የአንበሳ ልጅ ሳለ የጅብ ልጅ ገነነ፣ አላስበላም አለ ጸጉሩ እየበነነ

ይገረም አለሙ

Lion vs Hyena
ጅቦች አንበሲትን ሲያሳድዱ

ነገር በምሳሌ
ጠጅ በብርሌ፣
ይሉ የነበሩቱ
አበው እና እመው እነዛ የጥንቱ፣
እንደ አሁኖቹ ቃላት ሳይደርቱ
ዙሪያ ጥምዝ ሄደው ነገር ሳይጎትቱ፤
በምሳሌ አዋዝተው በስንኝ ቋጥረው
በሁለት መስመር ቃል - ቅኔ ተቀኝተው፤
ምክረ ነገራቸው - ከጆሮ ደጃፍ ነጥሮ ሳይመለስ
ከውስጠ ልቦና ከአዕምሮ እንዲደርስ፤
አድርገው ነበረ የሚያስተላልፉት
ሳይወርሰው ቀረ እንጂ ይሄ ትውልድ ንቆት፤

አልፎ አልፎ ለጽሁፌ የአበውን አባባል የምጠቀመው በሁለት ምክንያት ነው። ዋናውና የመጀመሪያው ምክንያቴ አባባሉ መልዕክቱ ጥልቅ ይዘቱ ምጥቅ የሆነና ዘመን ባዘመነው ይሁን ባደነዘዘው የእኛ ብዙ ደቂቃዎች የሚወስድ አገላለጽም ሆነ ቢጻፍም ገጽ የማይበቃውን ነገር መረዳት ለሚችልና ለሚፈልግ ሰው በአጭር የሚገልጽ በመሆኑ ነው። ሁለተኛው ሥልጣኔ የራስን እየተዉ፤ በተውሶ ነገር መኮፈስ ማለት ይመስል እንኳን ለልጆቻውን ሊያስተምሩ ለራሳቸውም ወግ ባህላቸውን የአነጋገር ዘያቸውን እየረሱ ላሉት ወገኖች በእግረ መንገድ ማስታወስ ከተቻለ በሚል ነው። ፕ/ር አዱኛ ወርቁ ጥርት ባለው አገርኛ አነጋገር ሲናገሩ፤ ሰለጠን ባዮቹ ቢከፍቱ ተልባዎች ብዙ እንደሚሉ ባውቅም፤ እኔ ግን እንዴት እንደምኮራባቸውና እንደምቀናባቸው እኔና እኔ ነን የምናውቀው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በስያትል ከተማ የተካሄደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ጉባዔ በመልካም ውጤት ተጠናቀቀ

ዘውገ ፋንታ

Prof. Mesfin Woldemariam in Seattle
ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም በስያትል ከተማ በተካሄደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ጉባዔ ላይ ንግግር ሲያደርጉ

መግቢያ

በስያትል ከሚገኙት አንዱ ነባር ድርጅት፣ ‘የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ፎረም’ የተባለው ለስድስት ወራት ያህል የተዘጋጀበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ጉባዔ ለሁለት ቀኖች ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ በምሽቱ በ12 ሰዓት ላይ በአስደሳች ውጤት ተጠናቋል። ይህ ጸሐፊ በቦታው ተገኝቶ ስለነበር፣ የቀረቡትን የተለያዩ ሀሳቦች፣ ውይይቶችና የጥያቄ መልሶች፣ ምንም እንኳን ሁሉንም ተንትኖ ለማቅረብ ባይቻልም እየቆነጣጠበ ከፊሎቹን ለማቅረብ ይሞክራል። ከአስራ ስምንት ሰዓት በላይ የተወሳውን ለማቅረብ እጅግ ይከብዳል። ስለዚህ አንባቢ ይኽን እንዲረዳ ጸሐፊው ይጠይቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚቅበዘበዙ ሁሉ እነሱ ይጠፋሉ እንጂ ኢትዮጵያ አትጠፋም” ፕ/ር አስራት ወልደየስ

ዶ/ር አበባ ፈቃደ

Prof. Asrat Woldeyes
ፕሮፈሰር አስራት ወልደየስ

ኢትዮጵያ በዓለም ጥንታዊ የሥልጣኔ ባለቤትነት፤ ቀዳሚና ዋና ከሆኑት አገራት ውስጥ አንዷና የመጀመሪያዋ ነች። በወዳጆቾ፣ በተቀናቃኞ፣ በጠላቶቿ ሆነ በራሷ ሊቃውንት በኩል በታሪክና በሳይንስ መዛግብት፤ የሥልጣኔ ቁንጮ የፍጥረታት ሁሉ ምንጭ፤ እጹብ ድንቅ ፣ የጠቢባን አገረ ፣ ቅድስት ምድር መሆኗ ተመስክሮላታል። ለምስራቅም ሆን ለምእራባዊ ሥልጣኔ መሰረት ተበሎ የሚታወቀው የግብጽ ሰልጣኔ ጭምር ምንጭ በመሆን የግብጽ እናት (Egypt the daughter of Ethiopia) ተብላ የተጠራች ኢትዮጵያ መሆኖ አከራካሪ አይደለም። ከጥንቶቹ ሄሮድትስ፣ ሆመር እስክ የቅርብ ጊዜ ሊቃውንት፣ ቼክ አንታ ዲዮፕ፣ ቤን ዮሃነን፣ ጸጋየ ገብረ መድህንን ዋቢ ምስክሮችን ለናሙና ያህል መጥቀስ ይቻላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአንድ ሰሞን ጩኸት፣ አይገኝ ነጻነት

