የመረጃ ነፃነት

ይድነቃቸው ከበደ Yedenekachew Kebedeይድነቃቸው ከበደ

"ሕዝቡ እኔ ማን እንደሆንሁ ይላል?" በማለት እየሱስ ክርስቶስ መረጃ ይጠይቃል፤ ደቀመዛምርቶችም ስለሱ የተባለውን አንድም ሳያስቀሩ ይነግሩታል። እሱም መልሱ እንዲህ ይላቸዋል "እናንተስ እኔ ማን እንደሆንሁ ትላላችሁ?" አላቸው። እነሱም መለሱለት። ሙሉ ታሪኩ ሉቃስ ም.9 ቁ.18 ላይ ይገኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ ለምን ኋላ ቀረች?

ግርማ ሞገስ
ኢትዮጵያ ከውጭ ወረራ ረጅም የነፃነት ዘመን እንዳላት የሀገር ተወላጅ እና የውጭ ሀገር የታሪክ ተመራማሪዎች ያረጋግጣሉ። ይሁን እንጂ በሥልጣኔ ግን ብዙም እንዳልገፋች ይኸው ዛሬ የእኛም ትውልድ ሳይቀር የሚያየው ሕቅ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጆን ኬሪና አልባራዴ አሸባሪዎች ናቸውን?

ግርማ ካሳ
ጆን ኬሪ (ግራ)፣ ቴዎድሮስ አድኀኖም (ቀኝ) John Kerry (L) Tedros Adhanom (R)ኢቲቪ በቅርቡ አንድ፣ በአንድ በኩል አሳዛኝ፤ በሌላ በኩል አስቂኝ ዶኪሚንተሪ ለተመልካቾቹ አቅርቧል። በርካታ ጉዳዮች ተነስተዋል። በዚህ ጽሑፍ የፌዴራል ከፍተኛ አቃቤ ሕግ የሆኑት፣ አቶ ብርሃኑ ወንድማገኝ፣ አንጋፋው ጋዜጠኛ እስክንደር ነጋን በተመለከተ፣ በተናገሩት ላይ ጥቂት ሃሳቦችን ለመገልጽ እወዳለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኬሳ ኬሳ አዱሬን ቢነሳ

(ውስጥ ውስጡን ድመትም ነብር ናት) ክፍል 1
ይድረስ ታሪክ ለምትንሻፈፉ እና በብሔር ለማጋጨረት ለምትጠሩ ሁሉ
ቶሎሣ በቀለ

አባቴ አንድ ነገር ሳይጥማቸው ሲቀር "ኪሳ ኬሳ አዱሬን ቢኒሳ" ይላሉ። በኦሮምኛ፤ "ውስጥ ውስጡን ድመትም ነብር ናት" ማለት ነው። ይህ የኦሮሞን አባባል የተጠቀምኩት የኦሮሞ ልጆች ላይ ነብር መስለው ድመት የሆኑ የተገላበጠ ገመና ያላቸው እንደ እባብ ቆዳቸውን እየሸለቀቁ ወደ እሳት የሚገፉት ስንኩል ሰዎች ስላሉ ነው። ለእነዚህ የታሪክ ዝቃጮች ጥያቄ ማቅረብና እና እውነታውን ማሳየት እፈልጋለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሻምበል ጉታ ዲንቃ፤ ጊዜውን ጠብቆ ይነጋል

መስፍን ወልደማርያም (ፕ/ር)

በአሁኑ ጊዜ ወያኔ ሰውን እያፈረሰ፣ ማህበረሰብን እያፈረሰ ሰማይ-ጠቀስ ሕንጻዎችን በሚሠራበት ጊዜ፣ ከትናንት ወዲያ የሰዎችን ቤቶች አፍርሶ ትናንት የመኪና መንገድ ከሠራ በኋላ ዛሬ መንገዱን አፍርሶ የባቡር መንገድ እየተሠራ አዲስ አበባ በትራፊክ መጨናነቅ መኪና መንዳት አደገኛ በሆነበት ጊዜ፣ ዛሬ ባለሥልጣኖች የሚሠሩት ጠፍቶአቸው የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የሚባለውን በአማካሪዎች ከሞሉት በኋላ ለሚኒስትሮችም አማካሪ መሾም በተጀመረበት ጊዜ፣ ዛሬ በሳኡዲ አረብያ ኢትዮጵያውያን እንደአደገኛ አውሬ እየታደኑ በሚደበደቡበት፣ በሚታሰሩበት፣ በሚደፈሩበትና በሚገደሉበት ጊዜ፣...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሕዝባዊ ብሶት - የከተማ አብዮት?

