የያያ አባቦር፣ የበፈቃዱ ሞረዳ እና የተስፋዬ ገብረአብ አስተያየቶችና ምልልሶች
|
|
ከተስፋዬ ገብረአብ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)
እነሆ! ዛሬ ቅዳሜ ነው።
ዕለቱም ግንቦት 9፣ 2009።
ትናንት ደግሞ ግንቦት 8 ነበር። በአበሻ የዘመን አቆጣጠር ልክ የዛሬ ሃያ ዓመት ግድም ”ጥቂት ጄኔራሎች” ኮሎኔል መንግሥቱ ላይ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ አድርገው ነበር። ሳይሳካላቸው በመክሸፉ ዛሬ በሕይወት የሉም። ማንኛውም አጥንት - አስከሬን ሆነዋል። አምላክ የጄኔራሎቹን ነፍስ ይማር። እኒያ ሰዎች ከነሙሉ ችግራቸው ከኮሎኔል መንግሥቱ የተሻሉ ዜጎች ነበሩ ብዬ አምናለሁ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ከበፈቃዱ ሞረዳ
ቀድሞው የጋዜጣችን ተወዳጅ አምደኛ፤ የዛሬው እንደኔው ስደተኛ ያያ አባቦር፤ ”የጋዜጠኛው ማስታወሻ” በተባለው መጽሐፍ ላይ ባለፈው የ”ናፍቆት ኢትዮጵያ” መጽሔት ዕትም ("የአደአው ጥቁር አፈር" ጋዜጠኛ ወይስ የፓርቲ ካድሬ?") ባቀረበው ጽሑፍ መነሻነት ወይንም ተንኳሽነት የተጻፈ ማስታወሻ ነው ይኼ ጽሑፍ። ይህ የእኔ ማስታወሻ የተስፋዬ ገብረአብን ማስታወሻ ሥነጽሑፋዊ ወርድና ስፋት የመመርመር ተልዕኮ የለውም። ዕይታው ወዲህ ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ያያ አባ ቦር - ከሂዩስተን
ባለፉት 48 ወራት ውስጥ ያነበብኳቸውን የአማርኛ መጻሕፍት ሳስብ ሦስት መጻሕፍት በውስጤ ያኖሩት ደስ እስከወዲያኛውም ባይደበዝዝ ደስ ይለኛል። ዘነበ ፈለቀ (የብዕር ስሙ ነው) የፃፈውን ”ነበር”፤ የፕሮፌሠር መስፍን ወልደማርያምን ”የውድቀት ቁልቁለት” እና አንዳርጋቸው ፅጌ የፃፈውን ”ነፃነትን የማያውቅ ነፃ አውጪ” የተሰኙት መጻሕፍትን መጥቀሴ ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ሕብረት ሰላሙ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)
ከጥንቶቹ ጀግኖቻችን፤
እንደሚታውቀው ዐፄ ዮሐንስን እጅግ በጣም ከሚያስደንቃቸውና ከሚያስከብራቸው ታሪካቸው ዋነኛው ለውድ ሀገራቸው ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ዳር ድንበር መከበር በቆራጥነት ይከላከሉ የነበረውና ሕይወታቸውንም የሰዉለት መሆኑ ነው። የጀግናው የዐፄ ዮሐንስ ራስ ተቆርጦ ሱዳን ከተወሰደ ልክ 120 ዓመት ሆኖታል። እስካሁን አልተመለሰም!
ሙሉውን አስነብበኝ ...ልጅ ተክሌ-ከካናዳ
የትችት ብድር፤
ጋሽ ገዳሙ መኳንንት እና አያ ነአምን ዘለቀ
የጀርመኑ ጋሽ ገዳሙ መኳንንት የምወደው፣ የማከብረው፣ የኢትዮጵያ ጉዳይ እለት እለት የሚያቃጥለው፣ የወያኔ ስራ የሚፈጀው፣ ወደዚህ ወደሀገረ ካናዳ ከመጣሁበትና እሱን ካወቅኩበት እለት አንስቶ ስለኢትዮጵያ ያለው ስሜት የማይዋዥቅ፣ አገር ወዳድ፣ ታላቅ ትሁት፣ የሩቅ የሀሳብ ወዳጄና መምህሬ ነው። ጋሽ ገዳሙ ሲናገር፣ ሲጣራ፣ ሲመሰክር እንዴት ደስ ይላል?። አያውቀኝም። ግን ያውቀኛል። ሲጣራ፡ “ተክልዬ፡ የናቴ ልጅ” ሲል ሆዴ ሽብር ይላል። ለማውገዝና ለመሳደብ አይቸኩልም። ተስፋዬን ግን ጠላብኝ። ኢትዮጵያዊውን ተስፋዬ ገብረአብን ጨከነበት።
ሙሉውን አስነብበኝ ...አምሃ ዳኘው (የአንድነት ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የጥናት እና ምርምር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ) This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
ይህ ጽሑፍ በታህሳስ ወር 2001 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ለአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ቀርቦ የነበረ ጥናታዊ ጽሑፍ ነው። አቶ አምሃ ዳኘው የአንድነት ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የጥናት እና ምርምር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ስንት ዘመን “መፈንቅለ መንግሥት”፣ “ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ሊናድ …”፣ “ልንገደል ነበር” እያሉ ቴያትር ይስሩብን?
ልዑልሰገድ (ከአቢሲኒያ) This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
በሥልጣን ላይ ያለው የአቶ መለስ ቡድን በየጊዜው ንጹሃንን ለመግደል ለማሰቃየትና ለማስር የመሰለውን ወንጀል ይፈጥራል። አንዳንዴ ቴአትሩ መልኩን ለወጥ አደረገ ሲባል ሌላ ጊዜ እንዲህ እንደሰሞኑ የተለመደና አስቂኝ የሚሆንባቸው አጋጣሚዎች ሞልተዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ፕሮፌሠር ሰይድ ሐሰን፤ መሪ ስቴት ዩኒቨርሲቲ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)
በመሪ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስና ፋይናንስ ዲፓርትመንት ውስጥ የኢኮኖሚ ፕሮፌሠር የሆኑት ዶ/ር ሰይድ ሐሰን "የግብርናው ነገር እውነታው ሌላ፤ የሚባለው ሌላ” በሚል ርዕስ ባቀረቡት በዚህ ጽሑፍ በኢትዮጵያ ያለውን የግብርና መስክ፣ የመንግሥትን የመሬት ፖሊሲ፣ ድሃው የኢትዮጵያ ገበሬ ያሉበትን ችግሮች፣ በተለይም በኢህአዲግ የሥልጣን ዘመናት የደረሱበትን በደሎች፣ ... በመተንተን የመፍትሔ ሃሳቦችን ጠቁመውበታል። መልካም ንባብ!
ሙሉውን አስነብበኝ ...አማኑኤል ዘሰላም This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. (ሚያዝያ 29 ቀን 2001 ዓ.ም.)
ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት ሁኔታ፣ የፖለቲካ መሪዎችን ተጠያቂ የሚያደርጉ ጥቂቶች አይደሉም። አንዳንድ ሰዎች “መሪ የለንም!” ብለው እስከመናገርም ይደርሳሉ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...