ክቡር ሚኒስትር (ከሪፖርተር ጋዜጣ)

[በሥራ ምክንያት ውጭ አገር በሔዱ ቁጥር ክቡር ሚኒስትሩ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን አገራቸው ገብተው በእውቀታቸውና በገንዘባቸው እንዲሠሩና የልማት አጋር እንዲሆኑ ይወተውታሉ። አንድ የዲያስፖራ አባልም ይህን መልዕክት ተቀብሎ ከወንድሙ ጋር አንድ ፋብሪካ ለማቋቋም በኢትዮጵያ ውስጥ ይገኛል። ያጋጠመውን ሁሉ በየጊዜው ለክቡር ሚኒስትሩ ይነግራቸዋል]

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ ለኢሕአዴግ መሪዎች (በሊቢያ በኩል የተላከ)

እስክንድር ነጋ - (አዲስ አበባ)

ፓሪስ፤ ቅዳሜ፣ ምሣ ሰዓት፣ መጋቢት 10/2003

የሳርኮዚ የታላቅነት ህልም እየሆነ ነው... ምሳ ግብዣቸው ላይ የዓለም ዋና ዋና መሪዎች በአድናቆት ታድመዋል... «በመሪዎች መሪነት» አድምቀዋቸዋል ... ትንሽ የማይባሉ ፈረንሣዮች እንባ እየተናነቃቸው ነው፤ በታላቁ ንጉሣቸው ሊዊ 16ኛው ዘመን የነበረው ኃያልነታቸውን እየታወሳቸው ... ዛሬ ፈረንሳይ የዓለም መዘውር ሆናለች.... ሳርኮዚም በሊዊ 16ኛው ተመስለዋል። ኦባማ ብቻ የውሃ ሽታ ሆነዋል.... የመሪነቱን አክሊል ለአውሮፓዊያን አቀብለው ወደ ብራዚል ነጉደዋል። ግራ አያጋባም ጃል?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ

"መለስና ጉዋደኞቹ ሁለገብ የንግድ ሥራ አክሲዮን ማኅበር" በሥሩ ላቋቋማቸው እህት ኩባንያዎች ከ1967ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 36 ዓመታት ለልዩ ልዩ ክፍት የሥራ መደቦቹ ሥራ ፈላጊዎችን እያወዳደረ ሲቀጥር መቆየቱ ይታወቃል። በ1967 ዓ.ም. በዐዋጅ ቁጥር መዜአ/666/6606/66 ዓ.ም. መሠረት በሰባት አባላትና በሰባት ሶቪየት ሠራሽ አሮጌ ክላሽኖች መነሻ ካፒታል ትግራይ ላይ የተቋቋመው መለስና ጉዋደኞቹ ሁለገብ የንግድ ሥራ አክሲዮን ማኅበር በአሁኑ ወቅት በሚሊዮን የሚቆጠሩ አባላትን ያቀፈ ሲሆን ካፒታሉም በብዙ ቢሊዮኖች የሚገመት ዶላር፣ ፓውንድና ዩሮ የደረሰ መሆኑን በማስታወስ በተለይ ደንበኞቹንና ወዳጆቹን እንኩዋን ይህን ያልታሰበ ድንቅ አጋጣሚ ለመታዘብ በቃችሁ በማለት የተሰማውን ጥልቅ ደስታ ይገልጻል። በዚህ አጋጣሚ ታሪካዊ ጠላቶቹ እንደተለመደው ሁሉ እርር ድብን እንዲሉ ልባዊ ግብዣውን ሲያስተላልፍላቸው አሁንም በታላቅ አክብሮትና ሥጋዊ ሃሤት በመታጀብ ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመለስ ዜናዊ አስገራሚ ቃለ-ምልልስ ሲዳሰስ!

እስክንድር ነጋ (አዲስ አበባ)

ጠ/ሚ/ሩ ቃለምልልስ እየሰጡ ነው ... ቅዳሜ መጋቢት 3/2003 ... በዚያን ሰሞን ሞላ ብሎ የነበረው ሰውነታቸው አሁን ከሳ ብሏል ... ውይ! ውይ! ውይ! ... እኔን! ግን ... ግን ... ከትላንት ወዲያ ቱኒዚያ፣ ትላንት ግብፅ፣ ዛሬ ደግሞ ሊቢያ እየተፈራረቁባቸው ከሳ ማለትማ ይነሳቸው እንዴ? ... «ኑሮ ካሉት መቃብርም ይሞቃል» እንጂ፣ የሰሞኑ የመለስ የስጋት ኑሮ «ውስጡን ለቄስ» እንደተባለው ነው ... የስቃይ ኑሮ! ... አሳዛኝ ኑሮ! ... እኔን! ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ መለስ ይቺን ጽሑፍ ቢያነብልኝ ዕድለኛ ነኝ

