የእንቧይ ካቡን ትተን ለወደፊቱ የአለት መሰረት እናብጅ (መርስኤ ኪዲን)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

መርስኤ ኪዲን This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ሰሞኑን የአንድነት ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጂነር ግዛቸው ሺፈራሁ “አንድነት ችግር ላይ ተጋርጧል … ሊዘጋ ይችላል” ሲሉ ዴይሊ ኔሽን ለሚባለው የኬንያ ጋዜጣ መግለጻቸውን ሰንደቅ ጋዜጣ ታህሳስ 28 ቀን 2002 ዓ.ም. ባወጣው ዕትሙ አስፍሯል። የኢትዮጵያን ፖለቲካ በአንክሮ ለሚከታተል ሰው ይህ ዜና ብዙም አስገራሚ አይሆንበትም። ለምን? ቢባል አንድነት መድረክ የተባለውን “የእንቧይ ካብ” የተቀላቀለ ጊዜ እንዳበቃለት ግልጽ ነውና። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሕዝብን ያሳተፈ ጠንካራ የተቃዋሚ አመራር ምርጫን በድል መወጣት ይችል ይሆን? (ብሩክ ለማ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ብሩክ ለማ ከስድስት ኪሎ bThis email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

በግንቦት 2002ቱ ምርጫ የ1997ቱን ያህል የሕዝብ ተሳትፎን መጠበቅና የለውጥ ተስፋን መሰነቅ ከምኞት ባያልፍም፣ አጋጣሚውን ተጠቅሞ የግፈኛ ስርዓቱን እድሜ ለማሳጠር መትጋት ግን ተገቢ ነው። መላው ሕዝብም ሆነ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚጠበቅባቸውን ከተወጡ ቀዳዳ አይጠፋምና የምንጠብቀው ድል ላይርቅ ይችላል። በምርጫ መሳተፉ ዋና ግቡ የፖለቲካ ስልጣንን በሕዝብ ይሁንታ መቆጣጠር ቢሆንም በምርጫ ሂደት የተፈጠረ ደባና ሴራን አጋልጦ የአሸነፍኩ ባይን ህጋዊነት መንፈግና እንዲነፈግ በማድረግ ቀጣይ ትግልን ማፋፋም ሌላኛው ግብ ተደርጎ መወሰድ ይኖርበታል። የሕዝብን ስሜት በአግባቡ ተረድቶ፣ ከወያኔ የአፈና ስርዓት ጋር አገናዝቦ ትክክለኛ ስትራተጂን መቀየስ ወደ ተጠቀሰው ድል ያደርሳል። የዚህ ፅሁፍ ዓላማም በዚሁ ዙሪያ ያጠነጠነ ሲሆን በምርጫው ለመሳተፍ ሽር ጉድ የሚሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ምረጠኝ የሚባለው ሕዝብ ቢያጤኗቸው ወደ ተሻለ ውጤት ሊመሩ ይችላሉ የሚባሉትን ይጠቁማል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አማተሩ የአቶ መለስ ፊልምና ትውስታዎቻችን (ሀብታሙ አሰፋ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ሀብታሙ አሰፋ (ከላስ ቬጋስ)

በኢትዮጵያ ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት ነው። በህዝቡ ዘንድ ጎልቶ የሚደመጥ አንድ መራር ቀልድ ነበር። የአሜሪካ የስለላ ድርጅት ሲአይኤ የሩሲያው ኬጂቢ እና የኢትዮጵያው የወያኔ የስለላ ቡድን ከፌዴራል ፓሊስ ጋር ተጣምሮ ለአንድ ግዳጅ ይቀርባሉ። ግዳጁ ነብር አድሮ ማምጣት ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቻውቼስኮ እንደ መለስ፤ ኤሌና እንደ ሀዜብ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ልጅ ተክሌ - ከካናዳ

ትንቢተ ሮማኒያ፤ መልእክተ ኢትዮጵያ

1989 ዓ.ም. ነው እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር። ታህሳስ፡ 1981 ዓ.ም. እንደ ኢትዮጵያ። በዚያ የሆነው በ20?? የሚሆነውና ያሳያል እነሆ በሮማኒያ የተከሰተውን ታሪካዊ ክስተት ማተት ፈቀድን። በዚያም ጊዜ እንዲህ ይሆናል። ከዚያ አስቀድሞ በሆነ ግዜም፤ ኒኮላ ቾቼስኮ አላደመጠም ነበር። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከ92 እስከ 2002 ልደቱ አያሌው፤ እሱም አጣን እኛም አጣነው

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

አለቃ ተክሌ - ቫንኩቨር (ካናዳ)

ትንሽ ወደኋላ፤ የጠፉት በጎች ሲወለዱ

ጥቅምት 1992 ዓ.ም. (መሰለኝ)። አዲስ አበባ ኢትዮጵያ። ሶሰት አራት መልካቸው ያመረ፤ ወጣት፣ ሱፍ የለበሱ ቁመናቸው ብቻ ሳይሆን አቋማቸውም ጭምር የሚመሳሰል፤ ግማሹ እስላም ግማሹ ክርስቲያን፣ ግማሹ ጉራጌ ግማሹ አማራ ግን ደግሞ የሚመቹ ኢትዮጵያዊ ወጣቶች/ጎልማሶች የፖለቲካ ፓርቲ አቋቋሙ ተብሎ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ሲነገር ከምር የወሰድናቸው አልነበርንም። ብንኖርም ብዙ አልነበርንም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...