የቀረንን ስላለማስነጠቅ፤ እሴታችንን ስለመጠበቅ!

ልጅ ተክሌ (ኦታዋ - ካናዳ)

መጀመሪያ አገራችንን፣ ቀጥሎ ደግሞ ባህላችንን፣ ከዚያ ማንነታችንን

1 - ሰዉ ሁሉ፡ የሚተነፍሰው ሊቢያን ነው። ግብጽን ነው። ቱኒሲያን ነው። የመንን ነው። ጅቡቲንም ሳይቀር። ስለዚህ ያኛው ጉዳይ ብዙ ሰዎች ስለበዙበትና የተጣበበ ስለመሰለኝ፡ “እንቁላላችንን ሁሉ ባንድ ቅርጫት” እንዳናደርግ በማሰብ፡ ደግሞም ትግሉ ፈርጀ ብዙ ስለሆነ እነሆ ፊቴን ወደ ባህልና ውርስ አዞርኩ። ለነገሩ የፖለቲካ ሩጫችንስ ቢሆን የባህልና የባህርይ ለውጥ ለማምጣት፡ ማንነታችንንና እኛነታችንን ለማስጠበቅ አይደል?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስጋት አርግዘን ስጋት ለብሰናል! (ግሩም ተ/ኃይማኖት - የመን)

በየመን ያለ ሀበሻ ቁጥሩ ሲጠራ የሚያምን የለም::ትክክል የማይመስል ነገር ነው። በህጋዊና ህጋዊ ባልሆነ ሁኔታ የመን ውስጥ ያለ ኢትዮጵያዊ ከ 80,000 በላይ ነው። 5000 የምንጠጋው በUNHCR ስር ያለን ስንሆን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለማቋረጥ እና የመን ለመኖር ከጅቡቲ..ከሱማሊያ..ተነስተው በባህር በየእለቱ የሚገቡትን መገመት ይከብዳል። ከ4,000,000 በላይ ትውልደ ሀበሻ አለ። ከአረብኛው ቀጥሎ ህዝቡ በሰፊው የሚናገረው አማርኛ ቋንቋ ነው ማለት ይቻላል። ይህ የሚያሳየው የመናዊያን እና ኢትዮጵያዊያን አብረው የኖሩ ህዝቦች መሆናቸውን ነው። ነገር ተገልብጦ ሆኗል። ትላንት ችግራቸውን ለመቅረፍ ወደ ሀገራችን እንዳልተሰደዱ ለሀበሻ ያላቸው ጥላቻ ኢትዮጵያን እጀ ሰባራ ያሰኛታል። ለነገሩ እንኳን የተጠለለባት ከአብራኳ የወጣውስ ነካሽ እንጂ አይዞሽ ባይ መች ሆናት?…ቢሆን ኖሮ ከነቀዞች ማላቀቂያው ሰዓት አሁን ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የበርሊኑ ጉባዔና የመሬት ሽሚያ (በወርቁ ለገሰ)

የቤልጅጉ ንጉስ ሊዮፖልድ የአፍረሪካን አህጉር ለመቀራመት በ1884 ዓ.ምየበርሊን ኮንፍረንስ እንደጠሩ ይነገራል።በዚህ ኮንፍረንስ ዩናይትድ ስቴትስ ስትቀር ሌሎች ታላላቅ የአውሮፓ መንግስታት ተወካዮቻቸውን ልከዋል። የበርሊን ኮንፍረንስ የምድርን ወገብና የቻድን ባህር ቋሚ ምልክት በማድረግ እንግሊዞች፣ ጣሊያኖች፣ ጀርመኖችና ፈረንሳዮች የአፍሪካን መልክአ ምድር እጣ ሲጣጣሉበት አንድም የአፍሪካ መሪ በመሬት ሽንሽኑ ስብሰባ የተካፈለ አልነበረም። በዚህ ስብሰባ ስምምነት መሰረት ከኢትዮጵያና ከላይቤሪያ በስተቀር የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች መላውን አህጉር ለአመታት ሲመዘብሩ ኖሩ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

ቀድሞ ሊያመጽ የሚችል ህዝብ ሊኖር ይገባ ነበርን? (ይሄይስ አእምሮ)

ይሄይስ አእምሮ

ኢትዮጵያ ውስጥ በሠላም መኖር ከፈለግህ ማሟላት የሚጠበቅብህ ብዙ ነገሮች መኖራቸውን አትርሳ። በዋናነት ግን ገበያ አትውጣ። የምትገዛው ነገር አይኑርህ - እንዲኖርህም በፍፁም አትመኝ። የማንኛውንም ዓይነት አላቂም ሆነ ቋሚ ዕቃ ዋጋ አትጠይቅ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጄኔራል ፃድቃን፣ ኢሕአዴግና የሰሜን አፍሪካ አብዮት (ክፍል ሁለት)

እስክንድር ነጋ (አዲስ አበባ)

