ተላላኪው ማን ነው? ታማኝ በየነ (ሊመለከቱት የሚገባ)

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ተላላኪው ማነው ታማኝ በየነ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር በመወያየት በተለይ ህወሃት መራሹ የኢህአዴግ መንግስት ተቀናቃኞቹን ማጥቂያ በማድረግ "የኤርትራ ተላላኪዎች" የሚላቸውን ተቃዋሚዎች የተለያዩ አዋጆችን በማወጅ ሲወነጅል መሰንበቱ ይታወቃል። ታማኝ በየተ በዚህ ዙሪያ በምስልና በድምጽ የተደረፉ መረጃዎችን በማጣቀስ ተላላኪው ማን ነው? ይላል። ምላሹን ከቃለምልልሱ ያገኙታል።
(ቪድዮውን ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)

ቆይታ ከአንዳርጋቸው ጽጌ እህት ጋር! "ለአንዳርጋቸው አታልቅሱ!" እስከዳር ጽጌ

የአንባብያን ድምፅ: 3 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar InactiveStar Inactive

ዳዊት ከበደ ወየሳ - አትላንታ

ምሽት ላይ ከአንዳርጋቸው ጽጌ ታናሽ እህት ጋር ቀጠሮ ነበረን። ወሬያችንን በስልክ ላለማባከን ስንል በአካል ተገናኝተን ለመጨዋወት ነው የተቃጠርነው። ከእስከዳር ጋር የሚኖረኝ ቀጠሮ የአሁኑን የአንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ ለመነጋገር ቢሆንም፤ ሳልወድ በሃሳብ ወደኋላ እንድመለስ መገደዴ አልቀረም። በምርጫ 97 ወቅት (ከዘጠኝ አመታት በፊት) አንዳርጋቸው ጽጌ በየእለቱ ወደ ቅንጅት ቢሮ በማምራት የማደራጀት እና የቅስቀሳ ስራዎችን ያከናውን ነበር። የሰኔ የመጀመሪያ ሳምንት ግን ወጣቶች መንገድ ላይ የሚረሸኑበት፤ የቅንጅት ደጋፊዎች የተባሉ ሰዎች በገፍ እየታፈኑ ወህኒ ያሚጋዙበት ወቅት ሆነ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቃለ ምልልስ ብጹእ አቡነ መቃሪዮስ ከተክለሚካኤል አበበ ጋር

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

የኩቤክና የአውስትራሊያ ሊቀ ጳጳስ የሆኑትና የአውሮፓና የምስራቅ አፍሪካ ም/ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ መቃርዮስ በተለይ ለሃዋርያዊ ስራ አገልግሎት በቫንኩቨር ካናዳ በተገኙ ጊዜ ከተክለሚካኤል አበበ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቆይታ ከአቶ ሃብታሙ አያሌው ጋር

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

አቶ ሃብታሙ አያሌው ከቫንኩቨር ካናዳ ዘወትር ቅዳሜ ከሚተላለፈው መለከት ራዲዮ ጋር ቆይታ አድርጓል።

  • አቶ ሃብታሙ አያሌው በተለይ በአሁኑ ሰአት በጎንደር አደባባይ እየሱስ መንግስት ምረጡኝ በማለት ስለሚያድለው 8ሺህ ብር ይናገራል።
  • በጎንደር 5 የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች ታስረዋል
  • አቶ ሃብታሙ ለኢትዮጵያ ያለውን ምኞትና ተስፋም ተጠይቋል
  • በአራት ደህንነቶች ታጅቦ ወደ ቢሮው እንደሚሄድም ያወጋዎታል

(ሙሉ ቃለ ምልልሱን ለማዳመጥ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)

ቃለ ምልልስ ከህግ ባለሙያዋ ኤልሳቤት ወሰኑ ጋር (ሰማያዊ ፓርቲ)

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

የህግ ባለሙያ የሆነችውና የሰማያዊ ፓርቲ የዲሲፕሊን ኮሚቴ አባል ኤልሳቤት ወሰኑ ከመለከት የኢትዮጵያ ራዲዮ (ቫንኩቨር) ጋር ያደረገችው ቃለ ምልልስ:-

- ኤልሳቤት በማርች 8 ቀን በአዲስ አበባ በተደረገ የሩጫ ውድድር ላይ ተቃውማችኃል ስለተባሉና ለ11 ቀናት በእስር ቤት ተጥለው ስለነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የምትለው አለ


ሻምበል ጉታ ዲንቃ ከመለከት ራዲዮ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ሻምበል ጉታ ዲንቃ ታላቁ የሰላም አባት በመባል የሚታወቀው የነጻነት ታጋይ በነበረበትና ኢትዮጵያ ውስጥ ለወታደራዊ ስልጠና በከፍተኛ ምስጢር ወታደራዊ ስልጠና  ሲወስድ ለህይወት አድን ጥበቃ ተመድበው ከነበሩት ሁለት ኮማንዶዎች አንዱ የነበሩ ሲሆን ማዲባ በ95 ዓመታቸው ህይወታቸው ካለፈ ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር መገናኛ ብዙሀን መነጋገሪያ የነበሩ ጡረተኛ ወታደር ናቸው። ከቫንኩቨር ካናዳ ዘወትር ቅዳሜ የሚተላለፈው መለከት ራዲዮ በተለይ የማንዴላ ጠባቂ የነበሩትን ሻምበል ጉታን ከትውልድና እድገት ጀምሮ በወቅቱ የነበራቸውን ደመወዝ፤ የቀረበላቸው 2 ሺህ ፓውንድ የፈጠረባቸው ጉጉትና የተቋቋሙበት መንገድ፤ እንዲሁም ይህ ለ52 አመታት የተደበቀ ምስጢር አወጣጥን በሚመለከት ሰፊ ማብራሪያ ይሰጣሉ። (ቃለምልልሱን ለማዳመጥ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)

'ነውጥ አልባ ትግል'፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ ወንድሙ ስለአዲሱ ዶክመንታሪ ፊልም ይናገራል

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

በዓለም ዙሪያ ተበታትነው ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከነ ጋንዲ ምን ይማራሉ? የሳውዲ ዐረቢያ መንግሥት በዜጎቻችን ላይ እያደረሱ ያሉት ግፍና መከራን እንዴት መቋቋም ይቻላል? በሌሎችስ ላይ እንዳይደርስ እንዴት መከላከል ይቻላል? - 'ነውጥ አልባ ትግል’ ለእነዚህና ሌሎች ተዛማች ጥያቄዎች ምላሽ አለው። ጋዜጠኛ ኤልያስ ወንድሙ ስለዚሁ አዲስ ዶክመንታሪ ፊልም ይናገራል። አስተናጋጁ የኢሳቱ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ነው።

 

ቃለ ምልልስ ከዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ጋር

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

“ኢሕአዴግ ሃገሪቱን ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንዳይከታት እሠጋለሁ” ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ

ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር ናቸው፡፡ ላለፉት 30 ዓመታት በአሜሪካ ኖረዋል፡፡ የየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆኑና ሆነውም የማያውቁት ዶ/ር ዳኛቸው በሀገሪቱ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ግን ምሁራዊ አስተያታቸውን በየጊዜው ይሰጣሉ፡፡ ከዶ/ር ዳኛቸው ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሎሚ አዘጋጅ ቶማስ አያሌው ያደረገው ቆይታ ይህንን ይመስላል፡-

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