነብሰ ገዳይ የሽብር ጓድ ባፈሰሰው የንጹህ ሰው ደም የበቀል ዛሩ አልረካምና የሟቿን አስከሬን ለምርመራ በሚል ዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል አስገብቶ የዲሞክራሲና የነፃነት ታጋይ ጓዳችን ዓለምዙሪያ ተሾመ እናቷን በክብር ለመቅበር የቀረበላት ምርጫ እናቷን የገደላቸው ቅንጅት ነው ብለሽ ፈርሚ የሚል ማስገደጃ ያቀርቡላታል። እርሷም በቆራጥነት ራሳችሁ ገላችኋት እንደገና በውሸት እናቴን አልገልም፤ እንደፈለጋችሁ አድርጉት በሚል አቋም ጸንታ ይህንንም ግፍ ለሕዝብ እንዲገለጽ ለሚዲያዎች አስተላልፋ ቀሪ ተንከባካቢ የሚያስፈልጋቸውን ሕጻናት ወንድምና እህቶቿን ትታ ሕይወቷን ለማትረፍ እርሷም ለስደት የተዳረገችበት ሁኔታ ከብዙዎቻችን የትግል አጋሮቿ ሕሊና የማይጠፋ አሰቃቂ ትዝታ ነው።
ጎበዝ እንግዲህ ኢትዮጵያችን የምትገዛው ዛሬም ይህን በመሠለ ሣጥናዔላዊ ቡድን ነው። እናትን ገሎ፤ አባትን አስሮ፤ ብላቴናውን አቁስሎ፤ ታላቅ እህትን አሰድዶ፤ ቀሪ ሕጻናትን ያለ ተንከባካቢ የትም ሜዳ እንዲበተኑ የሚያደርግ አረመኔው የህወሓት ቡድን ከአሌቃይዳ የማይተናነስ ጨካኝ ዘረኛና ሽብርተኛ ቡድን መሆኑን ከላይ ከመግቢያ ላይ የቀረበው ዓለም የተስማማበት የሽብርተኝነት ትርጓሜ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸም ማናቸውም አይነት የሰቆቃ ተግባር የሚያደርግ ቡድንም ይሁን ግለሰብ ድርጊቱ ፈጻሚውን በሽብርተኝነት የሚያስጠይቅ አድራጎት ነው።
አሮጊት ገዳይ፣ ሕጻን አቁሳይ፣ ቤተሰብ አፍራሽ የሆነው ሠው በላው የመለስ ቡድን እንዲህ ያለ የሽብር ተግባር ፈጻሚና ወንጀለኛ ሆኖ እያለ እንደ እስክንድር ነጋ ያለ እግዚያብሔርን የሚፈራ፣ ሠውን የሚያከብር፣ ለደሀ የሚራራ፣ ለጋስ፣ የዋሕ፣ ንጹህ፣ ሀገሩንና ወገኑን የሚወድ፣ የዲሞክራሲ ፋና ወጊ፣ ደፋርና በሠላማዊ ፖለቲካ ፍጹም የሚያምን ብዙ ግፍ የፈፀመበትን ቡድን እንኳ የማይጠላ የሠላም ሰው እንደሆነ የሚያውቀው ሁሉ የሚመሰክረው ሐቅ ነው። እንዲህ አይነቱን መልካም ዜጋ ሽብርተኛ ማለት በሕዝብ መሣለቅና በፍትሕ መቀለድ ነው።
ለማጠቃለል የወያኔ አገዛዝ በሀገር ቤት በቅርቡ ሃሳባቸውን በነፃነት ባንሸራሸሩት የአንድነትና የመድረክ የፖለቲካ መሪዎችና በጋዜጠኞች ላይ የወሰደው በግፍ የማሰር እርምጃ በመላው የሀገሪቱ ዜጎች ላይ የተቃጣ የእብሪትና አንባነናዊ እርምጃ በመሆኑ፤ በሀገርም ውስጥ ይሁን በውጭ ሀገር የሚኖር ኢትዮጵያዊ ሁሉ ዘርና ጎሣ፣ ኃይማኖትና የፖለቲካ አመለካከት ሳይገድበው ያለ ጥፋታቸው በእስር ለዲሞክራሲ ለፍትሕ የበላይነትና ለሀገር ሉዓላዊነት ሲሉ ለሁላችን የጋራ ጥቅም ሲሉ የታሰሩትን ባስቸኳይ እንዲፈቱ ለማድረግና እንደ ግብጽ፣ ሊብያና ቱኒዝያ በሕዝባዊ ንቅናቄ ኋላቀሩንና አሸባሪውን የወያኔ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ከጫንቃችን አውርደን ለመገላገል ሁሉም ባለበት ”በቃ!” በሚል መንፈስ ወቅቱ የሚጠይቀውን የእናት ሀገር ጥሪ ምላሽ ሊሰጥ ግድ ይለዋል።
እግዚያብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅልን!!!
ቴድሮስ ኃይሌ - This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.



