”የኔ አጋርነት በኢትዮጵያ ውስጥ ለዲሞክራሲ ሥርዓት ከሚታገሉ ኃይሎች ጋር ነው” አና ጐሜዝ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

 'ለተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጥሪ የማቀርበው ነገር፤ ህዝቡ በምርጫ እንዳይሳተፍ የሚከለክል መልዕክት ማስተላለፍ አይገባቸውም'

 

Ana Gomesበአውሮፓ ፓርላማ የሶሻሊስት ፓርቲ አባልና በኢትዮጵያ ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም. ተካኺዶ በነበረው ምርጫ የአውሮፓ ምርጫ ታዛቢ ልዑካን ሊቀመንበር የነበሩት አና ጐሜዝ በቅርቡ ከዩሮ ጋዜጣ ጋር በኢትዮጵያ ስላለው የዲሞክራሲ ሁኔታ፣ ስለኦነግ (ስለየኦሮሞ ነፃነት ግንባር)፣ በቀጠናው ስላለው መረጋጋትና ”የቅርብ ወዳጃቸው ናቸው” ተብለው ስለሚጠቀሱት በዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ስለተቋቋመው የግንቦት 7 ንቅናቄ ዙሪያ ያደረጉትን ቃለ-ምልልስ ለኢትዮጵያውያን አንባብያን በሚመች መልኩ በአማርኛ ቋንቋ ተርጉመን አቅርበነዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአሜሪካ ምርጫ በኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ዕይታ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Bulcha Demeksa
አቶ ቡልቻ
”… በሰው ሀገር ምርጫ ማንስ ቢመረጥ እኔ ምን አገባኝ? ከዚህ በፊት ሌሎች ጋዜጦች ጠይቀውኝ አስተያየት የለኝም ብያለሁ …” ሲሉ የኦፌዲን ሊቀመንበር አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፤ ዓለም ጆሮውን ተክሎ የሚከታተለውን፣ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አስመልክቶ ማን እንዲመረጥ ይፈልጋሉ? በሚል እንቢልታ ጋዜጣ ላቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዶ/ር ኃይሉ አርኣያ ስለ38ቱ የፓርላማ አባላት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Dr. Hailu Araya“ፓርላማ የሚገኙት አባላቶቻችን በተቻለ መጠን ጠቃሚ ሥራ ሊሠሩ በሚችሉበት ሁኔታ ጥረት ማድረግ አለባቸው” ዶ/ር ኃይሉ አርኣያ

በምርጫ 97 በቅንጅት ስም ፓርላማ የገቡ 38 የፓርላማ አባላት በአንድነት ፓርቲ ስም እንዲመዘገቡ ፓርቲው ለአፈ-ጉባዔ ጽ/ቤት ማመልከቻ ማስገባቱን ጥቅምት 1 ቀን 2001 ዓ.ም. ዘግበናል። የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ኃይሉ አርኣያ ጉዳዩን አስመልክቶ ከእንቢልታ ጋዜጣ ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቆይታ ከፕሮፌሠር መስፍን ጋር

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

«በኢትዮጵያ ሠላማዊ ትግል አያዋጣም የሚባለው ከአሜሪካ ወይም ከአውሮፓ አይደለም» ፕሮፌሠር መስፍን ወ/ማርያም

Prof. Mesfin Woldemariyamፕሮፌሠር መስፍን ወ/ማርያም የሰባዊ መብት ታጋይ በመሆን ለረጅም ዓመታት የኢሰመጉ ፕሬዝዳንት ሆነው አገልግለዋል። ከዛም ቅንጅትን ትተው እስከወጡበት ጊዜ ድረስ በፖለቲካ ትግል ውስጥ ቆይተው የነበረ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ በአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል ናቸው። ፕሮፌሠር መስፍን ከፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ አስራት ጣሴ ጋር በመሆን በአሜሪካን ሀገር በዘጠኝ ስቴቶች ለሚገኙ ደጋፊዎቻቸው ቅስቀሳ ሲያደርጉ ቆይተው ባለፈው ሣምንት ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል። ፕሮፌሠር መስፍን የትጥቅ ትግልን አጠንክረው ሲቃወሙ ይደመጣሉ። ጽዮን ግርማ (የእንቢልታ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ) ስለትጥቅና ሠላማዊ ትግል ስልት ከፕሮፌሠር መስፍን ወ/ማርያም ጋር ቆይታ አድርጋለች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"በኢትዮጵያ ረሃብ የለም" ጠ/ሚ/ር መለስ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

PM Meles Zenawiየታይም መጽሔት ዘጋቢ በአዲስ አበባ ተገኝቶ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር ስለ ወቅታዊ የረሃብና እርዳታ ጉዳዮች ያደረገውን ቃለምልልስ ሙሉ ቃል በዛሬው ዕለት (እሁድ ነኀሴ 4 ቀን 2000 ዓ.ም. / August 10, 2008) የተነበበውና ሀገር ቤት የሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ በአማርኛ ተርጉሞ እንደሚከተለው አቅርቦታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቅንጅት ስም የተሰበሰበው ገንዘብ የማነው?

