"የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ"!

አብርሃ ደስታ

"ህዝቡ አሁን በአዋጁ ምክንያት የሚያጣው ዴሞክራሲያዊ መብት የለም። ምክንያቱም ከአዋጁ በፊትም ዴሞክራሲያዊ መብቱ ተነፍጎ ነበረ። የአመጹ መንስኤም የዴሞክራሲ እጦት ነውና"

Abraha Desta

የኢህአዴግ መንግሥት የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አውጇል። በሕገመንግሥቱ መሰረት አዋጁ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ይወጣል፤ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይፀድቃል። በሁለቱም ምክር ቤቶች ልዩነት ስለሌለ መፅደቁ አይቀርም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ11ኛው ሰዓት አዋጅ እና ህዝብ

ክንፉ አሰፋ

PM Hailemariam Desalegn

ስለአስቸኳይ ግዜ አዋጁ የጠየቅኩት አንድ የአዲስ አበባ ወጣት ምላሽ አስገረመኝ። “የምን አዋጅ?” ነበር ያለው።

"ትላንት የታወጀው።"

"አቦ መስሚያችን ጥጥ ነው። ... ሚሰማ የለም" አለኝ።

ኃይለማርያም ደሳለኝ ዝም ብለው ኖሯል የደከሙት!

"ለመኖር ብቸኛው አማራጭ ሌላው እንዲኖር መፍቀድ ነው።" ብለው ነበር የሕንዷ ማህተመ ጋንዲ። እነሱ እየኖሩ ሌላው እንዳይኖር ለሚሹ ራስ ወዳዶች ትልቅ መልዕክት ነበረው። ማስተዋል የተሳናቸው ግን "እኛ ብቻ እንኑር" ይህንን የማይቀበል በሙሉ ይጥፋ የሚለውን ጭፍን አመለካከት እንደ ብቸኛ ምርጫ ይዘውታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አልተገናኝቶም፣ ህዝብ ለነጻነት፤ ፖለቲከኞች ለቤተ መንግሥት

ይገረም አለሙ

አልተገናኝቶም

የፖለቲካ ትግል የሥልጣን ትግል መሆኑ እሙን ቢሆንም ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን መሆን በመታገል በህዝብ ድምጽ ተመርጦ ሥልጣን መያዝን ዓላማ ካላደረጉ የቤተ መንግሥቱ ወንበር የሚሆነው ለአንድ ሰው ብቻ በመሆኑ ትግሉ የመጠላለፍ ጨዋታው የጥሎ ማለፍ ይሆንና ሥልጣን ላይ ያለውን ኃይል ዕድሜ በማራዘም ሁሉም የሚመኙትን ወንበር ሳያገኙ ዘመናት ይቆጠራሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሥህተቶችን ሳንደግም የተሻለች ኢትዮጵያን ወደ መገንባት

ገለታው ዘለቀ

በሚመጣው ህዳር ወር ላይ የኢትዮጵያ ልጆች የኦሮሞ ብሔር ልሂቃን ተሰብስበው በከፍተኛ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ሲባል ምክክሩን ወድጄው በስብሰባው ላይ ቢነሳ ጥሩ ነበር ብየ ባሰብኩት ላይ ለመወያየት ነው አነሳሴ። የውይይቱ አሳብ ለሁሉ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ነው በርግጥ። እነዚህ የኦሮሞ ወገኖቼ ከዚህ ስብሰባ በሁዋላ የሚያወጡት የአቋም መግለጫ የኢትዮጵያን ማኅበረ ፖለቲካ ለመለወጥ ትልቅ ድርሻ ያለው የትብብር፣ የአንድነት አሳብ እንደሚሆን አምናለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ለመቼ ሊሆን ነው?

ግርማ በላይ

Amhara protesters

“ዝምታ ወርቅ ነው” - ጥሩ አባባል ነው። “ዝም አይነቅዝም” - ይሄኛውም ግሩም አባባል ይመስላል። “በለፈለፉ በአፍ ይጠፉ” - ጠንከር ያለ ሀበሻዊ መልእክት ያለው ነው፤ ፀረ ዴምከራሲያዊነቱም እንዲሁ ከሌሎቹ አየል ይላል። አዎ፣ የሀገራችን ሥነ ቃላችንም ሆነ አጠቃላይ ባህላዊ ትውፊታችን መናገርንና ሃሳብን በነፃነት መግለጽን አያበረታታም ብቻ ሣይሆን ክፉኛ ይኮንናል። በዚህም ሳቢያ ይሉኝታ እየገነነና ሀፍረትን እየወለደ “የዝምታ የዝምታ” የሚል አንደርብ የተደገመብን ይመስል፤ ውስጥ ለውስጥና በየመሸታ ቤቱ እየተማማን እንኖራለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አለባብሰው ቢያርሱ ባረም ይመለሱ

ይሄይስ አእምሮ

Bishoftu protest 2nd Oct, 2016. (Photo AP)

