አዘራፊና ዘራፊ ሲበላ ባለ አገር ይቀላውጣል (አስራደው - ከፈረንሳይ)
ወያኔ በጎሣ በረት ያጎራቸው የአስተሳሰብ ዴንክዬዎች፤ በታጎሩበት የጎሣ በረት ውስጥ ሆነው ሲያጓሩ ስንሰማ፤ እኛ እንደነሱ በዘረኝነት ታጥረን ሳይሆን፤ በኢትዮጵያዊነት ማማችን ላይ ሆነን ቁልቁል ስንመለከታቸው፤ እያንጋጠጡ የሚተፉት ሁሉ ተመልሶ ባፋቸው እየገባ፣ አረፋ ሲደፍቁ ስናይ፤ አዘንላቸው እንጂ አልጨከንባቸውም። ታዘብናቸው እንጂ አልከፋንም። ይበልጥ አበረቱን እንጂ ክንዳችን አልዛለም። ብዕራችን አንደበቱ ሳለ እንጂ አልተዘጋም። ሙሉውን አስነብበኝ ...
ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል የታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ነች። በምርጫ 97 ወደ ወህኒ ቤት ከተላኩት ጋዜጠኞች ውስጥም አንዷ ነበረች። ወደ 18 ወራት በእስር ቤት ቆይታለች። የወለደችውም በወህኒ ቤት በታሰረችበት ወቅት ሲሆን፣ ሕፃኑ ሲወለድ ከክብደት በታች በመሆኑ ማሞቂያ ወይንም ኢንኩቤተር ውስጥ እንዲገባ በፖሊስ ሆስፒታል ሐኪሞች ተወሰነ። የእስር ቤቱ ኃላፊዎች ግን ሥልጣናቸውን በመጠቀም ሕፃን ናፍቆት እስክንድር ማሞቂያ ውስጥ እንዳይገባ ፈረዱበት።