ተመስገን ደሳለኝ
ባለፈው ሳምንት ኢህአዴግ በከተሞች ላይ የቋጠረውን ስር የሰደደ ጥላቻ ከነመግፍኤው ጨርፈን ከተመለክተን በኋላ፤ ለዛሬ፣ ታላላቅ ግድፈቶቹ ሕዝባዊ ተቃውሞ ለመቀስቀስ ሊኖራቸው የሚችለውን አስተዋፅኦና በአደባባዩ የሚነሱትን ዋና ዋና ጥያቄዎች ለመዘርዘር፤ እንዲሁም ‹‹ማኦኢዝም›› የሚበይነውን ከገጠር የሚነሳ ብረታዊ ትግል፣ ከሰላማዊው የከተማ አብዮት አንፃር ለመፈተሽ ቀጠሮ መያዛችን ይታወሳል፡፡ እናም እንዲህ እንቀጥላለን…

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሰላማዊ ትግል እድገታችን

ግርማ ሞገስ
የዚህ ጽሑፍ ግብ የሰላማዊ ትግል እድገት ከኢትዮጵያ ውጭ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያደረጋቸውን እድገቶች ታሪክ ማጥናት ነው።
ከኢትዮጵያ ውጭ፥
(1) ከክርስቶስ መወለድ ቀደም ብሎ
ጥንታዊ ሮማውያን ከክርስቶስ ልደት 509 አመቶች ግድም ቀደም ብሎ የነበረውን ፍጹም አምባገነናዊ የዙፋን አገዛዝ አፍርሰው ረፓብሊክ የፖለቲካ ስርዓት መሰረቱ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዘመንን ለማሰር

በልጅግ ዓሊ

ይህን 77 እስሩት በገመድ፣

ወደ 78 እንዳይረማመድ።

ይህች አነስተኛ ስንኝ የሰማኋት እንደ ሃገራቸን አቆጣጠር በ1978 ዓ.ም  ላይ ነበር። መቼም የማይረሳ የለም አሥረኛው የአብዮት በዓልም ተረሳ። ያኔ እነ “ጓድ መንግሥቱ“ ድርቁን ደብቀው አሥረኛውን የሥልጣን ዘመናቸውን ለማክበር ውስኪ በመርከብ ያስገቡበትና የተራጩበት ዘመን ነበር። ያኔ እነ “ብጻይ መለስ“ በድርቁ ስም በተገኘው ገንዘብ ጠብመንጃ የገዙበት ዘመን ነበር። የማይረሳ የለም በዚያ ዘመን በድርቅ ያለቀው ወገናችንም ተረሳ። የሕዝብ ገንዘብ ለውስኪና ለጠብመንጃ ያዋሉት ትንሽ ቆይተው ስልጣን ተቀያየሩ። 1977 ማሰር አቅቶን 1983 ከድጡ ወደ ማጡ አነጎደን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አይ ስብሐት ነጋ!

Sebhat Nega ስብሐት ነጋፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

በኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጣን ሳይኖረው ባለሙሉ ሥልጣን፣ እውቀት ሳይኖረው ባለሙሉ እውቀት የሆነ ሰው ስብሐት ነጋ ብቻ ነው፤ እንዲያውም ከዚያም አልፎ ራሱን የቻለ ሉዓላዊ ነፃነት ያለው ግለሰብ ነው ለማለት የሚቻል ይመስለኛል። በዚህ ግለሰብ ላይ የማደንቃቸው ሁለት ነገሮች ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የከተማ አብዮት!

ተመስገን ደሳለኝ - አዲስ አበባ
ከሩሲያውያኑ ቦልሼቪክና ሜንሼቪክ አንስቶ፣ የእኛዎቹ ኢህአፓና መኢሶን በፊት-አውራሪነት እስከ ተሳተፉበት ድረስ ያሉ በደም የጨቀዩ አብዮቶች በሙሉ በከተሞች የተካሄዱ ሲሆን፣ አብዛኛው አጋፋሪዎቻቸው ደግሞ ልሂቃኖች እንደነበሩ በጉዳዩ ዙሪያ የተፃፉ ድርሳናት ያወሳሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