መግቢያ ”ሻይ፤ በሎሚ፣ ያለስኳር” አልዃት፤ ትዕዛዝ ልትቀበለኝ ፊት ለፊቴ የቆመችውን ወጣት። ትላንት፤ ሰኞ፣ የካቲት 28 ቀን 2003 ዓ.ም፤ ከጠዋቱ 2 ሰዓት። ኢንተርኔት ካፌ እስከሚከፈት ሚጢጢ ሻይ ቤት ውስጥ ቁጭ ብያለኹ። በእጄ "OBAMAS" የሚባለውን ቢጫ እስክሪቢቶ ይዣለኹ። ጠረጴዛ ላይ ወረቀት አስፍሬያለኹ። የጀኔራል ፃድቃንን ክፍል ሁለት መጣጥፍ ለመጀመር እያቅማማኹ ነው። ቴሌቪዥኑ ትኩረቴን እየተሻማው ነው። የኒክ ኒልቴ የድሮ ፊልም በዐረብ ሳት እየተላለፈ ነው። ፊት ለፊቴ ሶስት ሰዎች ሞቅ ያለ ጨዋታ ይዘዋል። አንዱ ሽበት ጣል ጣል አድርጎባቸዋል። ሁለቱ ወጣቶች ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ገሀነም ደርሶ መልስ

ይድረስ ለአንድ የሀገሬ ወታደር!

ከአቢይ አፈወርቅ

“ቅዱስ ማለት ራሱን ንጹህ ለማድረግ ሙከራውን የማያቋርጥ ሀጢያተኛ ነው ይላሉ። ምናልባትም የህይወቱን 3/4ኛ ጊዜ ያሳለፈው በተንኮል ይሆናል። ይሁንና ቀሪውን የእድሜውን ሩብ በቅዱስ ተግባር በማሳለፉ ስሙ ሲወደስ ይኖራል።” ይህን ያሉት ኔልሰን ማንዴላ ናቸው። በኛ ዘመን ሰሌዳ ህዳር 30 ቀን 1972 ዓ.ም ከእስር ቤት ሆነው ለቀድሞዋ ባለቤታቸው ለዊኒ ማንዴላ ከላኩላት ደብዳቤ ላይ የተነቀሰ አባባል ነው። “አንዴ ሌባ - ሁሌም ሌባ” ከሚለው ጭፍን ድምዳሜ ርቆ ለክፉዎች እንኳ በህይወት እስካሉ ድረስ በጎ የመሆን ጀምበር እንደማትጠልቅባቸው የሚያሳይ ይመስለኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስጋ ቆራጭ እንደ ጆሮ ቆራጭ የሚያስፈራበት ጊዜ መጣ!?

አቤ ቶክቻው (ከአዲስ አበባ)

ወዳጄ እንዴት ሰነበቱልኝ? በዛሬው ወሬያችን ርእስ ያደረግነውን ጉዳይ ከማውጋታችን በፊት እስቲ ሌሎቹን ጉዳዮች ትንሽ ትንሽ እናውጋቸው! እንዴት ነው ወዳጄ ኮንዶሚኒየም ቤት እጣ ደረሰዎት እንዴ? እስቲ አዎ! ይበሉና ያስደስቱኝ። እውነቱን ለመናገር የዘንድሮው ኮንዶሚኒየም እጣ ደረሰኝ ብሎ ሲያወራ የሰማሁት አንድም ሰው እኮ የለም። ወይስ የኔ ወዳጆች በሙሉ ምዝገባው በነበረበት 97 አመተ ምህረት በስራ ተጠምደው የነበሩ ናቸው? የሆነ ሆኖ እጣው ከደረሰዎ እንኳን ደስ አለዎ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጄኔራል ፃድቃን፣ ኢህአዴግና የሰሜን አፍሪካ አብዮት

እስክንድር ነጋ (ከአዲስ አበባ)

ጥድፊያ፣ ጥድፊያ፣ ጥድፊያ ሰዓቱ እየደረሰ ነው። ገና መጣጥፉ አላለቀም፤ ይቀረዋል። መጻፍ ... ማረም፣ ... መሰረዝ ... እንደገና መጻፍ፤ ማስተካከል ... ምን ማለቂያ አለው ... ሁለት ሰአታት ይቀራሉ ... ለመጨረሻዋ ቡና ጊዜ አለ። እፎይ! ... የአርብ የግማሽ ቀን ውሎ ይህንን ይመስላል ... ለእኔ ለጸሀፊው። በዋሽንግተን ካለው ግዙፉ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጋር የአርብ ቀጠሮ ከያዝኩኝ ይሄው ሰነባብቻለሁ። ይህች ቀጠሮ እንዳትፋለስ ነው ጥድፊያው። ሌላው ዲያስፖራ እንኳን በሚመቸው ሰአት ነው የሚያገኘኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ውግዘት፣ ውርደት፣ ስደትና ተጠያቂነት

PM Meles Zenawiአምባገነን የአፍሪቃ መሪዎች ቀጣይ ዕጣ ፈንታ

ስሜነህ ታምራት በቀለ

አፍሪቃ በዕድገት ሂደቷ የፈጠረቻቸው መልካም አስተዳዳሪና ምግባረ ሰናይ ሰብዕናን የተላበሱ በጣም ጥቂት መሪዎች አሏት። በአንፃሩም በስም ካልሆነ በቀር በተግባር ከጥንታዊያን አፄዎችና ፋሽስቶች የማይለዩ በርካታ መሪዎቿ አጠቃላይ ዕድገቷን ለጉመው ይዘውታል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...