ፍቅር ይበልጣል

አሁን ይህችን ጽሑፍ ስከትብ አዲስ አበባ አካባቢ ዝናብ እያካፋ ነው። በውጭ ለምትኖሩ ይህ ወሬ መልካም ዜና ነው። ፀሐይዋ አናት እየበሳች ተቸግረን ከረምን። የዝናብ መጥፋት በቅድሚያ ለእህል ዘር መጥፎ ነው። ቀጥሎም የአካባቢ ሙቀትን በመጨመር ለአየር ንብረት መዛባትና ለበረሃነት መስፋፋት እንዲሁም ለሰውና ለእንስሳት ሕይወት መጥፎ ነው። አሳስቦን ነበር ተመስገን። በዚሁ ያዝልቅልን። በሁሉም መበደል አይገባንም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠ/ሚኒስትሩ እንዴት ቀልድ ጨምሯል ጃል!

ይነጋል በላቸው

በቤቴ ኢቲቪ አይከፈትም። ከወያኔ ጋር ንክኪ ያለው ሬዲዮም እንዲሁ። ትክክል እንዳልሆንኩ ይገባኛል። ምን ላድርግ? ስለሚያመኝ እኮ ነው፤ ወድጄን መሰላችሁ? ይህቺን አልፎ አልፎ የምሞነጫጭራትን ነገር እንኳን የማቀራስመው ባብዛኛው በስማ በለው ከማገኘውና ከውጭ ሚዲያዎች ከምከታተለው ነው። ይሁንና እኔ አልሰማም ብልም ሰው እያመጣ ሳልወድ በግዴ ይነግረኛል። እምቢ አልል ነገር ከሰው ጋር ነው የምውል። ጓደኞቼ እየተናደዱ ትናንት ማታ ‘እገሌ እንዲህ አለ፤ እገሊት እንዲህ አለች’ ሲሉ ስለምሰማ አንዳንዴ እቤቴ አለማዳመጤን ሳስበው አልሸሹም ዘወር አሉ ዓይነት ነገር ይሆንብኛል። ጠበል ሄጄ ትግስቱን እንዲሰጠኝ ልለማመን ይሆን?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እንደጠላት ለሚታይ ሕዝብ ድጎማ ለምን?

ይነጋል በላቸው

የፕ/ር እንድርያስ እሸቴን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝደንትነት መሰናበት ልዩ የሚያደርጉ ሁለት ሰሞነኛ ክስተቶች አሉ። ቀዳሚውና ከዚሁ ግለሰብ ጋር በቀጥታ የሚገናኘው የወያኔ መንግሥት ቅሌትን እንደ ክብርና ሞገስ የሚቆጥር መሆኑን የገለጸበት መንገድ ነው። እንድርያስ እሸቴ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ድራሹን ማጥፋቱ በመለስ ዜናዊ አድናቆትና ከፍተኛ ዋጋ ተሰጥቶት ለማን ደስ ይበለው በሚል ይመስላል ሰውዬው በሚኒስትርነት ማእረግ የጠ/ሚንስትሩ የአቶ መለስ ‹አማካሪ› እንዲሆን ተሹሟል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ትኩረት ያልተሰጠው

ፍፁም ከእስራኤል

ኢትዮጵያ ሀገራችን የብዙ ብሔር ብሔረሰብ መኖሪያ ቤት መሆንዋ ይታወቃል። ሆኖም ግን እስካሁን ያሳለፍናቸውን ዘመናት ከታሪክ እንደተረዳነው በርካታ ጦርነት ተካሂደውባታል። የተደረጉት ጦርነቶች ጎሣን መሰረት ያደረጉ አልነበሩም፤ የግዛት አድማስን ለማስፋት ወይም ያለተቀናቃኝ ብቸኛው ንጉሥ ለመሆን እንጂ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አድርባይነታችን ብዙ እያስከፈለን ነው (ቀመሩ ደስአለኝ)

ቀመሩ ደስአለኝ

ኢትዮጵያ ውድ ሀገራችን በወያኔ ማፍያ ቡድን ተወራ፣ ብሔራዊ አንድነቷ፣ አሃዳዊ ሉዓላዊነቷ፣ ታሪካዊ ክብሯ ተደፍሮና ተዋርዶ፣ ሀገር ተቆርሳ ሀብቷ እየተዘረፈና እየተበዘበዘ፣ ለም መሬት እየተሸጠ፣ ህዝቧ ተረግጦ በጠብመንጃ ኃይል መብቱን ተነፍጐ፣ ፍዳውን ሲያይ እነሆ ሃያ ዓመት ሆነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...