የተያዘው ሥራ ህዝብን ማስተባበር ወይንስ ከትግሉ ፈጽሞ ማራቅ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ፍቅሩ ይበልጣል

ሰሞኑን በሀገራችን ፖለቲካ ለሁለተኛ ጊዜ የህዝብን ቅስም የሚሰብር ድርጊት በመካሄድ ላይ ይገኛል። በአንድ ወቅት የህዝብን የጋለ ስሜት አነሳስቶ የነበረውና ወደ ድል ሊያሸጋግረው ነበረው የቀድሞው ቅንጅት፣ በአመራር ላይ ባሉ ግለሰቦች አሳፋሪ የሆነ ድክመት ባልታሰበና ህዝብና ደጋፊ ባልጠበቀው ሁኔታ መንገድ ስቶ ተንኮታኩቶ ወደቀ። ያንን የወዳደቀ ስብርባሪውን አንስተው፣ ጠግነው፣ የተሰበረውን የህዝብ ልብ መልሰን ቀድሞ ወደነበረው አመኔታ እንመልሰዋለን በማለት የተነሱ ጥቂት አመራሮች እንደገና በማንሰራራት የቅንጅት ወራሽ የሆነውን አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ በሚል ስያሜ በመመስረትና ልበ ሙሉዋን ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን በመሪነት በመምረጥ ትግሉን ለመቀጠል ለህዝብ ቃል ገቡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዶ/ር ነጋሶና አቶ ስየ አንድነትን ተቀላቀሉ፤ ኢትዮጵያዊነት እያሸነፈ ነው (ግርማ ካሣ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ግርማ ካሣ (ቺካጎ) This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

“ኢትዮጵያውያንን እስከሆንን ድረስ ትግራይ መሬታችን ነው። ኦሮሚያ መሬታችን ነው። ደቡብ ና ሶማሊያ መሬታችን ነው። አፋርም መሬታችን ነው። ለነርሱም ትግራይ መሬታቸው ነው። አማራም ትግራይ መሬቱ ነው። ሊኖርበት ይችላል። በዚህ ማመን አለብን። ከዚህ ውጭ የፖለቲካ ተቃዋሚ ድርጅቶችን እንደጠላት ለማስፈራሪት መጠቀም የሥልጣን እድሜን ማራዘሚያ እንደሆነ መታወቅ አለበት። አሁንም በሰላምዊ ትግል ካመኑትና ሕጋዊ ፈቃድ ካገኙት ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር አብረን መሥራት እንቀጥላለን።” - አቶ ገብሩ አሥራት

“ኢትዮጵያ እኮ የኢህአዲግ ብቻ አይደለችም። ኢትዮጵያ የእኛም ናት” - አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

“ኢትዮጵያችን” - ዶ/ር መራራ ጉዲና

አቶ ስየ አብርሃና ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የሚመራውን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ መቀላቀላቸውን በተመለከተ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው። አስተያየቶቹ በጥቅሉ ብንመለከታቸው በሦስት ምድብ የሚከፈሉ ናቸው። የመጀመሪያው ምድብ የአብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ስሜት ያንጸባርቃል ብዬ የማስበው፣ በአቶ ስየ አብርሃና በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ውሳኔ የተደሰቱ ኢትዮጵያውያን አስተያየቶችን የያዘ ምድብ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ግልጽ ደብዳቤ ለጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ይድረስ ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ

ከየሺወርቅ ወንድሜነህ (የኢትዮጵያ ተወላጅ፣ የዓለም ዜጋ - በስዊድን ኗሪ)

የኢትዮጵያ ህዝብ ወደ 85 ሚሊዮን ደርሷል ተብሎ ይገመታል። ከህዝቡ ወደ 57 በመቶ የሚሆነው ለመጠጥና ለምግብ መሥሪያ የሚሆን ውሃ እንኳን በመኖሪያው አካባቢ አያገኝም። ለመፀዳጃ የሚሆን ውሃ የማያገኘውማ ከመቶው 89 ይደርሳል። ከመቶው 38 ያህሉ ህዝብ ሳይጠግብ የሚያድር ደሃ ነው። ከመቶው ስምንቱ ህፃናት አምስት ዓመት ሳይሞላቸው ነው የሚሞቱት። እነዚህ ከሞላ ጎደል ተጨባጭ የሆኑ መረጃዎች ለኢትዮጵያ ህዝብ በጣም መሠረታዊ የሆኑትን ፍላጎቶቹን እንኳን የማሟላት ሁኔታ እንዳልተፈጠረለት የሚያሳዩ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መጪው ምርጫና የብርቱካን ሚደቅሳ የመፈታት መቼት?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ክርስቲያን

አብዛኛውን ጊዜ አምባገነን መሪዎች እንዴት እንደሚያስቡ ማወቅ ካባድ ነገር ነው። ባህሪያቸውን ለመተንበይ በጣም አስቸጋሪ ነው። ግን ይህንን ከባድ ነገር ለመሞከር ተነሳሁ። ብርቱካን መቼ እንደምትፈታ ለማወቅ ከመጓጓቴ ብዛት የማይደፈረውን ለመድፈር አሰብኩ። እናም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የብርቱካንን መፈታት መቼ እንደሚፈቅዱ ለማወቅ ሞከርኩ። ከምርጫ በፊት ወይስ ከምርጫው በኋላ?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአቶ ስየ አብርሃና የአቶ ልደቱ አያሌው ትችቶች

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

“የፓርቲዎች የሥነምግባር ሕግ” በኢህአዲግና በተቃዋሚዎች መካከል መፈረሙን ተከትሎ የመድረክ መሥራች የሆኑት አቶ ስየ አብርሃ “ሥነምግባር ሲሉ …” በሚል ርዕስ ሀገር ቤት በሚታተመው “አዲስ ነገር” ጋዜጣ ላይ ኅዳር 5 ቀን 2002 ዓ.ም. ዕትም ላይ አስተያየት ሰጥተው ነበር። የአቶ ስየን አስተያየት አስመልክቶ አቶ ልደቱ አያሌው ደግሞ “እነ አቶ ስየና የስምምነት ጥላቻቸው፤ ‘አርባ ዓመት ውቅያኖስ ውስጥ የኖረ አለት መዋኘት አይለምድም’ …” በሚል ምላሽ ሰጥተዋቸዋል። የሁለቱንም ወገኖች አስተያየት ለአንባብያን ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ አቅርበነዋል። መልካም ንባብ!!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከሳጥን ውጭ ማሰብ አይከፋም (ኩችዬ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Hailu Shawel shaking hands with Meles Zenawi (ስለ ኃይሉ፣ ኢህአዴግ፣ ፈረንጆቹና ብርቱካን)

ኩችዬ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ብርድ ልብስ ውስጥ እንደተጀበንኩ የኢትዮጵያን ፖለቲካ መፍታት ሲሳነኝ የቡና ተርቲበኛ ወዳጄን “ካሪቡ” እንደምቀጥረው አምና አካባቢ ያጫወትኳችሁ መሰለኝ። እጣኑ ይጐድል እንደሁ እንጅ የካሪቡ ቡናና የቤቱ ጌጥ (ፌንክ-ሹዌ ይሉታል ቻይናዎች) ከራማ ያስታርቃል። ታዲያ ይሄ ወዳጄ አንገቱን ከብርድ ልብስ ውስጥ ብቅ አርጎ መወያየትን አይፈራም። ጥልቅ አሳቢነቱን ብቻ ሳይሆን ወዛም ጨዋታውንም እናፍቀዋለሁ። እንዲህ ያለ ወዳጅ አያሳጣችሁ አቦ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...