ማለባበስ በጣም ጎጂ ነው። አሁን የምንገኝበት ማኅበራዊና ፖለቲካዊ አጣብቂኝ እንደእስከዛሬው ዓይነት የሽፍንፍንና የጥግንግን አካሄድን የሚያስተናግድ አይደለም - አምርሯል። አካፋን አካፋ ማለት የሚገባበት ትክክለኛ ጊዜ ላይ ደርሰናል። አንድን እውነት ሺህ ጊዜ ብንሸፋፍነው መገለጡ አይቀርም። ሲገለጥ ደግሞ የሚያስቀይም ስዕል ጎልቶ የሚታይበት አጋጣሚ እየበዛ ይመጣና ከመገናኘት ይልቅ መለያየት የማያመልጡት አሳዛኝ ክስተት ይሆናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቢሾፍቱው እልቂት

ይገረም አለሙ

Irrecha protest, 2nd Oct, 2016

ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረውን የኢሬቻ በዓል ለማክበር ኢትጵያውያን በቢሾፍቱ/አዳማ ከተማ የከተቱት ቅዳሜ መስከረም 21 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ሲሆን፣ በማግስቱ እሁድ ረፋዱ ላይ በምስል ተደግፎ በማኅበራዊ መገናኛ የተሰራጨው ዜና ፈጽሞ ያልተጠበቀ ብቻ ሳይሆን፤ ሊገመት የማይችል ነበር። በአንድ ጣራ ስር ሆነን መርዶውን ከሰማነው መካከል ዕድሜአቸው ስድሳውን የዘለለ አንዲት እናት ለስንቱ እናልቅስ ብለው አንባቸውን አዘነቡት። ሌሎቻችንም በየውስጣችን አለቀስን። ለደቂቃዎች ቤቱ ጸጥ ረጭ አለ። ሁሉም በየራሱ ስሜት ውስጥ ሰምጦ የሚናገር ጠፋ። ዝምታው የተሰበረው ሆራ ኃይቅ ዳር የተሰበሰበ ህዝብ አይደለም ሰላማዊ ተቃውሞ ማሰማት ድንጋይ ቢወረውር ምን ጉዳት እንዳያደርስ ነው በአስለቃሽ ጭስ የሚባረረው በጥይት የሚደበደበው በሚል መልስ የለሽ ጥያቄ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ህወሓት የማይወድቅባቸው የትግል ሥልቶች

ነፃነት ዘለቀ

Irrecha protest 2nd Oct, 2016.

ባሳለፍነው እሁድ በደብረ ዘይት የኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ በአጋዚ የወያኔ ቅልብ ጦር ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችንን ነፍስ እግዚአብሔር ይማርልን! ከዚህች ዘግናኝ ቀን በፊትም ሆነ በኋላ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በዚሁ የወያኔ ጦር ያለቁና ወደፊትም የሚያልቁ ወንድም እህቶቻችንንና ልጆቻችንን መንግሥተ ሰማይን ያውርስልን። ፈጣሪ የነሱን መስዋዕትነት እንደአቤል ንጹሕ ደም ቆጥሮልን የነፃነታችንን ቀን ያፋጥንልን። የቤተሰባቸውንም ሆነ የሁላችንን የተሰበረ ልብ ይጠግን። አሁንስ እጅግ በጣም እየተጎዳን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለዘብተኞችን ማጥቃት፤ አክራሪዎችን ማብዛት

አንዱዓለም ተፈራ

Irrecha protest, 2nd Oct 2016

የሃሳብ ልዩነት፤ ያለ ነገር ብቻ ሳይሆን፤ አስፈላጊም ነው። የተለያዩ ሃሳቦች መከሰት፤ አማራጮችን በመድረክ ላይ በማቅረብ፤ ልዩነቶችን እንድንመረምርና፤ በብዙኀኑ ዓይን የተሻለ የተባለውን እንድንመርጥ ዕድል ይፈጥርልናል። ከነዚህ የተለያዩ ሃሳቦች ተነስቶ ርስ በርስ መወነጃጀሉ፤ አንድም እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን ባይነት ብሎም ራስን የማግዘፍ ጥንውት ነው። ሌላም ትግሉ መልክ ይዞ ወደፊት እንዳይሄድ እንቅፋት ለመሆን የተጠነሰሰ ሴራ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የታሪክ ሂደት ርቃናችንን እንዳያስቀረን

ይገረም አለሙ

የመብትና የነጻነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

ገና እንደባተ ታዋቂ ኢትዮጵያውያንን በተከታታይ ነጥቆ ኀዘን ያስቀመጠን የተሰናበተው የግፍ ዓመት ሊባል የሚችለው 2008 ዓ.ም.፤ የሞት መርዶ፣ የእስር፣ እንግልትና ስቃይ ዜና ሳይለየው ከል እንዳለበሰን ነው ወደ 2009 ዓ.ም. የተሸጋገርነው። ፈጣሪ በቃችሁ ካላለን በስተቀር፤ የ2009 ዓ.ም. አጀማመርም አስፈሪ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