ቂመኛው ፓትሪያርክና በቀሉ! ወንድሙ መኮንን (ለንደን)

ተፈጥሮን ተመክሮ መቼ መልሶት! የዱሮው አባ ገብረምድህን፤ የዛሬው ታጋየይ ጳውሎስም፤ ገና ከጅምሩ ገና ከጠዋቱ የሀይማኖት አባትነት ይቅርና የአንድ ተራ የክርስቶስ ተከታይ ምግባርና ትህትና አልታየባቸውም። ሳይበበቁ መነኮሱ፣ ሳይገባቸው ጰጰሱ፣ በጉልበታቸው ፐተረኩ። (ሙሉውን ጽሁፍ ላማንበብ ይህንን ይጫኑ)

... በቅጥረኝነት የተነሳው ስማችን! (ነብዩ ሲራክ - ከሳውዲ አረቢያ)

እለተ አርብ አመሻሹ ላይ በአንድ የጓደኞች እድርና በኮሚኒቲው ካፍቴርያ በተደረገ ማህበራዊ አገልግሎት ስብሰባ ከተላያዩ ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቸ ጋር የመገናኘት እድል አግኝቸ ነበር። ከወትሮው የተለየ ሞቅ ያለውይይትና ክርክር ያስነሱ ሁለት ጉዳዮች ተከስተዋልና ውይይቱ ቀጠለ። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!

እንኳን ለጠብ ለፍቅርም አትመች!

አትክልት አሰፋ (ቫንኩቨር - ካናዳ)

አራት ኪሎ አካባቢ ትንሽ ቡና ቤት ያላቸውና ቁም ነገርን ጣል በማድረግ ዝናቸው የናኘ እናት በጠባብ የመጠጥ ቤታቸው ውስጥ ሁለት ጠጭዎች ተደባድበው ወደ ጣቢያ ለምስክርነት ተጠርተው ያያቸው የመቶ አለቃ በዝና ያውቃቸው ኖሮ፤ የሚናገሩት የማያጡትን እናት እያየ ‘እማማ ምነው? ምነው?፤ እንዴት ቤትዎ ውስጥ ጠብ ሊነሳ ቻለ?’ ቢላቸው “አረ ዝም ብለው ነው ልጄ ቤቴን ታውቃት የለ እንኳን ለጠብ ለፍቅርም አትመች” አሉት ይላሉ። ዛሬ በየአረብ ሀገራቱ እየተፈጠረ ያለው የህዝብ የነጻነት ጥያቄ ነገ ከጥቁሮቹ ቤት አይገባም ብሎ እጅን ማጣጠፍ የሚቻልበት ሰዓት ላይ አይደለንም። የአለም የፖለቲካ አዙሪት ያለ ህዝባዊ ይሁንታ በኃይል ብቻ ይዘለቃል የሚባልበት ዘመን አክትሞለታል ማለት ይቻላል። አሁን አሁን መንግስትን ለመገልበጥ የሟች ቁጥር እንደጥንቱ፤ እንደዚያ ዘመን በመቶ ሺህዎች መቁጠር የለም። እድሜ ለቴክኖሎጂ። ህዝብ በቃ ካለ ነገ ስራ አልገባም ብሎ ለማመጽ ደቂቃ የማይወስድበት የስልጣኔ ዘመን እየመጣ ይመስላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመጨረሻው ደወል! (አስራደው - ከፈረንሳይ)

ኳ! ኳ! ኳ! ኳ! ሊል ፤ሊደወል፤ የመጨረሻው ደወል፤ ከወዲያ ከሩቅ ከሚካአኤል ደጅ፤ ከማሪያም ደብር፤ ከጊዮርጊስ ደጃፍ፤ ከተክልዬ ገዳም፣ ከእየሱስ ደጅ፤ ሊያስተጋባ የደውሉ ጥሪ፣ በዱር በገደሉ፤ በየመንደሩ፤ በየገጠሩ፣ በየከተማው፤ በክፍላተ ሀገሩ፤ በተራሮች አናት ተሻግሮ እንደገና፤ ኳ! ኳ! ኳ! ኳ! ብሎ ሊጣራ፤ ያልሰማው እንዲሰማ፤ የተኛው እንዲነቃ፣... (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

በሳውዲ አረቢያ የተደበቁ እውነቶች (ክፍል ሰባት - ነብዩ ሲራክ)

ነብዩ ሲራክ - ከሳውዲ አረቢያ

እግረ መንገድ ...

