አቶ መለስና ወ/ት ብርቱካን ሲነፃፀሩ (ግርማ ካሣ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ግርማ ካሣ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

ሁለቱም በኢትዮጵያ እየተፋፈመ በመጣው የፖለቲካ ሂደት ውስጥ ትልቅ ስፍራ አላቸው። ሁለቱም አባል የሆኑበት ድርጅት ሊቀመንበር ናቸው። ሁለቱም በደጋፊዎቻቸው ይደነቃሉ። ሁለቱም የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ የነበሩ ጊዜ ጎበዝ ተማሪዎች ነበሩ። ሁለቱም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነበሩ። ሁለቱም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት በአዲስ አበባ ነው። ሁለቱም ወላጆች እንደመሆናቸው የልጅን ፍቅር ያውቃሉ። ሁለቱም ኢትዮጵያውያን ናቸው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመጪው ምርጫ ቧልትና ቁምነገር (ይኸይስ ሞረዳ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ይኸይስ ሞረዳ - ከአዲስ አበባ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

እንደመንደርደሪያ

በኪነ ጥበብ ዓለም ቧልታይ ተውኔት (Farce) የሚባል የኮሜዲ ዘውግ አለ። የቧልታይ ተውኔት ዋና ተግባር የተጋነኑና በእውኑ ዓለም ከምናያቸው ሁነቶች ወጣ ያሉ፣ ከዕለት ተዕለት የኑሯችን ገጠመኞች የራቁ ጉዳዮችን ይሁነኝ ብሎ (deliberately) በመከሰት ተመልካችን ወይም አድማጭን ማሳቅ፣ ማዝናናትና ማስደሰት ነው። የኮሜዲ ዘር በመሆኑም ፍጻሜው በደስታ የሚደመደም ታሪክ ያለው ተውኔት ወይም ድራማ ነው። አድማጭም ሆነ ተመልካች ብዙ ቁምነገር የሚገበይበት አይደለም- ምንም እንኳ ሳቅና መዝናናት በራሱ አንዳች ፋይዳ ያለው ነገር ቢሆንም። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ምርጫው የማይከበርለት ሕዝብ እንዴት “ምረጠኝ” ይባላል? (ሀብታሙ አሰፋ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ሀብታሙ አሰፋ

የአቶ መለስ አስተዳደር ደጋግሞ እንደተናገረው የ97ቱ ምርጫ እንዳይደገም ቀዳዳዎችን ሁሉ ደፍኗል። እነዚህ ቀዳዳዎች የታወቁ ናቸው። ምርጫ እንዳይኖር የሚያደርጉ የአፈና እርምጃዎችን ነው። ይቃወሙኛል የሚላቸውን ሁሉ በሞትና በእድሜ ልክ እስራት የሚቀጣበት የፀረ-አሸባሪነት ሕግ አውጥቷል። ከዚህ አልፎም ሕጉ በነማን ላይ እንደሚሰራ እነ ጀነራል ተፈራ ማሞ በፈጠራ ወንጀል በዚሁ አዋጅ መሰረት ተፈረዶባቸዋል። በ97ቱ ምርጫ በገለልተኝነት የታዘቡ የሲቪል ማህበረሰቡን የሚወክሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ፀጥ የሚያደርግ አዋጅ ወጥቷል። የፕሬስ ነፃነት ተስፋ ጭምር እንዲጨልም የዘጋውን ዘግቷል። ያሰጉኛል የሚላቸውንም የቀሩትን ለይቶ ተራ በተራ ለመጨፍለቅ ዘመቻ ይዟል። ተቃዋሚዎችን ለመከፋፈል የጀመረው ዘመቻ ከቅንጅት ውህደት ተቃውሞ ተነስቶ አጋር ተቃዋሚዎች እስከማፍራት ሄዷል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወያኔ/ኢህአዲግ የሚፈልገው አንድነት/መድረክ ከምርጫው እንዲወጣ ነው (ግርማ ካሣ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ግርማ ካሣ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ምርጫውን በተመለከተ ሀገር ቤት ያሉ ድርጅቶች የሚበጃቸውን እንደሚያውቁና በተለይም ውጭ ሀገር ያለን ብዙ ጫና ማብዛት እንደሌለብን የሚገልጽ ሃሳብ ከጥቂት ወራት በፊት፣ ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም. “ኢህአዲግ ብርቱካን ሚደቅሳን ለምን ይፈታታል?” በሚል አርዕስት በጻፍኩት ጽሁፍ ላይ አቅርቤ ነበር። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዘር ፖለቲካን እናምክን! (አማኑዔል ዘሠላም)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

አማኑዔል ዘሠላም This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ኢህአዲግ ስልጣን በጨበጠ በአሥራ ስድስት ወራቱ ነው ሀገሬን ለቅቄ የስደት ኑሮ የጀመርኩት። በማውቃቸው የአሥራ ስድስት ወራቱ የኢህአዲግና የኦነግ የጋራ አገዛዝ፣ የባንክ ሰራተኞች ያለምንም ርህራሄ ሲባረሩ፣ በበደኖና በአርባ ጉጉ “ነፍጠኞች” እየተባሉ ኢትዮጵያውያን በግፍና በጭካኔ ሲገደሉ አስታወሳለሁ። በድሬደዋ ከተማም ለሶስት ቀናት ተቀስቅሶ የነበረው የዘር ግጭት በዚያ ወቅት ነበር የተከሰተው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ተባብሮ መዳን ወይስ ተበታትኖ ማለቅ? (ሣሙኤል ይሄነው)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ሣሙኤል ይሄነው This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

አብዛኛው ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊ የሚስማማበት ጉዳይ ቢኖር የችግሮቻችን መጠን፣ አይነቶችና ምንጮቻቸው ቢለያይም ቅሉ፤ ችግሩ ግን በዘር፣ በቀለም፣ በጎሣ፣ በጾታ፣ በዕድሜ፣ … ወዘተ ሳይለይ የእያንዳንዱን ቤት በየተራ ማንኳኳቱ ነው። ኑሮ የከበደው፤ ነፃነቱን ተገፍፎና ተረግጦ ያለው፤ የተራበው፤ ፍትህ የተጠማው፤ … እከሌ ተከሌ ሳይባል አብዛኛው ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ይታወቃል። ይሄ እውነት ከሆነ ታዲያ ለውጥ ማምጣት እንዴት ከበደን? የምር የተገፋና የመረረው ህዝብ እንዴት ዝም ይላል? ሙሉውን አስነብበኝ ...