ይገረም አለሙ

Protests accusing the Ethiopian government
የሕዝብ ተቃውሞ በገዥው ፓርቲ ላይ። [ፎቶ፣ Reuters]

እንደ መነሻ፣ ምክንያት እየፈለገ የወያኔን ኮቴ እየተከተለ የሚጮኸው ሁሉ በእኩል ደረጃና እምነት የወያኔ ተቀዋሚ መሆን አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ ነጻነት ፈላጊ መሆኑ ራሱ አጠራጣሪ ነው። ይህ ባይሆን ኖሮ ከምር ሁሉም ነጻነት ፈላጊ ቢሆን ኖሮ የጎሣ አጥር፣ የኃይማኖት ድንበር ወዘተ እየሰራ በየግል ሕልሙ ታጥሮ ለውጥ ሊያመጣ ቀርቶ ሰሚ ሊያገኝ እንኳን ያልቻለ ጩኸት በየመንደሩ በማሰማት ላይ ተወስኖ ሃያ ስድስት ዓመታትን ባላስቆጠረ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአማራውን ማኅበረሰብ የመብት ትግል የማጠልሸት ዘመቻ

ሐመልማል

አማራ
በወያኔ/ሕወሓት በደል እየተፈፀመበት ያለው የአማራ ሕዝብ

ባለፉት 40 እና ከዛ በላይ ለሚሆኑ ዓመታት በኢትዮጵያ ህልውና ላይ የተነሱ የውጭም ሆነ የውስጥ ኃይላት በአማራው ማኅበረሰብ ላይ ያላካሄዱት የማጠልሸት እና የማጥላላት ተግባር አልነበረም። በዚያድ ባሬ የሚመራው የሶማሊያ ወራሪ ኃይል አማራውን ቀንደኛ ጠላት አድርጎ ቀስቅሶአል። ኤርትራን ለመገንጠል የታገሉ ምንደኞችም የነጻነት ትግላቸው አማራ ከሚባል ሕዝብ ጋር የተደረገ በማስመሰል እንደነበር እናስታውሳለን። ወያኔ ገና ከመነሻው አማራውን እንደ ሕዝብ በጠላትነት ፈርጆ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳው ኢላማው እንድርጎአል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፕ/ር አስራት ወልደየስ 18ኛ ሙት ዓመት

ይገረም አለሙ

Prof. Asrat Woldeyes
እውቁ የቀዶ ሕክምና ባለሙያ ፕ/ር አስራት ወልደየስ

እውቁ የቀዶ ሕክምና ባለሙያ ፕ/ር አስራት ወልደየስ የወያኔ አብዮት ማግስት በዜጎች ላይ የተፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊት የህሊና እረፍት ነስቷቸው በሙያቸው ከበሽታ ሲፈውሱት የኖሩትን ኢትዮጵያዊ በፖለቲካ ትግል ከወያኔ የበቀል ደባ ለመታደግ የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት ፕሬዝዳንት ሆነው ለወያኔ የውስጥ እግር እሳት በመሆናቸው በእስር ተሰቃይተው ከሞቱ (ከተገደሉ ማለት ሳይሻል አይቀርም) እነሆ ግንቦት 2009፣ 18 ዓመት ሆናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጥፋቱ የማን ነው? የትግሬዎች ወይንስ የአማሮች?

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ጥፋቱ የማን ነው? የትግሬዎች ወይንስ የአማሮች?
እጅግ አሣፋሪና ታሪክ ይቅር የማይለው በደል “ወንድም በወንድሙ ላይ” ሲፈጽም በጣም አሳዛኝ ነው

‘ትግራይ ሪፐብሊክ’ ውስጥ ሰሞኑን የእግር ኳስ ጨዋታ በአማራና በትግሬ መካከል ተካሂዶ እንደነበርና ትግሬዎች አማሮችን ሰባብረው መጣላቸው ከተሰማ ሰነበተ፤ አጀንዳ መፍጠር የማይታክታቸው ትግሬ ወያኔዎች በዚህችም እያንጫጩን ነው። “እሰይ!” አይባል ነገር ሆኖብኝ እንጂ ትግሬዎቹ ያደረጉት ነገር የማይጠበቅ አልነበረምና ጥፋቱ ሙሉ በሙሉ የአማሮች እንደሆነ የማተቤን መመስከር እችላለሁ። የቀበጡ ለት ሞት አይገኝም፤ ፍየል ሲሰባ(ም) ሾተል ያሸታል። ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ። ደግሞ ተረት ለአማራ ሊያቅት?! በንግሊዝ አፍም ልጨምርልህ ከፈለግህ - “When its time has arrived, the prey comes to the hunter.”

