“ካርቱም ሄዶ ቀረ” እንዲሁም “ካምፓላ ሄዶ ተቀረቀረ”
ክፍሉ ሁሴን
ስደት ለወሬ ያመቻል እንዲሉ በ1999 ዓ.ም ስደት ከገባሁ ጀምሮ መጽሐፍ እጽፋለሁ እያልኩ እንደፎከርሁ አለሁ። ሳልሞክር ግን አልቀረሁም። በተለያየ ጊዜና በተደጋጋሚ እያነሳሁ ከጣልኩ በኋላ ለስንፍናዬ መጽናኛ ያደረኩት በቅርቡ እስተወዲያኛው ያሸለበው ስብሃት ገብረእግዚያብሄር በአንድ ወቅት በራዲዮ ቃለምልልስ “ከመጻፍ መኖር ይበልጣል፤ የምንጽፈው ከኑሮ ነውና” ያለውን በመውሰድ ‘መች ኖርኩና ለመጻፍ እጋበዛለሁ’ ብዬ ራሴን ቀስ በቀስ በቁመና እየገዘገዝኩት እገኛለሁ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
በወሎ ክፍለ ሃገር፣ የዛሬ 81 ዓመት የተወለዱት ማሞ ውድነህ፣ ወላጆቻቸውን በአምስቱ አመት የጣሊያን ወረራ ጊዜ ነው ያጡት። ማሞ ውድነህ 12ኛ ክፍልን ያጠናቀቁት ገና በ15 ዓመት እድሜያቸው መሆኑ በጊዜው ተደናቂ ወጣት አድርጓቸው ነበር። ከዚያም ወደ ጽሁፍ ዓለም በመዝለቅ እጅግ በርክታ መጻህፍትን ሲጽፉ፣ ብዙዎች፣ በተለይ በስለላ ሥራ ላይ ያተኮሩ መጻህፍትን ተርጉመዋል።