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ድጋፍ አሰባሳቢዎቹ መልስ አላቸው

በኢ/ር ኃይሉ ሻውል የሚመራው ቡድን ቅዳሜ ሰኔ 13 ቀን እና እሁድ ሰኔ 14 ቀን 2000 ዓ.ም. ጠቅላላ ጉባዔ አድርጎ አመራሮቹን መምረጡ አይዘነጋም። በጠቅላላው ጉባዔ ም/ፕሬዝዳንትና የሰሜን ኢትዮጵያ ቀጠና ኃላፊ ሆነው የተመረጡት አቶ አባይነህ ብርሃኑ፤ የጉባዔው መዝጊያ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸውን መዘገባችን አይዘነጋም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ዶ/ር ብርሃኑ ያቋቋመውን ንቅናቄ አልተቀላቀልኩም። የሚወራው ሁሉ ሐሰት ነው” ዶ/ር አድማሱ ገበየሁ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ የቀድሞ ም/ሊቀመንበርና፤ ቅንጅት አዲስ አበባን ተረክቦ ቢሆን ኖሮ ለአዲስ አበባ በምክትል ከንቲባነት ተመርጦ የነበረው ዶ/ር አድማሱ ገበየሁ በተለይ በሀገር ውስጥ ባሉ አንዳንድ የመገናኛ ብዙኀን ግንቦት 7 ንቅናቄን እንደተቀላቀለ ተደርጎ የሚናፈሰውን ወሬ አስመልክቶ በሀገር ውስጥ የሚታተመው የእንቢልታ ጋዜጣ ቃለምልልስ አድርጎለታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዳንኤል እጮኛ የነፃነት እህት ስትሆን፣ ዓቃቤ ሕጉ የዳንኤል የ20 ዓመት ጓደኛው ነው

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

Netsanet Demissie (left), Daniel Bekele (right) and Yemesrach Demissie (Daniels fiancé, Netsanets syster in the middle)
ከአቶ ዳንኤል በቀለ እና ከአቶ ነፃነት ደምሴ ጋር የተደረገ ቃለምልልስ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሚያዝያ 4 ቀን 2000 ዓ.ም. April 12, 2008) መጋቢት 19 ቀን 2000 ዓ.ም. ከእስር የተፈቱት የሲቪል ማኅበረሰብ መሪዎች አቶ ዳንኤል በቀለ እና አቶ ነፃነት ደምሴ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለእራሳቸው፣ ስለቤተሰቦቻቸው፣ ስጓደኞቻቸው፣ ስለሥራዎቻቸው፣ ስለእስሩ፣ ስለክሱና የፍርድ ሂደቱ፣ … ሀገር ውስጥ ከሚታተመው እንቢልታ ለተሰኘው ሣምንታዊ ጋዜጣ ቃለምልልስ ሰጡ።

 

የአቶ ነፃነት ደምሴ እህት ወ/ት የምሥራች ደምሴ የአቶ ዳንኤል በቀለ እጮኛ እንደሆነችና በቅርቡም ተጋብተው ባለቤቱ እንደምትሆን ከቃለምልልሱ ለመረዳት ተችሏል። ከዚህም ሌላ ክሱን በዋነኛነት ይመራ የነበረውና “በሞት ፍርድ ይቀጡልኝ” እያለ ሲከራከር የነበረው ዓቃቤ ሕግ ሽመልስ ከማል ከአቶ ዳንኤል በቀለ ጋር የ20 ዓመት ጓደኛሞች እንደነበሩ በቃለምልልሱ ላይ ይፋ ሆኗል። 

 

አቶ ሽመልስ እና አቶ ዳንኤል ከዩኒቨርስቲ ወደ ሥራ እስከተሰማሩበት ጊዜ ድረስ፣ አንድ ማዕድ አብረው ቆርሰው፣ ያላቸውን ሣንቲም ለሁለት ተካፍለው አብረው በልተውና፣ አብረው ጠጥተው ከኢትዮጵያ እስከ እንግሊዝ አገር ዘልቀው፣ በአንድ አልጋ ላይ ተኝተው፣ የሆድ የሆዳቸውን ያወሩ ጓደኛሞች ነበሩ። ቃለምልልሱን ያደረገችላቸው ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ስትሆን፤ እንቢልታ ጋዜጣ ያወጣውን ሙሉውን ቃለምልልስ እንደሚከተለው አቀርበነዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"ገበሬው ነፃነት ካላገኘ ችጋር ሁልጊዜ በኢትዮጵያ ይኖራል"

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

 

Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 26 ቀን 2000 ዓ.ም. April 4,2008) አንጋፋው መምህርና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆኑት ፕሮፈሰር መስፍን ወልደማርያም በተለያዩ ገዳዮች ላይ በማተኮር በኢትዮጵያ ውስጥ በየሣምንቱ ከሚታተመው እንቢልታ ከተባለ ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደርጋሉ። የኢትዮጵያ ዛሬ ዝግጅት ክፍል ይህንን ታሪካዊ ቃለ ምልልስ በየሣምንቱ የሚያቀርብላችሁ ሲሆን፣ ዛሬ ፕሮፌሰሩ ከጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ጋር በድርቅ ወይንም በፕሮፌሰሩ አጠራር በ”ችጋር” ጉዳይ ላይ ያደረጉትን ቃለምልልስ ይዘንላችሁ ቀርበናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...