«የምርጫውን ውጤት ሕዝቡ ተቀብሎታል» አምባሳደር ቡዝ

እስክንድር ነጋ (አዲስ አበባ)

ቻይና ሰራሽ እስክሪብቶዬን ከገዛኹት ሁለት ቀናት እንኳን አላስቆጠርኹም። ገና ከወዲሁ እየተቆራረጠ ግን ትዕግስቴን እየተፈታተነው ነው። በዘመኑ የአራዳዎች ዘይቤ «ሙዴ» ሊበላሽ አፋፍ ላይ እየተንገዳገደ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

'ጥሎ ማለፍ'ን እንዳየሁት

(የመጽሐፍ ዕይታ - በአቢይ አፈወርቅ)

ፍርሃት… ሽብር… ጥርጣሬ!... ዘመኑ የአደጋ ነው። በእያንዳንዱ ህልመኛ ዙሪያ የስጋት ደመና አንዣቧል። ማንም ማንንም አያምንም፤ ጠላትና ወዳጅ የማይለይበት ጊዜ!... ሁሉም ትላልቁን ወንበር ያልማል። ተጫራቹ ብዙ፤ መድረስ የሚችለው ግን ጥቂቱ ነው። ‘ጥሎ ማለፍ’ የሚችለው ብቻ።…

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የተደበቁ እውነቶች (ነቢዩ ሲራክ)

ኢትዮጵያን ሯጮች በሳውዲ የደገሙት የአረንጓዴው ጎርፍ ድል (ክፍል 9)

ነቢዩ ሲራክ - ከሳውዲ ዐረቢያ

ከሰሞኑ ሰበር ቅኝት ...

ወደ እኛ ዘመን የተስፋ ምድር ወደሆኑት ዐረብ ሀገራት በተለይም ወደ ሳውዲ ዐረቢያ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በሚያደርጉት ጉዞና በሚያጋጥማቸው መከራ ዙሪያ በተከታታይ ክፍሎች የማደርገውን ቅኝት አላቆምኩም። ያለፈውን በትዝታ የማስቃኘው ዝካሬየ ነገም ይቀጥላል ... የዛሬው ቅኝቴ ከዚህ በፊት እንደማደርገው በሰሞነኛው ትኩረቴ በጅዳው ማራቶን በኢትዮጵያን አትሌቶች በተገኘው ድል ዙሪያ በማተኮር ያየሁ የሰማሁትን ከመረጃ ጋር ላጋራችሁ ግድ ይለኛልና ፈቃዳችሁ ከሆነ ተከተሉኝ ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ ግብጽ አይደለችም - አንድ ተብሎ የሚጀመረው

ናኦሚ በጋሻው - ሎንግ ቢች ካሊፎርኒያ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

በግብጽና በቱኒዚያ የታየውን ህዝባዊ እንቅስቃሴ እንደ ምሳሌ በመጥቀስ፣ ድርጅታዊ ሥራ ሳይሠራ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዛሬ ነገ ሊነሳ ይችላል ብለው ብዙዎች ይጠባበቃሉ። እነዚህ ሰዎች እንደጠበቁትም ህዝቡ ሊነሳ ይችላል። የወደፊቱን እንዲህ ነው ብሎ በርግጠኝነት ለመተንበይ ይከብዳል። ነገር ግን ያለውን ሁኔታ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ስናያቸው አሁን ባለው ሁኔታ ህዝቡ የሚነሳ አይመስልም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለመሠረታዊ ለውጥ መታገል ወይስ መገለባበጥ? (አሉላ)

አሉላ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

ኢትዮጵያ ሀገራችን ስላለችበት አስቸጋሪ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሁኔታና መወሰድ ስለሚገባው እርምጃ በግልም ሆነ በድርጅት ደረጃ የተለያዩ ጽሑፎች ይወጣሉ። ትክክለኛው የለውጥ መንገድ፣ መወሰድ የሚገባው እርምጃ ግን በታጋይ ፖለቲካ ድርጅቶች ዘንድ አሁንም አወዛጋቢና ወጥነት የሌለው ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ ቃለ ምልልስ ሲዳሰስ

