የሀብታሙ አያሌው ባለ አራት ምዕራፍ ፖለቲካ
ይገረም አለሙ

አቶ ሀብታሙ አያሌው እሱም ብዙ እያለ ስለ አርሱም እየተባለ ነው። ፖለቲካችንም ማህበራዊ ኑሮአችንም የተቃኘው በእውነት ላይ ሳይሆን በስሜት ላይ ሆነና አፍቅረን ሰንደግፍ ሆነ ጠልተን ስንነቅፍ ምክንያት ብቻ አይደለም ለከትም የለንም። ሜዳው ላይ ልጆች በዙና፣ ጨዋነት እየኮሰመነ ዋልጌነት እየገነነ መጣና ትላልቆቹ ዕድሜ ጠገቦቹ ተግባራቸው አገር ሊያድን፣ ረጋ ሰከን ብሎ ነገሮችን ግራ ቀኝ አይቶና መዝኖ የመደገፍም የመንቀፍም ባህል የሌለን መሆናችን ሰሞኑን በአቶ ሀብታሙ አያሌው ዙሪያም እየታየ ነው። ሜዳው ላይ ልጆች በዝተው ጨዋነት እየኮሰመነ ዋልጌነት በመግነኑ ትላልቆቹ ስራቸው አገር ሊያድን ምክራቸው ትውልድ ሊቀርጽ የሚችሉቱ አፋቸው ከመናገር እጃው ብእር ከማንሳት በመቆጠቡ ነገራችንን በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ እንዲሉ አድርጎታል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...









