የወያኔ ነፍስ በበረከት ስምዖን በኩል ስትቃዥ

በረከት ስምዖን  Bereket  Simon

ነፃነት ዘለቀ
አንደኛው መስከረም ጠብቶ ሌላኛው መስከረም እስኪጠባ ድረስ ባሉት የ365.25 ቀናት ውስጥ ስንት ጉድ መስማት እንዳለብን የሚጠቁም አሃዛዊ መረጃ ሊኖር እንደማይችል መቼም ግልጥ ነው፤ ነገር ግን የዘመናችን ኢትዮጵያ የታሪክ ጎርፍ ያመጣብን ከወያኔና መሰሎቹ በስተቀር ሌሎቻችን ያልጠበቅነው ዱብዕዳ ክስተት ምሥጋና ይንሳውና በዬቀኑ የማንሰማውና የማናየው ዕንቆቅልሽ እንዳይኖረን ሆነናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዳር ድንበራችንን ለባዕድ?

Ethiopian Sudan border protestበደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፈን አንሰጥም!
ብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ
ሀገራችን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብቷ የታደለች፣ መልካም የአየር ፀባይ ያላት፣ ህዝቦቿ የራሳችን አኩሪ ባህልና ወግ ያለን፤ የራሳችን መልካም መልክዓ ምድራዊና አሰፋፈር ያለን፤ በጋራ ተሳስረን አብረን የኖርንባትና የምንኖርባት በየትኛውም ዘመን ሉዓላዊነቷ ያልተደፈረ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ሀገር ናት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢዜአ ማደናገሪያ ዜና - አንድ ተጨባጭ ምሳሌ

ፎቶ ከኢዜአ Photo from ENAታደሰ ብሩ
በቅድሚያ የሚከተለውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን (ኢዜአ) ዜና አጣጥሙልኝ።
በባሌ ዞን በንብ ማነብ ፓኬጅ የተሳተፉ አርሶ አደሮች ከ53 ነጥብ 7 ሚሊዮን የሚበልጥ ገቢ አገኙ
ጎባ ጥር 10/2006፦ በባሌ ዞን ከእርሻ ስራ በተጓዳኝ በንብ ማነብ ፓኬጅ የተሳተፉ አርሶ አደሮች ከ53 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ማግኘታቸውን የዞኑ የእንስሳት ሀብት ልማትና ጤና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ክህደት ከአናት ሲጀምር

በቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ

እውነት ቤት ስትሠራ ... ውሸት ላግዝ ካለች
ሚስማር ካቀበለች ... ጭቃ ካራገጠች
ቤቱም አልተሠራ ... እውነትም አልኖረች።

... እንደዚያ ነው በባቢሎን ዘመን። የአንዱ ቋንቋ ከአንደኛው ይዘበራረቃል ... መግባባትና መረዳዳት ብርቅ ይሆናል። በጠራ አማርኛ የተጣፈውን በጉግማንጉግኛ በመተርጐም ከውስጡ የሚፈልጉትን ብቻ አለፍ አለፍ እያሉ ያነቡታል። እናም የራሳቸውን ትርጉም ይሰጡታል። ፍየል ወድያ ... ቅዝምዝምም ወዲህ ይሆናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ነፃነታችንን መልሱልን!?”

ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

የኢህአዴግ መራሹ መንግስት ‹መዝገበ ቃላት› ለነፃነት የሚሰጠው ትርጓሜ ‹አራምደዋለሁ› ከሚለው ግራ-ዘመሙ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ብያኔ አንፃር የሚተነተን በመሆኑ፣ የየትኛውም ተቋም ነፃ ሆኖ የመንቀሳቀስ መብት ላይ ረዣዥም እጆቹን ደጋግሞ እየጫነ ሲጨፈልቅና ሲያስጨፈልቅ ለመኖሩ በርካታ ማሳዎችን ማቅረብ ይቻላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ወደው አይስቁ”

ክንፉ አሰፋ

የጥምቀት በዓልን ተሰባስበን በምናከብርበት አንድ ቤት ውስጥ ካለወትሮው ፓልቶክ ተከፍቷል። በዚያ የበዓል ድባብ፤ የፓልቶክ ንትርክ መከፈቱ ሳይገርመን፣ ርእሱ የሁላችንንም ቀልብ መሳቡ። በእርግጥ አንድም ቁም ነገር በንግግሩ አልሰማንም። አዲሱን ቋንቋ ልዋስና የፓልቶኩ ተናጋሪዎች ሙድ  የሚያስይዙ ነበሩ። ሰዎቹ በዚህ ከቀጠሉ የእነ ክበበው ገዳን ገበያ መዝጋት እንደሚችሉ አያጠራጥርም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሕገ- መንግስት ወይስ ዶክመንተሪ ፊልም?

ተመስገን ደሳለኝ
አምስተኛው ዙር አገር አቀፍ ‹‹ምርጫ›› እንደወትሮው ሁሉ በቀጣዩ ዓመት ሊደረግ በዕቅድ ተይዟል፤ ወሬውም ከወዲሁ ለፖለቲካ ፍጆታነት እየዋለ ነው፤ ኢህአዴግም በበኩሉ ‹አውራ ፓርቲ›ነቱን ከቀደመው በበለጠ አጠናክሮ የሚቀጥልበትን ሴራ ፈትሎ በመግመድ ውሎ ማደሩን ገና በማለዳ እያቀላጠፈው መሆኑን እየታዘብን ነው፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድነት ፓርቲን በተመለከተ መልስ ለኢሳቱ ፋሲል የኔዓለም

ፋሲል የኔዓለም  Engi. Gezachew Shiferawግርማ ካሳ
የኢሳት ባልደረባ አቶ ፋሲል የኔዓለም "የአንድነት ፓርቲ የመጪው ጊዜ ፈተና" በሚል ርዕስ የጻፉትን ዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ አነበብኩ። አቶ ፋሲል ጽሑፉን ያቀረቡት እንደ ግል አስተያየት እንደመሆኑ፣ ኢሳትን በዚህ ውስጥ ጣልቃ አላስገባም። የአንድነት ፓርቲ አዲሱ ሊቀመንበር፣ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው፣ ሀገር ውስጥ ለሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ከሰጡት ቃለ ምልልስ፣ የሚከተለውን በመጥቀስ ነበር አቶ ፋሲል ጽሑፋቸውን የጀመሩት፤ 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንዱዓለም ግንቦት ሰባት ከተባለ፤ እኔም ግንቦት ሰባት ነኝ

አንዱዓለም አራጌ Andualem Aragieግርማ ካሳ

"በሕገመንግሥቱ የመደራጀት መብታቸው የተጠበቀላቸው ፓርቲዎችን አልከሰስንም። ፓርቲዎችን ግን ሽፋን አድርገው ሥርዓቱን ወይንም ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመናድ እንንቀሳቀሳለን የሚሉ ኃይሎችን ግን ዛሬም፣ ነገም፣ ሕጉን የማስከበር ግዴታና ኃላፊነት ስላለብን ከመከሰስ አያመልጡም ማለት ነው።"

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