እስክንድር ነጋ (ከአዲስ አበባ)

«ገራገር ይመስላል» አለኝ አንድ ወዳጄ ትክ ብሎ ምስላቸውን በመመልከት። «ውዥምዥም ሳይሆን አይቀርም» ብሎ ምስሉ ያረፈበትን የአውራአምባ ጋዜጣ ሲያቀብለኝ ከት ብዬ ሳቅኹኝ። የአማርኛ ችሎታው ላቅ ያለ ነው። የእኔ አላዋቂነት መቀለጃው ነው።

 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአግአዚ ሠራዊት እና የአግአዚ ልጅ

ሲሳይ አጌና

መጋቢት 20/2003 ምሽት ኮምፒውተሬን ስበረብር የታጋይ ዘርዑ ገሰሰ/አግአዚ ልጅ ትብለለጽ ብቅ አለች፤ ፎቶግራፏ ማለቴ ነው። አግአዚን ሳስታውስ ደግሞ የሰኔ 1997ቱ እና የጥቅምት/ህዳር 1998ቱ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ መጣብኝ፤ ...የቃሊቲ ክፍለጦር አባል የነበረውና ቃሊቲ ከእኛ ጋር አንድ ቤት ታስሮ የነበረው ሞላም ከፊቴ ድቅን አለ፤ የጓደኛው ኪሮስ መገደልና የእሱ የእስር ሁኔታ እንዲሁም የአግአዚ ሰራዊት የተደራጀ ግድያም ትዝ አለኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ፡ ሕዝባዊ ተቃውሞና የወታደራዊ መንግሥት ጥያቄ

እስክንድር ነጋ

የደርባባውና የ82 ዓመቱ አዛውንት ሆስኒ ሙባረክ ከስልጣን መውረድ ዓርብ አመሻሽ ላይ ሲበሰር፣ በግብፅ ታሪክ ተሰምቶ የማይታወቅ እልልታና ሆታ ቀለጠ... ሕዝብ በደስታ ሰክሮ ሌሊቱን አሳለፈ.... አይ ካይሮ ያቺን ምሽት!... እንዴት ትረሳለች?... እኛስ አብረናቸው አላደርንም እንዴ?... ዕድሜ ለአልጀዚራ፣ ለቢ.ቢ.ሲ፣ ለሲ.ኤን.ኤን፣ ለፕሬስ ቲቪ... የካይሮ ሕፃናት እንዴት ይረሱናል?... ገብቷቸው ይሆን እንዲያ የፈነጠዙት?... ጨለማውን ብርሃን እንደዋጠው እውን ለእነሱም ታይቷቸው ነበርን?... ቀልባቸው ነግሯቸው ይሆን?... የትላልቆቹማ ምኑ ይወራል... በእነሱ ደስታ እኛም እምባ ተራጭተናል ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአምባገነኖች የመጨረሻ ቀናትና የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁዩኔታ! (አንዷለም አራጌ)

ምዕራቡ ዓለም በዋናነነት በሁለት ዋና ምሰሶዎች ላይ የተመረኮዙ መርሆዎችን በማራመድ ከኮሚኒዝም ጋር የተያያዘውን ትንቅንቅ በድል ለማጠናቀቅ ትልሙን ጣለ ሁሉን አቀፍ ፀረ-ኮሚኒዝም ጦር መስበቅ እና የተጠናከረችና የፈረጠመች እስራኤልን በመኮከለኛው መስራቅ ማደላደል እነዚህ ሁለት ምሰሶዎች ላይ በመመርኮዝ ኮሚኒዝምን የሚያወግዙና የእስራኤልን ደህንነት አደጋ ላይ የማይጥሉ አምባገነኖች ሁሉ በዓለም ዙሪያ በሕዝባቸው ላይ ለሚያደርሱት ምሬትና ዋይታ ኬላው ከፍ ብሉ ተነሳላቸው በኋላ ላይ በፀረ-ሽብር ዘመቻው ተባባሪ ለሆኑ አምባገነኖችም ይኸው ቡራኬ ተቸራቸው

ሙሉውን አስነብበኝ ...