ግርማ ካሣ
መግቢያ
ዲሞክራሲ «ዴሞክራቶስ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ነው። «ዴሞስ» በግሪክ ቋንቋ ሕዝብ ማለት ሲሆን፣ «ክራቶስ» ደግሞ ኃይል ወይም ስልጣን ማለት ነው። «ዴሞክራቶስ» የሕዝብ ኃይል ወይንም የሕዝብ ስልጣን እንደ ማለት ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ግርማ ደገፋ ገዳ
ከሉሳካ (ዛምቢያ) ወደ ደቡብ አፍሪካ፣ ለጥቁር ደቡብ አፍሪካ ሕዝብ ይተላለፍ የነበረውን የኤ.ኤን.ሲ. ራዲዮ ጣቢያ፣ ዘረኛው የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ጃም ያደርገው ነበር። ጥቁር ደቡብ አፍሪካዊ ሆኖ በደቡብ አፍሪካ መወለድ፣ በገዥዎቹ ነጮች ዓይን ወንጀል ስለነበር፤ ዘረኛው የነጮች መንግሥት፣ አውሬ መሳይ ገዳይ ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎችን በጥቁር ደቡብ አፍሪካዊያን አንጀት ላይ ነድቷል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ክፍል 2. መሪ የሌለው ሕዝብ እረኛ እንደሌለው መንጋ ነውና መሪዎቹን ከሕዝቡ መነጠልና ከሀገር ማስወጣት
ከእለት ተዕለት ኑሮው ጋር እየኖሩ፣ ደስታውንና ሀዘኑን እየተጋሩ በየቀኑ የሚያድገው አስተሳሰብ ከሚፈጥረው እውነታን ገላጭ ቋንቋ ጋር ተሳስረው የሚኖሩ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣ መምህራን፣ የኪነጥበብ/ስነጥበብ ሰዎች፣ ተማሪዎችና ሌሎችም ህብር ነው የአንድን ማሕበረሰብ ጠንካራ ቁርኝት የሚገልጹት። እንዲህ ያለ ጠንካራ ትስስር ያለው ማሕበረሰብ ውስጥ የሚፈጠሩ መሪዎች ደግሞ በቀላሉ በችግሮቹ ዙርያ መወያየትና መፍትሄ መፈለግ ይችላሉ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ግሩም ተ/ኃይማኖት
ሀበሻ በየመን (ክፍል 11)
ተንደርድሬ ጥልቅ ሳልሰናበት ውልቅ ማለት አለመደብኝም እና ወደ ዋናው ጉዳይ ከመግባቴ በፊት የዚህ ሰሞኑ ዜናዎች እንደመክፈቻ ላቋድስ። ታዲያ ዜና ዘገባው ከተለያየ አቅጣጫ በመሆኑ እና በዛ በማለቱ የዜና አምድ እንዳይመስል ስል አሳጥረዋለሁ ስለዚህ ቅድመ ይቅርታ ላቅርብ። እለት ከእለት ወደ የመን የሚፈልሰው ስደተኛ ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ እንዳሳሰባቸው ቀይ መሰቀል፣ አይ.ኦ.ኤም. እና በጉዳዩ በጥምረት እየሰሩ ያሉ ድርጅቶች አስታወቁ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም
(ፍትህ እትም ቁጥር 176 አርብ የካቲት 16 2004 ዓ.ም.)
መንግሥት ለሚባለው ድርጅት የመጨረሻው ተጠያቂ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ‹‹መንግሥት ሌቦች›› በአደባባይ ሲናገር ከሌቦች ጋር እየሠራ በመሆኑ እንድናዝንለት ነው? ወይስ ምን እንድናደርግ ነው? ሰዎቹን እንዳንቆጣለት ስማቸውን አልነገረንም፤ ከዚያም በላይ የሚያስፈራው ማፈኛ የሽብርተኛነት ክስ አለ፤ ሰሞኑን በኢንተርኔት የሚሰራጨው ወሬ ታላላቅ ባለሥልጣኖች የሚያሠሩዋቸው ስለተባሉት ታላላቅ ሕንፃዎች ነበር፤ ስደት ለወሬ ይመቻል እንደሚባለው አጉል ጉረምረም መስሎን ነበር፤ አሁን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አምርሮ ስለ‹‹መንግሥት ሌቦች›› የሰጠው ምስክርነት ወሬውን ያጠናክረዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...አቢይ አፈወርቅ
ባለፈው ሳምንት የብዙዎችን ትኩረት የሳበው ዜና ተቀማጭነቱን በአሜሪካ ያደረገውን በአቡነ መርቆሪዎስ የሚመራውን የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን አዲስ አበባ ካለውና በተመሳሳይ መጠርያ በአቡነ ጳውሎስ ከሚመራው ቤ/ክርስቲያን ጋር ለማስማማት የተደረገው ጥረት ነበር። ሁለቱም ቤ/ክርስቲያናት ተወካዮቻቸውን ወደ አሪዞና ልከው መደራደራቸው ቢታወቅም የማይጣጣሙ ቅድመ ሁኔታዎቻቸውን እንደያዙ ለቀጣይ ውይይት በቀጠሮ ነበር የተለያዩት።
ሙሉውን አስነብበኝ ...እንግዲህ ቴዲ አፍሮ የፈለገውን ቢያፈቅር ወይም በፈለገውና ባልፈለገው ቢፈቀር የኛ ጉዳይ አይደለም። ‘ቴዲ አፍሮ የኛ ነው’ ለሚሉትም ‘ተስፋ ቁረጡ!’ ማለት ጥሩ ምክር ሊሆን አይችልም። አንድ በሩቅ የማውቃት ወጣት ሶማሌ አለች። ከወደ ደቡብ ሶማሊያ እና ቆንጆ ናት። ኢትዮጵያዊ በገጠማት ቁጥር ኃይለኛ ስልኳን ላጥ ታደርግና የቴዲ አፍሮን ዘፈን ታሰማለች። ‘ምን እንደሚል አላውቅም፤ ግን ዘፈኑንም እሱንም እወዳቸዋለሁ’ ትላለች። ‘ደሞ ባንቺ የተነሳ ሞቃዲሾን እና አዲስ አበባን በፌዴረሽን ወይም በኮንፌዴረሽን ስለመቀላቀል እንዳይዘፍንልንና ዳግም እስር እንዳይገባ’ እላለሁ በሆዴ። ዳህላክና ኢየሩሳሌም ከደረሳቸው ቀጣይዋ ሞቃዲሾ የምትሆን እየመሰለኝ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...“ስብ ት ለአብ…”፣ ሰሙኑ ምን ያልተከሰተ ነገር አለ? የህወሓት 37ኛው የልደት በዓል በሚከበርበት፣ ፈላስፋው ዘርአያዕቆብ ባስታወስንበት ድንቅ የፍልስፍና ቀን ማግስት ስብ ት ለአብ ገብረ እግዚአብሔር አጋፋሪ እንዳሻውን ተከተላቸው። በሰማእታቱ ቀን መሆኑ ነው። የቀድሞው የግብርና ምኒስትር ጓድ ተፈራ ዋልዋም ከርቸሌ ጎብኝተው እንደወጡ ሰማን። በዚህ ቢያሳልፈው ጥሩ ነበር። ነገር ግን አልሆነም።
ሙሉውን አስነብበኝ ...