በክፍል 6 ሰበር ሰሞንኛ መጣጥፌ አረቦች 'የቀይ ባህሯን ፈርጥ ሙሽራ' እያሉ የሚያንቆለጳጵሷትን የቀይ ባህር ወደብና የኢንዱስትሪ ማእከል የሆነችው ጅዳን ስላጥለቀለቀው ዝናብና የጎርፍ ናዳ ያላያችሁትን ለማሳየት ያደረኩት ሙከራ ረድቷችሁ ከሆነ መልካም ነው ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

ድንገት ካመጽን፤ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚነሳው አመጽ፡ የቅድመ-ጥንቃቄ ምክሮች፦

ልጅ ተክሌ (ኦታዋ -ካናዳ)

 

ባይሆንም፤ ባይሳካም 66 አብዮትያለምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደምእንደተባለው፡ በኛም ዘመን፡ እነዚህ የሕወሀት/ኢህአዴግ ሀይሎች፡ ያለምንም ደም ለውጥ የሚያመጡበት መንገድ ቢፈጠር ምኞቴ ነው። ነገር ግን ስለተመኘን ብቻ የሚሆን ነገር የለም። ከልምድ እንዳየነው፤ እንደ ልምድ ደግሞ ጥሩ ድግሪ የለም፤ ያለምንም ደም የሚሆን ነገር ያለ አይመስልም። እነሆ ሊነሳ ለሚችል አመጽና ሰፊ የሕዝብ እንቅስቃሴ ያገለግል ዘንድ፡ ከኛ ኢትዮጵያ በኔ አጭር እድሜ ካየሁት፤ ሰሞኑን ደግሞ ሁላችሁም እንደምትታዘቡት በዓረቡ ዓለም ከሚፈጠረው ተነስቼ፡ አንዳንድ ጠቃሚ የአመጽ ምክሮችን ልለግስ ወደድኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ወጣት እንደ ፈንጂ ቦምብ! ከአለማየሁ ገብረማሪያም

በኢትዮጵያ ውስጥ በመታየት ላይ ያለው ሁኔታ ወጣቱ የመፈንጃ ጊዜውን እንደሚቆጥር ፈንጂ መሆኑን ያመለክታል። ወጣቱ በሁለንተናዊ ፍርሀትና መሳቀቅ ውስጥ መሆን፣ ተስፋ ማጣት፣ በሀገሪቱ ላይ እያቆለቆለ የሚሄደው የኢኮኖሚ ቅድቀት፣ በሚተገበረው የኢኮኖሚ ቀውስ እና የፖለቲካውና የሀገሪቱ እድገት መጨንገፍ ዋነኛ መረጋገጫዎች ናቸው። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

የኢትዮጵያ ሕዝብ ... ከዚህ ወዴት! ክፍል 19 (አያልሰው ደሴ)

ያም በውስጥም በውጭም የነበሩና በሀገሪቱ አሉ የተባሉ ድርጅቶችን ሁሉ በአንድ ላይ አጠቃሎ ህብረቱን መፍጠር በመቻሉ አገዛዙ የደረሰበትን መደናገጥ ያስቀረለትና አልፎም ይበልጥ መፈረካከስ እንዲኖር የሚያደርገውን መተናኮል በአዲስ መንፈስ እንዲገፋበት አበረታቶታል ማለት ይቻላል። (ሙሉውን ጽሁፍ ይህንን በመጫን ያንብቡ)

ቀዳማዊ እመቤቶቻችን!

አቢይ ወርቅ

 

አንዳንድ ሴቶች ብልህ ናቸው። አንዳንዶቹ ደግሞ ያውቁበታል። በቅርቡ ወደ ሳውዲ አረቢያ የኮበለሉት የቱኒዝያው ፕሬዝዳንት ቤን አሊ፤ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ያከማቹት ሀብት ቢታገድባቸውም ወደ ድህነት ግን አልወረዱም። እድሜ ላስተዋይዋ ሁለተኛ ሚስታቸው ለላይላ ትራቡልሲ። 1500 ኪሎ ግራም ወርቅ ታጥቀው ነበር የተሰደዱት። ገና ግርግሩ ሞቅ ሞቅ ሲል ነበር ፈጣኗ ላይላ የብሄራዊ ባንክ ገዥውን ወርቅ እንዲያዘጋጅ ያዘዙት።እንደማልችል ስነግራቸው በባላቸው በኩል አሳዘዙኝይላሉ ገዥው። ላይላ ሁሌም ባላቸውን የሚያግባቡበት ሀይል አላቸው። የኛይቱ እ’ቴ አዜብም ያውቁበታል። ባለቤታቸውን ባሻቸው ሰዓት ጥብቅና ለማቆም የሚያግባቡበት ሀይል አላቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቱኒዚያውያን ተገላገሉ፤ ግብጾችም….እኛስ? በሲሳይ አጌና

ቬጋስን ጎብኝቶ፣ ውብ ህንጻዎቿን አይቶ፣ በማራኪ ትእይንቷ ውስጥ አልፎ ስለዚያ ለመጻፍ አለመቻል አለመታደል ነው። እንደኛ ላለው ሀገሩ በጣእር ላይ ላለችበት ከቬጋስ እንጻዎች በላይ ክፋታቸው የተከመረ ገዥዎች አሉብንና በሲዘር ፓላዝ፣ በፕላኔት ሆሊውድ፣ በኤም.ጂ.ኤም ግራንድ፣ በቢላጆ… ወዘተ ካዚኖ ሆቴሎች ስለሚታየው ትንግርት እና ትእይንት መቼ የምናወራበት ጊዜ ሆነ።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