ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች
እንኳን ለ1442ኛው የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ! ረመዳን ሙባረክ!
ኢትዮጵያ ዛሬ

ለተከበሩ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ሰላ አቦምሳ

የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ + ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

ለተከበሩ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፣ ለጤናዎት እንደምነዎት። በእርሶና በፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ መሃል ያለውን የሃሳብ ልውውጥ ከተመለከትኩ በኋላ የግሌን አስተያየት ለመስጠት ወሰንኩኝ። የሃሳብ ልውውጡን እንደተመለከትኩኝ ከሆነ መሪራስ አማን በላይ አንዱ የክርከሩ አካል እንደሆኑ ተረዳሁ። በዚህም መሰረት ስለ መሪራስ አማን በላይ ለማወቅና እሳቸውን በአካል ለማግኘት ካልሆነም ያሳተሟቸውን ለማግኘት ሞከርኩ። በአካል ማግኘት ባይሳካልኝም ፤ 10 የሚሆኑ ያሳተሟቸውን መጻሕፍት አገኘሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሳባ ንግሥት ትሩፋትና የዶክተር ጌታቸው ኃይሌ ስህተት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Prof. Getatchew Haileሙሉጌታ ውዱ

መግቢያ፤

ዶክተር ዶናልድ ሊቫይን የሚባል በቺካጎ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ የሆነ አንድ "አይሁድ" አሜሪካዊ የዛሬ አሥራ ስድስት አመት አካባቢ እኔ ወደምኖርበት አካባቢ መጥቶ ደወለልኝና በቀጠሮ ተገናኝተን በአንድ የኢትዮጵያ ምግብ ቤት ውስጥ አብረን መመገብ ጀመርን። በጭውውታችን መካከል ስለ ኢትዮጵያውያን "ምሁራን" አነሳና አስተያየቱን ይሰጠኝ ጀመር። ከሁሉም የሚወደው (my favorite በሚል አገላለፅ) እንድርያስ እሸቴ የሚባለውን ሰው እንደሆነ ነገረኝ። አከታትሎም በእንግሊዝኛ አግቦ አነጋገር ኢትዮጵያዊ ሊቅ (በምዕራባዊ ትምህርት) እኮ የለም አለኝ። የተጠቀመው የእንግሊዝኛ ቃል "true scholar" የሚል ነበር። ያን ጊዜ ብዙ ኢትዮጵያውያን "ምሁራን" (በምዕራባዊ ትምህርት) አሉ ብየ የማስብበትና ደረቴን የምነፋበት ጊዜ ስለነበረና ገና ብዙ ያልመረመረ የጎልማሳነት ስሜት ሰለነበረኝ በሰውየው አነጋገር ስሜቴ ተጎዳ። እኔም ጥድፊያ ከሚበዛባቸው ሥራዎቼ ፋታ ሳገኝ የኢትዮጵያን ጉዳይ እና ታሪኳንም ማጥናት ጀመርኩ።የዶክተር ዶናልድ ሊቫይንን ሥራዎችም በቅርብ ማየት ጀመርኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ከፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ (ክፍል ሁለት)

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ (ፕ/ር)

Merriras Aman Belay Certofocate

ውድ ፕሮፌስር ጌታቸው ኃይሌ

"ለውድ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ፣ የውውይቱ መንስኤ" በሚል ርእስ ባለፈው ሳምንት ያቀረቡአቸውን የትዕቢት ናዳዎችን፣ የብስጭት ውርጅብኞችንና የመከላከያ እሩምታዎችን ንቄ ትቼ፣ በእርስዎ ደረጃ ዝቅ ላለማለት ስል ከነሱ ውስጥ መልስ መስጠት ያለብኝን ብቻ በመጀመሪያ እሰጥና ወደ ቀድሞ ጥያቄዎቾ እመለሳለሁ። መልሶቼ ሁሉ ተደምረው የሌሎቹንም ግለሰቦች ሁሉ ጥያቄዎች ይመልሳሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። በጥንቃቄና በቀና ልብ ያነበቡት ሰዎች ሁሉ መጽሐፉ ራሱ ጥያቄዎቻቸውን መልሶላቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለፕ/ር ጌታቸው ኃይሌና ለፕ/ር ጳውሎስ ሚልኪያስ መልስ

የአንባብያን ድምፅ: 1 / 5

Star ActiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

Prof. Getachew and Fikres bookየኢትዮጵያ ታሪክ ጽሁፍ ገና ተጀመረ እንጂ አላለቀም

ስሜ ላቀች አክሊሉ ይባላል፣ እዚህ አሜሪካ አገር ከመምጣቴ በፌት በፈረንሳይ አገር ፓሪስ ጥቂት ዓመታት ኖሬአለሁ፤ እኔ የታሪክ ጸሃፊም ተመራማሪም አይደለሁም። ብዙ ግዜም በሚድያ ለሚወጡ ጹሑፎችም መልስ አልጽፍም።

ነገር ግን የኢትዮጵያን ታሪክ ጥናት ከሚያካሂዱ ሰዎች ዘንድ(ነፍሳቸውን ይማርና ከእነ ፕሮፌሰር ዮሴፍ ቱቢያና)ለተወሰነ ጊዜ ተሳትፌአለሁ። የአገሬም ታሪክ እግዚአብሔር ኢትዮጵያዊት አድርጎ እስከፈጠረኝ ድረስ በሰፊው ይመለከተኛል ብየ አስባለሁ። አሁን ይህን ሰሞን በፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ መጽሐፍ ላይ የተነሳውን ስድብና ውዝግብ ማየቴ በግድ ካለሁበት እንድወጣ አድርጎኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የውይይቱ መንሥኤ፤ ለውድ ፕሮፌሰር ፍቅሬ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

161230 prof getachew and fikre
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ

ለውድ ፕሮፌሰር ፍቅሬ፤ ከጌታቸው ኃይሌ

“የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ” ብለህ የጻፍከው፣ እውነተኛው የዘር ምንጭ አይደለም ጥሩ ተረት ነው ብየ ምክንያቴን ብሰጥ ቁጣህ ከመጠን አልፎ ስድብ ውስጥ ገባህ። “ተረቴን እንደታሪክ አልቀበል ያልክ ሁሉ ጌታቸው የደረሰበትን አይተህ ተቀጣ” ማለትህ ይመስላል። ውይይታችን በመጽሐፍህ ውስጥ ስላካተትካቸው ሐሳቦች እንጂ፣ አንተንና አንዳንድ አራጋቢዎችን እንደመሰላችሁ፣ ስላንተ ወይም ስለኔ አይደለም። እኔ ማስረጃ ይዤ ተረቶች ናቸው ያልኳቸውን አስተዋፅኦችህን አንድ በአንድ ከነማስረጃዬ ዘርዝሬያለሁ፤ ጉዳያችን ያለው እዚህ ላይ ነው። ለናሙና ያህል ከዘረዘርኳቸው ዓሥራ ሦስት ስሕተቶች ውስጥ የአማራው ሕዝብ አባት የተፀነሰው እባሕር ውስጥ ነው ያልከው ስሕተት ይገኝበታል። ስሕተቶች ያልኳቸውን ስሕተቶች አለመሆናቸውን አንድ ባንድ እንድታስረዳ አንባቢህ ይጠብቃል። እውነተኛ ታሪክ ለመሆናቸው ማስረጃው ስድብና ውሸት አይደለም። መልስ መስጠት ካልቻልክ አፍረህና አርፈህ ዝም በል። ማፈርና መልስ አለመስጠት መብትህ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!