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመለስን ልቃቂት አይቶ፣ ሰው እንዴት ያድራል ተኝቶ?!

ይገረም አለሙ

የመለስ ልቃቂት
"የመለስ ልቃቂት" የኤርምያስ ለገሰ መጽሐፍ

የፖለቲካ የበላይነትን በማረጋገጥ የሥልጣን ዕድሜን ለማራዘም ኢኮኖሚውን መቆጣጠር ወሳኝ መሆኑ ጥናትና ምርምር የሚጠይቅ የተለየ እውቀትም የሚሻ ጉዳይ አይደለም። ፖለቲከኞቹ ብቻ ሳይሆኑ ማንኛውም ሰው ሊያውቀው የሚችል ጉዳይ ነውና። አበውም "ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ" ይላሉ። ቁም ነገሩ ታዲያ ማወቁ ሳይሆን መተግበሩ ነው። እናም ወያኔ ይህን አውቆ ጠቀሜታና አስፈላጊነቱን ተረድቶ በኢኮኖሚ የበላይነት ፖለቲካውን ለመቆጣጠርና የሥልጣን ዕድሜውን ለማረዘም ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ባለሥልጣናት ለራሳቸው መጦሪያ ለልጆቻቸውም ተንደላቆ መኖሪያ የሚሆን ሀብት ማከበታቸውን የአቶ ኤርምያስ ለገሰ የመለስ ልቃቂት መጽሐፍ በመረጃና በማስረጃ አሳይቶናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአዲሱ ዘመነ መሳፍንት አክቲቪስቶች መነገር ያለበት ቁጥር 11

በልጅግ ዓሊ

Flag map of Ethiopia
ኢትዮጵያ

ኔ ምን አገባኝ - የምትሉት ሃረግ
እሱ ነው ያረዳት - አገሬን እንደ በግ
የምትለው ግጥም - ልጽፍ አሰብኩና
ምንአገባኝ ብዬ - ቁጭ አልኩ እንደገና
ኑረዲን ኢሳ

እነሆ እኛም “እነዚህ ሰዎች” እያልን፣ እየተማረርን አንዳንዴ ከሕዋ እንደ መጡ ሰዎች እየተመለከትናቸው፣ ሲደላን አብረናቸው ለመስራት ስንሞክር፣ ሲከፋን ትግሉን ጥለን እየሸሸን ስናማ፣ ስንቀማጠል በውጭ አገር በድረገጽ፣ በፌስቡክ፣ በቲዊተር ትግሉን እኛ ነን የምንመራው ስንል፣ ሲሰለቸን እጃችንን አጥፈን እየተቀመጥን፣ እነርሱን መታገል ሳንችል ስንቀር ከራሳችን እየታገልን ስንከፋፈል፣ ስንፈራ አጠገባችን ያለው ጠላት አድርግን ስንወጋ፣ አገራችንን ቀስ በቀስ ሲፈራርሷት አብረን እያፈረስን ሦስተኛው ዓሥርተ ዓመታት ዋዜማ ላይ ደርሰናል። ዛሬማ ብለን ብለን የወያኔን የዘር ፖለቲካ እኛው በመድገም አሳፋሪ ዜጋዎች ሆነን እንገኛለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በወያኔ ዘመን ቀልዶች ለአፍታ ፈገግ በሉ!

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ (ከአዲስ አበባ)

በወያኔ ዘመን ቀልዶች
በወያኔ ዘመን ቀልዶች ፈገግ በሉ!

አንጀት እያረረ እርሱ ስለሚስቅ ሊሆን ይችላል “ጥርስ ሞኝ ነው” ይባላል - እንደማሽላዋ። ቢሆንም አይብዛ እንጂ ቁም ነገርን እያዋዙ በቀልድ መሰል እውነተኛ ገጠመኞች ማስተላለፍ መጥፎ አይደለም። አንድ ስዕል በሺህ ቃላት ይመነዘራል እንደሚባል አንድ ቀልድም በአንድ መጽሐፍ ቢመነዘር ቀልዱ ከሚሸከመው ቁም ነገር አንጻር ቢያንስ እንጂ አይበዛበትም። እናም ዛሬ የማስኮመኩማችሁ የወያኔ ዘመን ቀልድ በጣም ሊያስቃችሁ ስለሚችል ለዐይን ማበሻ መሐረብ ወይም እራፊ ጨርቅ ይዛችሁ አንብቡ። ትግሬ የሆናችሁ ወገኖቼ ከዘረኝነት ፈንጣጣ ካልተሸለማችሁና እንደጤነኛ ሰው ማሰብ ካልቻላችሁ በስተቀር ልትናደዱና ልትቆጡ ትችሉ ይሆናል። መፍትሔው ታዲያ አለማንበብ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